Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-13 10:54:26 ጊዜው



ኢትዮጵያውን ከ ኤርትራ የተፈናቀሉበት ነበር።


ኤርትራውያንን ከ እናት ሐገራቸው ኢትዮጵያ ለማፈናቀል በተጠራው ስብስባ ላይ ኤርትራዊው የዮሮና አባት የተናገሩት


" እኔ ምንም እንኳን በ ዘር ኤርትራዊ ብሆንም የተወለድኩት ኢትዮጵያ ነው ።


ሳድግ ዘረኝነት አናቴ ላይ ወጥቶ ወደ እናት ሐገሬ ኤርትራ ካልሄድኩ አልኩ፤

የኤርትራን የመገንጠል መብትም እደግፍ ነበር


ኤርትራ እንደሄድኩ ግን የገጠመኝ ሌላ ነበር


ኢትዮጵያ ትናፍቀኝ ጀመር፤ ጎረቤቶቼ አብሮ አደግ ጓደኞቼ ሁሉ ነገር ናፈቀኝ።

አንዳንዴ የምንመኘውን ስለማናቅ ነው መዓት የምንጠራው


የተሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለምና


ይባስ ብሎ ታመምኩ፤ ህክምናም ፀበልም ሞክሬ አልተሳካም።

በስተመጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ ተሻለኝ።

አንዳንድ ሰዎች ከ ተወለዱበት አከባቢ ርቀው መኖር አይችሉም።

አንዲት ልጅ አሳዳጊዎቿ ዕውነተኛ ወላጆቿ እንዳልሆኑ ስታውቅ፤ ዕውነተኛ ወላጆቿን ለማየት ትጓጓለች። ያ ተፈጥሯዊ ዘረኝነት ይባላል ።


ውሎ አድሮ ግን ወደ አሳዳጊዎቿ ትመለሳለች። ክፉንም ደጉንም አብራ ያሳለፈችበት ቤተሰብ ይናፍቃታል። ከማታቃቸው ወላጆቿ ይልቅ ያሳደጓት እንደሚበልጡ በጊዜ ሂደት ትረዳለች።

"
700 viewsያቢ ነኝ, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:53:37 አዲስ የዘለሰኛ ግጥም ተለቀቀ ግቡና እዬት


https://vm.tiktok.com/ZMYGG85Eo/
478 viewsጥ ቁር ዝምታ, 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 11:59:14
ዛሬ በtik tok ቻናሌ

አንድ የዘለሰኛ ግጥም እለቃለው
እናንተስ ፍቃደኛ ናችሁ ??? ከሆናችሁ ከታች ባለችዋ link ግቡ እና ጠብቁኝ

https://vm.tiktok.com/ZMYGbV6pn/



follow
@geez_mulat
663 viewsጥ ቁር ዝምታ, 08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 18:50:19 ዮሮና ዮሮና

ናዓው ጊሽን

ሄዛው ጊሽን

ብለን እንዳልተማርን

ጆራችንን ይዘን በዕንብርክክ

እንዳልሄድን

ጢንዚዛ እንዳልነዳን


አህያ እንዳልጋለብን

ዛሬ ግን ታደገና

ተረት መሰለ ልጅነታችን

ያለፈ ትዝታችን

የሗላ ታሪካችን።
1.3K viewsያቢ ነኝ, 15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 01:23:06
ዛሬ...ሆሳዕና
ነገ ሆሳዕና
ምን ያደርግና
ሰላም የለምና
ፍቅር የለምና
ብዬ ሳልጨርስ በገና

ክርስቶስ በአህያይቱ በጉዝጓዝ መምጣቱ
ዛሬን ሊያሳይ ይሆንን እውነቱ፣

ነገ ላይ
ያቺ አህያ ሰላም ጭና፣
ስጋውን ረግጣ ክርስቶስ ሁና
ታምጣልን በጉዝጓዝ በ'ለተ ሆሳዕና

ነገ
ሰላም ሆኖ ታዬኝ ደዋዊው ሲነጣ፣
ታየች አህያይቱ በእውን ስትመጣ፣
ቄጤማ ግጫው ለፍቅር ሲዋጣ፣

ይታዬኛል ግጫ በራሳችን አስረን፣
ይታዬኛል ሰላም
በገዛ እረፍታችን ነፍሳችን ጋብዘን ፣

ይታዬኛል ጉዝጓዝ ይታዬኛል ሲራዝ፣
እንደ ሰለሜ ባሪያ ብርቱ ሰላም ሲጋዝ፣

ፍቅር ባሪያ አርጎን ሲበተን ጉዝጓዝ
ታዬኝ ጥላቻ  በበርሃ ሲጋዝ..

