Get Mystery Box with random crypto!

#ለፈገግታ #የቲጂዋ_ፍቅሬ #ግፍ_አይሆንብሽም ገንዘቤን ገፍግፌ፣ ኪሴን አራግፌ። ጊዜዬን ገድዬ፣ ሰ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ለፈገግታ
#የቲጂዋ_ፍቅሬ
#ግፍ_አይሆንብሽም
ገንዘቤን ገፍግፌ፣
ኪሴን አራግፌ።
ጊዜዬን ገድዬ፣
ሰዓትን በድዬ።
ባይኔ አፍጥጬ፣
ብሌኔን ቆንጥጬ።
ስጠብቅሽ ስውል፣
አፍርሼ ውል።
ስትዘልቂ በፈገግታ፣
ልቤ ሀሴት አግታ።
በዝምታ ስትቀጪኝ፣
በስንብት ስትንጪኝ።
ትተሽኝ ስታመሪ፣
ሀዘኔን ስታበጂለት መሪ።
ሌላ ምንም አልልሽም፣
ብቻ ግፍ አይሆንብሽም!?
16/12/2008
#መኮንን_ዮሴፍ
Fb ላይ ተፃፈ