Get Mystery Box with random crypto!

#ሰርዶ_አይብቀል እውነቱን ንገሪኝ እስኪ ልጠይቅሽ፣ እኔ ከሞትኩኝ ሌላ ታገቢያለሽ። አህያ ነኝ ት | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ሰርዶ_አይብቀል
እውነቱን ንገሪኝ እስኪ ልጠይቅሽ፣
እኔ ከሞትኩኝ ሌላ ታገቢያለሽ።
አህያ ነኝ ትቼ ከሄድኩኝ፣
ሰርዶ አይብቀል እላለሁ ከተሰናበትኩኝ።
በደጉ ጊዜ የገጥኩት ገላ፣
ያመኛል በሰው እጅ ሲበላ።
ስደቢኝ ግዴለም ብለሽ ራስ ወዳድ፣
አንቺን ማፍቀሬ ግን ነው የኔ ልማድ።
እሱ እኮ አጠናብኝ በሽታዬን፣
ትረሽው ይሆን ጠረን ሽታዬን።
አካል ሰውነትሽ ለምለሙ ሳርሽ፣
ብቀማው አብዳለሁ ሳልገኝ ከስርሽ።
#መኮንን_ዮሴፍ