ይታዬኛል....


___ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
127 viewsጥ ቁር ዝምታ, 22:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 09:36:46 በአንድ ወቅት ስለ ባለ ዕፀ-መሰውሩ ተማሪ በስፋት ይወራ ነበር፤ ግቢው ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር አንድ ሰሞን።

ተሰውሮ ሴቶች ዶርም ስለሚገባው፤ ተሰውሮ ካፌ ገብቶ ስለሚመገበው ተማሪ።

ተሰውሮ መምህራን ቢሮ ገብቶ ፈተና የሚሰርቀው፤ የሚወዳትን ልጅ ሻወር ስትወስድ ክፍሏ ገብቶ የሚሻፍደው ተማሪ።

ተሰውሮ የተማሪዎትን ታብሌትና ላፕቶፕ የሚሰርቀው ተማሪ።


አንድ ቀን፥ ሳያስበው ኤሌክትሪክ ያዘውና ተዝለፍልፎ ወደቀ።

ሆስፒታል በሄደና በታከመ፤ በዳነም ነበር።

ምንም ዋጋ አለው ፤ አይታይምና የሚረዳው ሰው አላገኘም።

****።



ዮሮና የልጁን ታሪክ እንዳነበበ ፈገግ አለ።

" ሕይወት እንደዚል ናት፤ አንዳንድ ሰዎች ፀጋቸው መጥፊያቸው ይሆናል። ገንዘባቸው፤ ዝናቸው፤ስልጣናቸው፤ ዕውቀታቸው ፤ ተስጥዖዋቸው መጥፊያቸው የሆኑ ሰዎች አሉ።" ሲል አሰበ።




ይቀጥላል
980 viewsያቢ ነኝ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 14:53:50 ራት ቀረበ፤ ዓይብ ነበር የተመገቡት፤ የዓይቡ ጣዕም ግን ለየት ያለ ነበር፤ መድሐኒት መድሐኒት ይል ነበር። ወዲያው ዕንቅልፍ ወሰደው ፤ ከዕንቅልፉ ሲነቃ ከፊት ለፊቱ የሻማ ብርሀን ነበር።

"ትኩረት አድርግ።" የጎረሞቴው ድምፅ ነበር።

" አንድ ስለምታውቀው ሰው ፤ አስብ። በቀላሉ ስለ ሰካራሙ ተበጀ ፤ ለምሳሌ ነው ታድያ።" የጎረሞቴውን ድምፅ ተከትሎ የዮሮና አንጎል ይፈስ ጀመር።

በቀላሉ በሰካራሙ ተበጀ አዕምሮ ውስጥ ገብቶ ተሸጎጠ።

ተበጀ ምን ግዜም ጠጥቶ ወደ ቤቱ ስለሚመለስ፤ የሰፈሩ ሕፃናት ምን ጊዜም እንደተተናኮሉት ነው።

አንጎሉ ውስጥ ሆኖ ተበጀ ለምን መጠጥ እንደሚጠጣ አነበበ።

ሚስቱ ሌሊት ሌሊት የሚያስጮህ ዛር አለባት፤ እንዲሁ እንደጮኽች ዕንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር ያድራል። የሚስቱ ሕመምና ዕንቅልፍ ማጣት ተባብረው ሊያሳብዱት ደረሱ። ከማበድ መስከር ይሻላል የሚል መላ አመጣ። የሌሊት ዕንቅልፉን የሚመልሱለት፤ ጭንቀቱን የሚያስረሱት፤ ሐዘንና ድባቴውን የሚረሳባቸው፤ መደበቂያዎቹ፤ መጠጦቹ፤ ሱሶቹ።

