Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜው ኢትዮጵያውን ከ ኤርትራ የተፈናቀሉበት ነበር። ኤርትራውያንን ከ እናት ሐገራቸው ኢትዮ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ጊዜው



ኢትዮጵያውን ከ ኤርትራ የተፈናቀሉበት ነበር።


ኤርትራውያንን ከ እናት ሐገራቸው ኢትዮጵያ ለማፈናቀል በተጠራው ስብስባ ላይ ኤርትራዊው የዮሮና አባት የተናገሩት


" እኔ ምንም እንኳን በ ዘር ኤርትራዊ ብሆንም የተወለድኩት ኢትዮጵያ ነው ።


ሳድግ ዘረኝነት አናቴ ላይ ወጥቶ ወደ እናት ሐገሬ ኤርትራ ካልሄድኩ አልኩ፤

የኤርትራን የመገንጠል መብትም እደግፍ ነበር


ኤርትራ እንደሄድኩ ግን የገጠመኝ ሌላ ነበር


ኢትዮጵያ ትናፍቀኝ ጀመር፤ ጎረቤቶቼ አብሮ አደግ ጓደኞቼ ሁሉ ነገር ናፈቀኝ።

አንዳንዴ የምንመኘውን ስለማናቅ ነው መዓት የምንጠራው


የተሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለምና


ይባስ ብሎ ታመምኩ፤ ህክምናም ፀበልም ሞክሬ አልተሳካም።

በስተመጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ ተሻለኝ።

አንዳንድ ሰዎች ከ ተወለዱበት አከባቢ ርቀው መኖር አይችሉም።

አንዲት ልጅ አሳዳጊዎቿ ዕውነተኛ ወላጆቿ እንዳልሆኑ ስታውቅ፤ ዕውነተኛ ወላጆቿን ለማየት ትጓጓለች። ያ ተፈጥሯዊ ዘረኝነት ይባላል ።


ውሎ አድሮ ግን ወደ አሳዳጊዎቿ ትመለሳለች። ክፉንም ደጉንም አብራ ያሳለፈችበት ቤተሰብ ይናፍቃታል። ከማታቃቸው ወላጆቿ ይልቅ ያሳደጓት እንደሚበልጡ በጊዜ ሂደት ትረዳለች።

"