Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ? ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ?? ____ ተይ በታቦቱ ተይ በሰማእቱ ተይ በአርባራቱ ላስይ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ጥያቄ?
ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ??
____
ተይ በታቦቱ
ተይ በሰማእቱ
ተይ በአርባራቱ

ላስይዝሽ እባክሽ በእናትዋ ባታ
በተወለድሽባት በቅብአ ቦታ

ታቦት ብዘረዝር ጎንደሬ አረጉኝ
አድባር ብጠራ ጎጃሜ ነህ አሉኝ

ይቆጠራል እንዴ ታቦት በአንድ አድባር
እምነት ለዓለም ነው ማን ሰጠው ለምድር

ጥያቄ ?

ታቦትን ለጎንደር የሰጠውስ ማነው
አባይን ለጎጃም የሰጠውስ ማነው
የኔን ልብ ላንቺ የሰጠውስ ማነው
እንደው አትፍረጂ ያው ያንቺ አምላክ ነው
ወንድ አዳም ልቤን፥ በሔዋን ሚያመልከው
ያፈቀረ ንፉግ እግዜር ከየት ሊያቀው?

መልስ ?

ታቦቱን ማንሳቴ
ጠበሉን ማንሳቴ
እንድትመጭ ነበር ያስያዝኩሽ በእምነቴ

እምነቴ አልበጀኝ ለልቤ ባረዳ
ነፍስ አፀድቅ ተብሎ ስጋ ለሚጎዳ

ምንድነው መልሱ?

ጥያቄ እኮ አለኝ ወትሮም ሰለስት ላሳዬ፣
ሰው ልብ ይላሉ አድባሩን ላዋዬ

ልብ ግን ስጋ ነው?
ከስጋ ተርታ ነውስ ሚመደበው?
ወይስ
ከነፍስስ ነው?
በእግዜር ዘንድ በሰማይ ሚታዬው ?

እና
የስጋ ከሆነስ ለፅድቅ ይሆናል?
አንቺን ማፍቀሬ ለነፍስስ ይባላል?

መልሽልኝ ????

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት