Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቶስ ሞኝ ነው ? ክርስቶስ ግን ሞኝ ነህ ድጋም ልበድልህ ድጋም ላሰቅልህ ድጋም ላስገርፍህ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ክርስቶስ ሞኝ ነው ?

ክርስቶስ ግን ሞኝ ነህ
ድጋም ልበድልህ
ድጋም ላሰቅልህ
ድጋም ላስገርፍህ
ለእኔ ለማረባው ለምን ትለፍለህ?
አዳም ብልጥ ሁኗል ለምን ትሞኛለህ?

ሰቅየህ ላይበቃህ ጭራሽ መግረፌ
አዳምን ስመስል በአንተ ዘንድ መትረፌ

እንኳን መታውህ ጅራፍ ሰነዘርኩ፣
ያኔ ባትምረኝ እኔን ባልነበርኩ፣


የጀርባህ መስመር ላይ የመስመሩ ጅማት
ፍቅርን ነው የሳለ ወይስ ዙፍን ጥማት
እያለ ሲጠይቅ በደምህ ላይ ክፍት

አዳምም ሞኝ ነው ሴጣንን ይወዳል
ፍቅርን እየገፍ ፍቅር ላይ ይተርፍል

እንደው ባምን እጂ በምን ለምመካ
የወገብህ ስፍት ስንት ግፍን ለካ
የሔዋን እንባ ነው? በደምህ ምትለካ
ያዳምን አጥም ነው በስጋህ ምትለካ

አምላክ ሆይ ንገረኝ ከበትርህ ወርደህ
ሰውነትክን ከፍለህ በደምህ አስታጥበህ
ላተረፍከው አዳም አንተ ሙሴው ነህ ?
ወይ? ከእርሱ ትበልጣለህ?

ቀድሶ ማይፀና መርምሮ ይደክማል፣
ስጋ መከፈሉ ከውሃ እንዴት ይለካል፣
ዓለምን ማትረፍ ከእስራኤል ይደርሳል?
ሙሴን ለፈጠረው ከአምላኩስ ይበልጣል?

(አዳም ሞኝ )

ስጋህ እስኪያምህ በስጋ ተመተህ፣
ደምህ ትን እስኪልህ በጫፉ ተወግተህ፣

ለማን ይሆን ዋጋው ሰው እኮ ሞኝ ነው
አንተን እየረሱ ሙሴን ነው ሚያነግሰው?
አሁን አላየህም እጂ ሰው እኮ ጌታ ነው !

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት