Get Mystery Box with random crypto!

ደህና ነበርኩ እኮ ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ፣ እንደል | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ደህና ነበርኩ እኮ

ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ
በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ፣

እንደልጅ ጨርቅ ኳስ አይኔ ሲንከባለል፣
ያላወቀ መስሎ በአንቺው ሳይደለል

መርሳት ራሱ ራሴን ሳይረሳው
የሸጥኩት ደስታዬ በውድ ሳለምነው

ፊቴ ወዝ ሳያጣ  ትዝታ ሳይተካ
አይኔ ሳያብጥ የእንባ ውሃ ሳይነካ

ፀጉሬ ሳይጨበርር ቅባት ሳያጣው
ከንፈሬ ሳይደርቅ ድርቅ ሳይመታው
አይኔ ውሃ ሳያጣ ትዝታሽ ሳይሞላው
የድሮ መልኬን ጎረቤት ሳይጠላው

ያኔ ገና ሳልወድሽ በነበርኩ
ማሪያምን ነው ምልሽ እኔ ደና ነበርኩ


@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት