Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-03-28 16:04:24 ከወር በፊት የተፃፈ ሚስጥር!

የትህነግ/ህወሓት ሰው ከአንድ ወር በፊት ለጦርነት ዝግጅት 13 አባላት ያሉት የጦርነት ቅስቀሳ ቡድን መመስረቱን ፅፎ ነበር። ከአንድ ወር በፊት የተፃፈበት እንጅ ቡድኑ ከዛም ቀደም ብሎ የተደራጀ ነው። ከእነዚህ ትህነግ ከፍሎ ለጦርነት ዝግጅት እንዲሰሩ ካዋቀራቸው መካከል አራቱ የሚዲያ ባለቤቶች ውጭ አገር የሚኖሩ ናቸው።

ስለ ፕሪቶሪያ፣ ወልቃይትና ራያ፣ አማራና ትግራይ ጉዳይ ሲዘግቡ ወይንም ሀሰት ሲያስተላልፉ የሚውሉት ደግሞ ከስር ያሉት ሰዎች ናቸው።

"የትግራይ ጀኔራሎችን አናግሬያቸዋለሁ ጦርነት አይፈልጉም" ሲል የከረመው ኤርሚያስ ለገሰ የጦርነቱ ቀስቃሽ ዋና ቡድን ሆኖ ነው። ሴኮ ቱሬ በድሮን ሲመታባቸው ድሮን የማያገኘው ሴኮ ቱሬን አግኝተዋል።
13.6K viewsedited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-26 15:49:30
17.8K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-26 15:49:24 እጅ ከፍንጅ የተያዘው ትህነግ /ህወሓት

ትህነግ በማያወላዳ መልኩ በአማራ ላይ የጦርነት ውሳኔ መወሰኑን ሳይደባብቅ የካቢኔ ውሳኔውን በመግለጫ አሳውቋል። ይህ መግለጫ የተሰጠበት ዋናው ምክንያት ትህነግ የጦርነት ዝግጅት ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ ስለተያዘ፣ ለዚህም ወንጀሉ ማቅለያ ይሆነኛል የሚል አማራ ላይ ብቻ እንደሚዘምት ለማሳወቅ ነው!

1) አብይ አህመድ የጓዳ ስምምነቱ አላዋጣው ሲል የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ አንድ ወር ውስጥ ትጥቅ መፍታት የነበረበትን የትህነግ ታጣቂ አሁን ትጥቅ ለማስፈታት ሽር ጉድ ይዟል። ትህነግ ደግሞ ላለመፍታት ብቻ ሳይሆን ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው። ትህነግ ትጥቅ ላለመፍፋት ራቅ አድርጎ የዘጋጀበትን ጦርነት በቅርብ ለማድረግ ጥድፊያ ላይ ነው። አብይ ይህን የትህነግ ዝግጅት ሰሞኑን በቲቪ ከመናገሩ በፊት ለአደራዳሪዎቹም፣ መቀሌ ደርሰው ተመልሰው ለሚጨቀጭቁት አምባሳደሮችና ሌሎች አካላትም በተለያየ መልኩ ካደረሰ ቆይቷል። አደራዳሪዎቹን ጨምሮ ሌሎች አካላትም የጦርነት ዝግጅቱ እንዳለ አሳምረው ያውቃሉ። ትህነግም በቅርብ ጦርነት ልትጀምር ነው ተብሎ በዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በመረጃ ተነግሮታል።

2) በቅርብ ዘፀአት በሚል አካውንት የሚፅፍ የትህነግ ደጋፊ ትህነግ በውጭ አገርና በአገር ቤት ኮሚቴ አዋቅሮ ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን ፅፏል። የትህነግ አባላት ቃል በቃል "ጦርነት አንፈልግም" እያሉ የሚፅፉት ዝግጅቱን ስለሚያውቁ ነው። የአንድ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር ስብሰባ አድርገው ሲወጡ "እኛ ጦርነት እንደማንፈልግ፣ ህወሓት ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን ነግረናቸዋል" ብሎ ፅፏል።

4) ስለ ትህነግ የጦርነት ዝግጅት በርካታ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። በአውሮፕላን በሌሊት መሳሪያ እንደገባለት ሲነገር ጫጫታ የተፈጠረው ሀቁ በመታወቁ ነው። ትህነግ ለጦርነት እየተዘጋጀ እንደሆነ እየቀረበበት ያለው ክስን ማስተባበል የማይችልበት በመሆኑና እጅ ከፍንጅ የተያዘበት በመሆኑ ሌላ ማቅለያ የመሰለውን መረጃ ማስተላለፍ ፈልጓል። እጅ ከፍንጅ የተያዘበትን ጦርነት ከአማራ ጋር ነው የማደርገው ብሎ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለ ማቅማማት ገልፆታል። ለዚህም እጅ ከፍንጅ የተያዘበትን የጦርነት ዝግጅት ውንጀላ ያቀልልኛል ያለባቸው ምክንያቶች አሉት።

5) ትህነግ ጦርነቱን ከአማራ ጋር አደርገዋለሁ በሚል የማይረባ ሰበብ ይዞ የመጣበት ምክንያት አለው። አደራዳሪዎቹን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጦርነት ዝግጅቱን በመረጃ ስለደረሱበት የሰላም ስምምነቱ ተጥሶ ነው የጀመርኩት ማለት ይፈልጋል። ታጣቂውን እንዲያስፈታ ገንዘብ ቃል እየገቡ ላሉት ጨምሮ ለሌሎቹም ትጥቅ የማይፈታበትን ሰበብ ከአሁኑ አቅርቧል። ከፊቴ የጦርነት ድግስ አለኝ ብሎ የጦርነት እቅዱን አሳውቋቸዋል። ለኦሮሞ ብልፅግና፣ ለኤርትራና ለሌሎች ኃይሎች ደግሞ ከአማራ ጋር ነው ጠቤ ብሎ መነጠሉ ነው። ጦርነቱ የአማራ ብልፅግና ጋርም አይሆንም። ሸሽቶ አዲስ አበባ ያለውን ካድሬ ሳይሆን የራያና ዋግ፣ ወልቃይትና ጠለምት ንፁሃንን እንደሚወር ግልፅ ነው።

6) የትህነግ የጦርነት ሰበብ እጅ ከፍንጅ የተያዘበትን ከማስቀየር ውጭ ምክንያት ያለው አይደለም። አካባቢዎቹ አወዛጋቢ በተባሉበት ሁኔታ ራሱም በትምህርት ብቻ ሳይሆን በየቀኑ በተለያየ መንገድ በሀሰት "የትግራይ ናቸው" እያለ ቀጥሏል። ከአሁን ቀደም ራስ ዳሸንና ላሊበላን የትግራይ አካል አድርጎ በትግራይ መማሪያ መፅሐፎች ያሳተመው፣ በዚህ ወቅት የምንዋሰነው ከአገውና ቅማንት እንጅ አማራ የሚባል ህዝብ የለም እያለ በየመድረኩ ያለ ሀፍረት የሚሰብከው፣ አማራን የሚሳደብ ሙዚቃ አሁንም ስፖንሰር እያደረገ የሚያሳትመው፣ ጠላቴ አማራ ነው ከሚለው ማንፌስቶው በስራም በአስተሳሰብም አንድ ክንድ ያልራቀው እንዲያውም ከድሮው ማንፌስቶ በባሰ እየሰራበት ያለው ትህነግ ነው ሰበብ ፈጥሮ ጦርነት ያወጀው።

7) ጦርነቱ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል የነገረበት ምክንያትም አለ። አብይና ደጋፊዎቹ የጌታቸው ረዳን ቡድን ጦርነት የማይፈልግ አስመስለው እያቀረቡ ነው። ራሳቸው ተመልሰው ግን ጌታቸው ረዳን ከግብፅ ጋር እየተገናኘ እንደሆነ እያስነገሩ ነው። ከኤርትራ ጋር መገናኘቱ ይታወቃል። ትህነግም እጅ ከፍንጅ የያዘው በጋራ ዝግጅት መሆኑን የተናገረው በእነ ጌታቸው ረዳ በኩል ነው። ይህ የሆነው ለጠላትም ለወዳጅም ወደ ጦርነቱ በአንድነት እንደሚገቡ ማሳወቅ ስላለባቸው ያደረጉት ነው።

