Get Mystery Box with random crypto!

#ቸር_ወሬ ጆሮዬን ደቅኜ ወደ አፌ ያሾልኩት፣ ቸር ወሬ ብዬ ለአምላኬ የነገርኩት። ብስራት ነበር | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ቸር_ወሬ
ጆሮዬን ደቅኜ ወደ አፌ ያሾልኩት፣
ቸር ወሬ ብዬ ለአምላኬ የነገርኩት።
ብስራት ነበር ማሬ መምጣትሽ፣
በባዶ መመለሱ አራተኛው ጣትሽ።
በቀጭን ጩኸት ሕዋሴ አረዳኝ፣
አሞራ ከበራፍ አንቋሮ አወላዳኝ።
ያለወትሮው ሽፋሽፍቴ እንዲያ ሲርገበገብ፣
መክረሜን አንሾካሾከ ካንቺ አጠገብ።
ዘንባባ ሰራልሻለሁ ለቀለበቱ ቅዶሽ፣
አስበሽበት ጠብቂኝ የፀሀይዋን ግርዶሽ።
#ማክቤል