Get Mystery Box with random crypto!

የዜግነት ክብር ተምሬ ያደግሁት... የዜግነት ክብር በማለት ዘምሬ class የምገባ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የዜግነት ክብር
ተምሬ ያደግሁት...
የዜግነት ክብር በማለት ዘምሬ
class የምገባ...
ስለ ሰንደቅ ክብር ብዙ ተመክሬ
ከክላስ ውስጥ ደግሞ...
የቀለሙን ትርጉም በ civics ተምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
ሶስቱንም ቀለም...
በወርድ እና እርዝመት በእኩል ቀምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
.ልዩነታችንን እንደ ጌጥ ቆጥሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
የክልልን ትርጉም
ብዙውን ሳላውቀው ብዙ ሳልረዳ
አስራ አንዱን ክልል
ሁሉንም አይቼ እንደ እናቴ ጓዳ
ሁሉን ቋንቋ ልወርስ
ሀሳቤን ስሸክፍ ምኞቴን ስነዳ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
በሶስቱ ቀለም በአንድ ሰንደቅ ታጥሬ አረንጓዴ...ቢጫ...ቀይ
በልቤ ዙፋን ላይ በእኩል ቀምሬ
ታድያ ምነው ዛሬ
አረንጓዴ ቢጫው ቀለሙ እየጠፋ
ቀዩ ቀለም ብቻ ከሰንደቁ ሠፋ
የዜግነት ክብር...
@peom_by_peom
by Belaya