Get Mystery Box with random crypto!

ዮሮና የተወለደው በ አርባምንጭ ከተማ ሲሆን፤ የ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ናዓው ጊሽን(በሁለት ሲ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ዮሮና የተወለደው በ አርባምንጭ ከተማ ሲሆን፤

የ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ናዓው ጊሽን(በሁለት ሲካፈል) ሄዛው ጊሽን (በሶስት ሲካፈል) ዕያለ ሂሳብን በ ጋሙኛ ቋንቋ ተማረ።


ወዘተ




ወዘተ



ካላልን የማይገባቹ አንባብያንን አስተውለናል።


ቀስ ዕያለ የአፃፃፍ መንገዳችንን እንደምትለምዱት ተስፋ እናደርጋለን።

በ ጋሞ ውስጥ ሶስት ዓይነት ማህበረሰብ አለ።

ሰዎች



መናዎች


ጎረሞቴዎች



መናዎች ብዙን ጊዜ ፀሐይ በደመናዎች ሳትከለል ከዘነበ ሚስት ያገባሉ ተብሎ ይታሰባል። የስራ ዘርፋቸው ሸክላ ሰሪና ብረት ቀጥቃጭ ናቸው።



ጎረሞቴዎች ብዙን ግዜ ከሰው አይቀላቀሉም።


ለብቻቸው ጫካ ውስጥ መኖር ያዘወትራሉ።


አልፎ አልፎ አንዳንዶች ከሰዎች ጋር ተመሳስለው ይኖራሉ።


ርስበርስ በጢንዚዛ መልዕክት ይለዋወጣሉ ተብሎ ይታሰባል።


አልፎ አልፎ ከሰው ልጆች ጋር በመጋባት አዲስ ዝርያን ይፈጥራሉ። ነገር ግን ከ ጎረሞቴ ጋር የተጋባ ማንኛውም ሰው ከፍተኛ የሆነ መገለል ይደርስበታል።