ከቀን ወደ ቀን ወደማይወጣው ሱስ እየገባ እንደሆነ ይታወቀዋል።


"ሚስቱን ግን ምን ያህል ቢወዳት ይሆን " ሲል አሰበ ዮሮና።

ሚስቱን በጣም ከመውደዱ የተነሳ እያያት ትናፍቀዋለች። የፈለገ ብታናድደው ብታሰቃየው ጧት ፊቱ ስትቆም ማታ ያሳለፈውን ስቃይ ሁሉ ይረሳዋል። ፊቷን በማየት ብቻ በውስጡ ይሰፍናል። አዕምሮው ረፍት ያገኛል። ዘላለም ፊቷ ተንበርክኮ ባያት፤ ባያትና ባመለካት እንኳን ሊፈታት ይቅርና።



ያለወትረው በጣም በማምሸቱና የሚሄድበት የገጠር ከተማ ራቅ በማለቱ፤ ሰካራሙ ተበጀ በአቅራቢያው ከምትገኝ ከተማ ገብቶ ለማደር ወሰነ።

ብር ስለጨረሰ ወደ አንዱ ቤት በረንዳ ተጠግቶ ተጋደመ።

።****

ዮሮና በ ሰካራሙ ተበጀ አዕምሮ ሆኖ፤ በተበጀ ጆሮ ያዳምጣል።

የተበጀን በረንዳ ላይ መተኛት ተከትሎ፤ የቤቱ መብራት በራ።

የሚጨቃጨቁ ባልና ሚስት ድምፅ ይሰማል።

በሩ ተከፍቶ ፤ ባል ወጣ፤ ሚስት ከባል ጀርባ

የተኛውን ሰካራም ቀሰቀሱት፤ ምስኪን ሰካራም


ቤቱ መኝታ የለው


ውጭም አባረሩ።

ቤቱ ካልተኛ


ደጅ ካልተኛ



የት ይተኛ??



ይቀጥላል

For more https://t.me/hiyawnet
1.2K viewsያቢ ነኝ, 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 18:12:02 "ጎሮሞቴ ለመሆን ወስነህ ስለመጣህና ልትቀላቀለን ስለወሰንክ ደስተኛ ነኝ።" አለ ጎሮሞቴው።

"ምን??" ወጥመድ ውስጥ እንደገባች ዓይጥ ሽምቅቅ አለ።

"ምነው ጎረሞቴ መሆን አትፈልግም?? አንድ የኛ ዘር የሰው ዘርን ሲያገባ ሚስቱን ወደ ጎረሞቴነት የሚለውጥበት መድሓኒት አለው። " አለ ጎረሞቴው።

"ግን ማነው ጎረሞቴ መሆን የሚፈልግ?? ማንም ጎረሞቴን ማግባት አይፈልግም።" አለ ዮቶር በመገረም።

"ምክንያቱም ስለምትንቁን??" አለ ጎረሞቴው በመኮሳተር። ዮሮና የሚናገረው ጠፍቶት ዝም ጭጭ አለ።

"ምርጫው ያንተ ነው፤ እንደ ሰዎች በባዶ ኩራትና ዝና መኮፈስ አልያም ሆነህ የዩኒቨርስን ሀይል ማጣጣም፤ የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ ፤ በሰዎች አዕምሮ ሰርጎ መግባት፤ ጅቦችን መጋለብ...ወዘተ ወዘተ"

አለ ጎረሞቴው ለመረጋጋት እየሞከረ።

"እና ሰዎችን ማሳመም ፤ ማሰቃየት ብሎም መግደል?? መጨረሻችሁ ሲዖል ነው የሚሆነው።" ዮሮና አለች ለመከራከር በሞከረ ቁጥር ራሱን ችግር ውስጥ እየከተተ እንደሆነ ይሰማዋል።

" እና እዚህ ቤት ለምን መጣህ??" ጎረሞቴው ነበር።

"ለማወቅ።"

"በንግግር ብቻ፤ ሁሉንም ነገር ልታውቅ አትችልም ልጅ።የግድ ያን ነገር ሆነህ መገኝት ይገባሀል። ያንድን ሰው ችግር የምትረዳው እሱ ባለፈበት መንገድ ስላለፍክ ሳይሆን እሱን ስትሆን ነው።"

"እና?"