8/ ትህነግ በሰላም ስምምነቱ ሲያወናብድ ከርሟል። ትጥቅ ሳይፈታ "የሰላም ስምምነቱ ይከበር" ሲል ከርሟል። የደቡብ አፍሪካው ስምምነት ላይ አወዛጋቢ የተባሉት ወደ ትግራይ ይካለሉ ባላለበት "በስምምነቱ መሰረት ይመለሱልኝ" እያለ ሲያጭበረብር፣ በአማራ ክልል ካድሬ ጅልነት ያለ ስምምኑ ስምምነት ይከበር ሲል ከርሟል። በቅርብ ነገሮች አፍጥጠው መጡ። ተደራዳሪ የነበሩ "ግዛቶቹ በአማራ ክልል ይቆዩ ነው የተባሉ" ማለት ሲጀምሩ መልስ አጣ። አብይ ለራሱ ስጋት ሲባል ትጥቅ ለማስፈታት ሲፈልግ እነ ደብረፅዮን "የሰላም ስምምነቱ ከእኛ ፍላጎት ውጭ በጥቂት ሰዎች ስህተት የተፈረመ የማናውቀው ውል ነው" ብለው ካዱት። በቅርብ በተደረገው የአደራዳሪዎቹ ግምገማ እነ ደብረፅዮን ሌላ ስምምነት ብቻ ሳይሆን አዲስ አደራዳሪ እንደሚፈልጉ የትህነግ/ህወሓት ጉምቱ ባለስልጣን ልጅ እና የጌታቸው ረዳ ቡድን አክቲቪስት ፅፎት አጀንዳ ሆኖ ነበር። አሁን ትህነግ እያወናበደ የትም እንደማይደርስ ተረድቷል። ትጥቅ ፍታ ተብሎ ዶላር ተሰብስቧል። በትግራይ ብዙ ታማኝነቱን ያጣው ትህነግ ታጣቂዬን አጥቸ ማንም እንደፈለኩ ያደርገኛል ብሎ ሲያወናብድበት የከረመውን ስምምነቱ በጦርነት አዋጅ አፍርሸዋለሁ ብሎ በሰላም ስምምነቱ መሰረት በቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል በይፋ አሳውቋል። የጦርነቱ አዋጅ በሰላም ስምምነቱ መሰረት በተቋቋመው አካል የተነገረ ነው።

9) ምን አልባት ትህነግ ይህን የጦርነት አዋጁን እንደ ማመልከቻም የሚጠቀምበት እድል ይኖረዋል። የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት አላውቀውም ብሎ የጦርነት አዋጅ አውጇል። ጦርነቱን ጀምሮም ጦርነቱ ያሳሰበው ዓለም አቀፍ አካል ወይም የደቡብ አፍሪካው አደራዳሪዎች "ተው" ካሉት በአዲስ አደራዳሪ ሌላ ጊዜ መግዧ ስምምነት ሊጠይቅ ይችላል።

አንዳንዶች የትህነግ የጦርነት ቅስቀሳ አካል ሆነው የትህነግን የጦርነት አዋጅ ማስጠንቀቂያ አስመስለው እያለማመዱን ነው። አንድ ክልል በካቢኔ ደረጃ በሌላው ላይ መሰል ውሳኔ እንዲያስላልፍ መብት የለውም። እውነት ቢሆን ኖር ትህነግም ለአደራዳሪዎቹም ለፌደራሉ ብልፅግግናም ሊያቀርበው የሚትለውን አቤቱታ ነው የጦርነት ፊሽካ አካል ያደረገው።

ጦርነቱን ከአማራ ብልፅግና ጋር የሚያስመስሉም የጦርነት ዝግጅቱ አካላት ወይንም ራሳቸውን የሚያታልሉ ናቸው። አማራ ብልፅግና የአማራን ህዝብ የማንነትም ሆነ የግዛት አንድነት ቀርቶ ሌላ ቀለል ያለ ጥያቄ መፍታት የማይችል ኃይል ነው። የአማራ ብልፅግና ከትህነግ ጋር መሰል ውዝግብ ውስጥ የገባ የሚያስመስሉ አካላት ብልፅግና ለአማራ ህዝብ የቆመ አስመስለው ሊያሞኙን የማፈልጉ ናቸው። የትህነግ የጦርነቱ አዋጁ ግልፅና ህዝብ ላይ ነው!

