Get Mystery Box with random crypto!

ልቡ ክው አለች፤ በቤቱ ውስጥ ከሱና ከሰራተኛቸው በስተቀር ምንም እንደሌለ አሰበና ተረጋጋ። አጠገቡ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ልቡ ክው አለች፤ በቤቱ ውስጥ ከሱና ከሰራተኛቸው በስተቀር ምንም እንደሌለ አሰበና ተረጋጋ። አጠገቡ የተኛችው ሴት ስለመሆኗ በረጅም ፀጉሯ ተረድቷል።

ለመጀመሪያ ግዜ ስለ ሰራተኛቸው መልክ ማሰብ ጀመረ፤ ረጅም ጥቁር ፀጉር፤ ትንንሽ ዓይኖች፤ ድርቅ ያለ ከንፈር፤ቆራጣ አፍንጫ፤ ነጭ የቆዳ ቀለም፤ ምንም የሚስብ ነገር የሌለው ጣረሞት ፊት።


አጠገቡ የተኛችውን ሴት ፊት መለየት አልቻለም፤ ጀርባዋን ሰጥታው ነበር የተኛችው።

ሰራተኛዋ ከሆነች ስለምን የራሷን መኝታ ትታ እርሱ ጋ መጣች??

አዕምሮው ሌላ ነገር ማሰብ ጀመረ፤ ግን ከመጣችስ በሗላ ጀርባ ሰጥቶ መተኛትን ምን ይሉታል??

ግራ ተጋባ፤ ሁኔታዎችን በትዕግስት ሊጠብቅና ከሷ ምንም ዓይነት ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ላይነካት ቃል ገባ።