"እናማ የግድ ጎረሞቴ መሆን አለብኽ።"



"ከዛ ምልከታው ሲጠናቀቅ ወደ ሰውነት የምትመልሰኝ ከሆነ።"





"ይ_ሁ_ና_" የተንኮል ፈገግታ ፊቱ ላይ እየተነበበ።
206 viewsያቢ ነኝ, 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:07:21 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ፤ ከመናዎች ቀጥሎ ጎረሞቴ ከሚባሉ ዘሮች ጋር ጓደኛ ሆነ። ማታ ማታ ጎረሞቴዎች ወደ ጅብ ይቀየራሉ የሚል አሉባልታ ነበር፤ አፈታሪኮችም በስፋት ይነገሩ ነበር።

አንድ ቀን ዮሮና፤ ስለ አፈታሪኮቹ ዕውነታነት ከ ጎረሞቴ ጓደኞቹ አንደኛውን ሊጠይቀው ወሰነ።

ልጠይቀው፤ ወይንስ በጥያቄዬ ይናደድ ይሆን?? እያለ ከራሱ ጋር ሲሟገት ከቆዬ በሗላ እንደምንም ጥያቄውን አቀረበ።

"ቡዳ ነህ??" አለ በፍርሃት የጥያቄው ምን ሊያስከትል እንደሚችል ባለማወቅ።

*









*



*



*





*






"ይላሉ።" አለው ጥያቄው ምንም ስሜት እንዳላሳደረበት ሁሉ።

" ማለት?? አይደለሁም ለማለት ነው??" አለ ዮሮና ግራ ተጋብቶ፤ ሁሉም ነገር ተረት ተረት አፈታሪክ ኖሯላ??

" የሰው ልጅ የተለየ ተሰጥዖ ይዞ ሊወለድ ይችላል። ያንን ተሰጥዖ በልምምድ ሊያሳድገው ይችላል፤ አንዳንድ ዕፅዋቶችም ሀይልህን ለማውጣት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ጀነቲክስ ወይንም ዝርያም የራሱ አስተዋፅዖ አለው። "

" እና ሰው ወደ ጅብነት ወይንም ወደ መቀየር ይችላል?"

ዮሮና በድንጋጤ ፈዞ ጠየቀ።

"ዛሬ ማታ ወደ እኔ ቤት ከመጣህ ሁሉንም በቅርቡ የምታውቀው ይሆናል።"
210 viewsያቢ ነኝ, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 15:27:33 ተናገር ብዕሬ

ማስክህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስገደል በዘሬ፣
ሌባ በወጣበት ምላስ ሻጪ ገብቶ፣
ህዝብ ሲያስጨበጭብ ምላሱን አብልቶ፣
የወጣውን ሌባ ሲነቅፍ ሲያረክስ፣
ለምስኪኑ ህዝብ ሞት ፅዋ ሲደግስ፣
እውነት ጎህ ቀደደ እውነትን ገለጠ፣
ጭብጨባው ረገበ እሮሮው በለጠ፣
አንድ ሳምንት እለቅሶ አንድ ሳምንት ዳንኪራ፣
አገር ዘማ ስታይ የራሷን መከራ፣
ምስኪን ሲፈናቀል ገዳይ ቤት ሲሰራ፣
ጭቀት ሲደራረብ በተራ በተራ፣
ብለን ስንጠይቅ አድነን ሙሴያችችን፣
ችግኝ ተከለልን ጥላ ለሬሳችን፣
ኮፈንህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስታረድ በዘሬ!
ሙሴ መጣ ብሎ ያጨበጨበን ህዝብ፣
አንገቱን ለካራ አስከሬኑን ለዝንብ
ማስክህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስሰደድ በሀገሬ።


Mak
594 viewsbelaya, 12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