የጦርነት አዋጁ ማስተባበል የማይቻለው የጦርነት ዝግጅትን፣ ቀጣዩን ጦርነት ማለማመጃ ተደርጎ አሳውቀን እንግባበት ተብሎ በሰላም ስምምነቱ በተመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሌሎች ጉዳዮች ሲጣስ የከረመው የሰላም ስምምነቱ በጦርነት አዋጅ የተጣሰበት ነው።
17.4K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-24 12:22:28
23.0K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-24 12:22:20 በቅርብ አመት ታዩታላችሁ!

ይህ ከአብይ አህመድ ጋር የሚተሻሸው ውሃብያ፣ ይህ ክርስትያኖችን በየቀኑ የሚያርደው ካዋርጃ በቅርብ አመት ወደ ምንነት እንደሚቀየር ታዩታላችሁ። በቱርክና በአረብ ኢሜሬትስ እየተደገፈ አሁን አደባባይ ላይ በስልት የመጣው ኃይል በቅርብ ምን አይነት ቅርፅ እንደሚይዝ ታዩታላችሁ።

በነገራችን ላይ ከ7 አመት በፊት በርካታ የአሸባሪው ISIS "ሴል" የተገኘው ኮልፌ ቀራኒዮ ነበር። አምነው የተከራከሩበት መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት አለ።

ዛሬ ሞስኮን ያስደነገጣት ሽብር ያኔ የትም ትሰሙታላችሁ።
22.4K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 15:16:03
20.8K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 15:15:47 አርሶ አደሩን እንደጨፈጨፉ እየነገሩን ነው!

አርሶ አደሩን ቤት ለቤት እየገቡ፣ ባገኙበት ቦታም ሁሉ ይገድላሉ። ቤቱን ፈትሸው ህጋዊ መሳሪያውን ቀምተው ይሰበስባሉ። የፋኖ አስመስለው ዜና ይሰሩበታል። ፋኖ መትረየስ፣ ስናይፐርና ዲሽቃ በታጠቀበት ሁኔታ ምንሽር፣ አብራራው፣ ጓንዴና አልቤን መሳሪያን ፋኖን ገድለን የማረክነው እያሉ በይፋ የፈፀሙትን ወንጀል ዜና ያደርጋሉ።

ፋኖ ሲያንስ ክላሽ ከፍ ሲል ዲሽቃና ሌላም ታጥቋል። ይህ የቃታ ብረት አርሶ አደሩን እየገደሉ ቤቱን ፈትሸው የሰበሰቡት ነው። እየነገሩን ያለው አርሶ አደሩን መጨፍጨፋቸውን ነው!
19.4K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 21:48:18
16.5K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 21:48:01 ጊዜያዊ አስተዳደሩ አረጋግጧል። ግን የታሰሩት 122 ብቻ አይደሉም!

ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ተይዘው ያልተለቀቁ ከአንድ ሺህ በላይ እስረኞች መቀሌ ጨለማ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ሲገለፅ ቆይቷል። አማራ ክልል ላይ "ጥቁር ክላሽ" እያለ ሰበብ የሚፈልገው መቀሌ ላይ ወታደሮቹ በቀን አንድ ዳቦ እየተጣለላቸው በሚሰቃዩበት ሁኔታ ነው።

በትህነግ/ህወሓት ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር 122ቱን ፈትቻለሁ ብሏል። እስር ላይ ያሉት ግን ከአንድ ሺህ በላይ ናቸው። አገዛዙ የሰላም ስምምነት ወዘተ ሲል በጀት የለቀቀለት በስሬ ያለ ነው የሚለው የእነ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር ግን በልመና የተወሰኑትን ብቻ ነው የፈታለት። አማራ ክልል ላይ ምንም ሳይፈጠር ሰበብ ሲፈልግ "አስገድጀ ወደ ድርድር አስመጥቸዋለሁ" የሚለው ትህነግ ግን እስካሁን በልመና ሁሉንም አልፈታለትም። ያውም አገዛዙ ትግራይ ውስጥ ኃይል አለኝ እያለ።

እስካሁን ስንለው የቅየነውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ወጥቶ አረጋግጧል። 122 ፈትቸለታለሁ ብሏል። ሌሎቹን በመደራደሪያነት ይዞለታል።
16.3K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-13 22:31:14

12.7K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