Get Mystery Box with random crypto!

ከጨለማ ያውጣን ከሞት ቤቱ አዳር ተነሱ ይበለን መጥቶ እንደአላአዛር ድምፆችን ይስማን እንደመቅደላ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ከጨለማ ያውጣን ከሞት ቤቱ አዳር
ተነሱ ይበለን መጥቶ እንደአላአዛር

ድምፆችን ይስማን እንደመቅደላዊት፣
በግንቡ ይጎብኜን መጥቶ በኛ ሌሊት፣

እንደመሼ መስሎ የፍሲካ ማታ
አጋጣሚ አይደለም ሳይፀና ወገግታ
በ ዘጠኝ ሰአቱ የተነሳ ጌታ

ሊያመስለን ቢሻ ነው የኛኑ ወገግ ማለት
ፀሀይ ሳትወጣ ሌቱ ሳይነጋበት

ክርስቶስ ሌባ ነው በሌሊት ይመጣል
ክርስቶስ ሊዘርፈን በሌቱ ይገኛል

ሀር ነጩን ለብሶ ሌሊት ሳይታዬን
ጉዝጓዝ መከራችን ሳይታይ ሊሰርቀን
ሰርቆ ጠራርጎ ፍቅር ሊያበድረን

ፍቅር ሊተካብን በልባችን ሳንቃ፣
ክርስቶስ ይሰርቃል
ሊነጋጋ ሲል እንባን እና ሲቃ፣
__

ይነጋል ሲነቃ ይነጋል

# አይዞን ፍሲካችን አለ #


# ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat