Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-26 22:47:54 ጥብቅ ሚስጥር ነው!

ዳንኤል ብርሃነ ወደ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ነው ያደገው። ሌሎች የትህነግ ሰዎች ለመግለፅ የማይደፍሩትን ሚስጥር ዘረገፈው! የሰምኑ ወረራም የሌላው ችግር ምንጭ ይህ ዳንኤል የነገረን አካሄድ ነው!

1) ትህነግ ስምምነቱ በተለይም ትጥቅ ማስፈታቱን ጨምሮ ሌሎችን በጓዳ ውል እንዲዘገይ ያደረገው በእርዳታና ብድር መሆኑን በራሱ ተሞክሮ ይነግረናል። ዳንኤል የአውሮፓውን ዲፕሎማት በብድርና እርዳታ ጫና አድርገልን ያለው በራሱ ተነሳሽነት አይደለም። የዋናው ትህነግ መጫዎቻ ስለሆነ ነው። የኦሮሞ ብልፅግና ካለው ፀረ አማራ ፍላጎት ባሻገር፣ ትህነግ ትጥቅ መፍታቱንም ሌላውንም በጓዳ ውል ያስቆየው በዚህ መንገድ ነው። ዲፕሎማቶች በየቀኑ ወደ መቀሌ ሲመላለሱ ለዚህ እንደሆነ ብልፅግና ያውቃል። ፍላጎቱም ነው።

2) ዲፕሎማቶቹም ሌላ ጥያቄ ሲጠየቁ ያለምንም ማወላዳት "ትጥቅ አትፈቱም" የሚሉት የትህነግ የመጀመሪያ ፍላጎት እንደሆነ ስለሚያውቁ ነው። ብልፅግናም በጓዳ የተዋዋለው፣ የአማራን ርስቶች ለብድርና እርዳታ ቀብድ ያደረጋቸው መሆኑን ማሳያ ነው።

3) ሰሞኑን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የአማራን ርስቶች አሳልፎ የመስጠት የአብይ አህመድ እና የትህነግ የጓዳ ውል ተግባራዊ እንዲሆን የሚደረገው አብይ ብድርና እርዳታ ሲፈልግ፤ የሞቀ ድርድር ላይ ሲሆን ነው። የሰሞኑ የራያና የሌሎች አካባቢዎች ወረራ አብይ ከዓለም የገንዘብ አበዳሪዎች ጋር ሲደራደር የተፈፀመ ነው። ዳንኤል ያወጣው ሚስጥርም ከዚሁ ጋር የተገናኘ ነው።

4) እየተተገበረ ያለው የሰላም ስምምነት አይደለም። አብይ የአማራን ርስቶች በብድርና እርዳታ፤ በጓዳ ውል ከሰላም ስምምነቱ በተቃራኒ አሳልፎ ነው እየሰጠ ያለው።

ዳንኤል በግልፅ ተናገረው እንጅ የምናውቀው ነው። ዳንኤል ያወጣው ዲፕሎማቶቹ በትህነግ የሚነገራቸውንና እየሆነ ያለውን እውነታ ነው። ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ጥብቅ ሚስጥር ነው!
12.9K viewsedited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 20:23:40
15.6K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 11:00:39 በመስዋዕትነቱ ልክ ብስለት ያስፈልጋል!

ባለፈው አንድ አመት ገዥዎቹ አማራውን በሀሰት በክፉ ጎን ለማሳየትና ለመድፈቅ ያደረጉት ጥረት እንዳይሳካላቸው የተደረገውን ያህል በሂደቱ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሏል። አገዛዙ በጥላቻ በርካታ ሕዝብ ጨፍጭፏል። በርካቶች ተሰውተዋል። የምናውቃቸው የፋኖ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና ጓዶቻቸውን ገብረውበታል። ሕዝባችን በርካታ ውጣ ውረድ አይቷል። በአማራው ላይ የተፈፀመው ወረራና የአማራው ተቃውሞ በብልሃት ከተኼደበት ለሌሎች ተስፋ በርካታ ጊዜ ታይቷል። ይህ የሚሆነው ግን ትግሉ በዋጋው ልክ ስሌት የደረገበት ሲሆን ነው።

1) ትግሉ የህልውና እንደመሆኑ መረር ያለ ግምገማ ያስፈልገዋል። አፍኖ ቆይቶ ግለሰቦች ወይ ቡድኖች ላይ መዝመት አያዋጣም። የሚያዋጣው አጠቃላይ አካሄድን መገምገም ነው። ለአብነት ያህል ብልፅግና ህዝብ ላይ ከሚያደርሰው ጥቃት ባለፈ ፕሮፖጋንዳው ላይ በርትቷል። የሚጠላውን ሕዝብ እየሰበሰበ ነው። ከአማራ ክልል አልፎ ለይምሰልም ይሁን በተግባር በውጭ አገር ጭምር ስብሰባ እያደረገ ነው። እንዴት? ለምን? ተብሎ መጠየቅ አለበት። በፖለቲካ "ይታወቃልኮ"፣ "ምንም አያመጣም" ወዘተ የሚሉ ማቃለያዎች፣ ጥቅል ፍረጃዎች ትግልን ገዳይ ናቸው። ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ ብቻ ማሳበብም የእለት ማስተንፈሻ ነው። ትግል እንደ አጠቃላይ በየጊዜው ይገመገማል። ግምገማ የኢህአዴግም፣ የብልፅግናም አይደለም። የትግል ማከሚያ ስልት ነው!

2) መሬት ላይ ያሉትን አንድ ካልሆኑ እያለ የሚጨነቀው፣ የሚወቅሰው የማህበራዊም ሆነ የሌላው ሚዲያ አካል ራሱ ዕዝ ሊኖረው ይገባል። መሳሪያ ከያዙት፣ ውጊያ ላይ ከሚውሉት፣ ብዙ የመነጋገር እድል ከሌላቸው ይልቅ ሚዲያ ላይ ያለው የመነጋገር እድልም አቅምም አለው። ለየራሱ ሰበር ዜና፣ ለየራሱ አጀንዳ ያልተናበበ አካሄድን እየመረጠ፣ በግምትና ባልተሰላ መንገድ እየሄደ መሬት ላይ ያሉት አብረው ቢሰሩ እንኳን ትግሉን የሚያበላሸው የሚዲያ ትርምስ ነው።

3) ትግሉ የህልውና ነው ካልን፣ ስለ አራት ኪሎ ካሰብን የከበደ ነገር የሚገጥመን ጠላት ካልነው ኃይል ብቻ አይደለም። የመጀመሪያው ፈተና ለዛ አላማ ብቁ ለመሆን ራስን መግዛት ነው። በዛ አላማ ልክ ራስን ማስተካከል ነው። ባለፉት ወራት የተወሰኑ ምክሮችን ፅፌ ነበር። ትግል ላይ ያሉ አካላት አማራ ውስጥ ያሉትን ኃይሎች ለመያዝ ዋጋ መክፈል ካልቻሉ እንቅፋት የከበደ ይሆናል። ለአብነት ያህል የሀይማኖት አባቶች ጋር ያለው አንዱ ነው። ሚሊሻ ሌላኛው ችግር ሆኗል። እነዚህ አካላት ጋር ተቃርኖ በጨመረ ቁጥር ብልፅግና ቦታ ያገኛል። ጦርነት ነውና የግዳቸውን ወገን ይፈልጋሉ።

የሰፈርህን ሚሊሻ ሳታሳምን የብሔር ድርጅቶች ጋር ተስማምተህ አገር ልትመራ አትችልም። ሚሊሻ ጓዶቻችን ስለገደለ፣ ስለሚጠቁም ወዘተ በብስጭት ካየነው ሌላ ጉዳይ ነው። የሌላ ብሔር የመከላከያ አባላት መርሯቸው መሳሪያ ሸጠው እየጠፉ ሰው በሰው የምታውቀው፣ ሰፈሩ የሚደበደበው፣ ራሱም ደጋፊ ነህ ተብሎ ሲገረፍ የከረመው፣ ክብር የማይሰጡትን ሚሊሻ ጋር የሚኖረውን ነገር ቁጭ ብሎ ማጤን ያስፈልጋል። አራት ኪሎን የሚመለከት ሚሊሻ የሚባልን እንቅፋት ማለፍ ካልቻለ ለአገዛዙ ምቹ መሆኑ ነው። እርስ በእርስ እያታኮሰ፣ የማህበረሰብ ደም እያቃባ ጊዜ ይገዛል። ትግሉን አራት ኪሎ ድረስ ያደረገ ሌላ አዋጭ አማራጭ መፈለግ አለበት። ዝርዝር ግምገማ ያስፈልገዋል።

በገጠር ያስቸገረን ባላንጣ አንድ አድርጌው ቤቴም ይፈርሳታል ብሎ የሚወስን አለ። የግል ጠብ ሲሆን ነው። ይህኛው አላማ ግን ቤት የመስራት ነው። ስርዓት የመስራት ነው። ይህን ለማድረግ የተነሳ አካል አካሄዱን ማጤን አለበት። የአማራን ጥያቄ ለሚሊሻው አስረድተን፣ ጥያቄውን ካልተረዳም ከእኛ ጋር የሚሆንበትን መንገድ ካልቀየስን፣ ካልሆነም የከፋው ጠላቱ ሌላ መሆኑን ማሳየት ካልቻልን ትግሉ ትርምስ ውስጥ ይገባል። ሚሊሻው በርካታ ቁጥር ያለው ነው። ከፋኖ አባላት ጨምሮ ዘመዶች አሉት። ከአርሶ አደሩ በክፉም በበጎም ይቀርባል። እጅግ አደገኛው ደግሞ አንዳንዴ በሚሊሻውና መሳሪያ በያዘው አርሶ አደር መካከል ያለው ድንበርም ቀጭን መስመር ይሆናል። በዚህ በኩል አንዳንድ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እየታዩ ነው። ባለፈው ጦርነት ሚሊሻ ተብሎ የዘመተ አርሶ አደር፣ አገዛዙ መሳሪያውን እንዳይቀማው ስብሰባ የሚሄድም ሆነ ሌላው እና ዋናው ሚሊሻ ጋር ያለው ልዩነትንና ድንበር የሚጠፉበት ሁኔታ ይኖራል። ከዚህ ሁሉ አንፃር ከትግሉ ዋጋና አስፈላጊነት አንፃር መረር ያለች ግምገማ፣ ጥናት፣ ምክክር ያስፈልጋል። ከእርስ በእርስ ጭቅጭቅና መፈራረጅ ይልቅ የውስጥ ኃይል አሰላለፍ ላይ ሰከን ብሎ፣ ከብስጭት ወጥቶ ማሰብ ያስፈልጋል። ሕዝብ ሲወደውና ሲያደንቀው የነበረው ኢሕአፓ በተወሰኑ አባላቱ፣ ከዕዝ ባፈነገጠ መንገድ፣ በብስጭት እርምጃዎች፣ በመሰላቸት፣ ፍረጃ ወዘተ ሕዝብ ጋር ተቃርኖ መግባቱን መተለያዩ ሰነዶች አንብበናል። ከቆየውም ከአሁኑ ተጨባጭ ሁኔታም መማር ያስፈልጋል።

መስዋዕትነት ብቻ ድል አያመጣም፣ ጀግንነት ብቻውን አሸናፊ አይደለም፣ ብልጠት፣ ብስለት፣ ጊዜውን የዋጀ ግምገማ፣ የውስጥ ኃይልን ማሰባሰብ፣ ጠላትን መቀነስ ለድል ያበቃል። ጀብዱ ብቻውን አላማን አያሳካም። ከብስጭት ያለፈ አካሄድ ግድ ይላል። ትግሉ የተከፈለበትን ዋጋ ያህል ብልጥነትና ብልሃት፣ ጥንቃቄም ያስፈልገዋል።
14.8K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 19:07:55
13.8K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 19:07:47 ሕዝብ ደንበኛ አማራጭ አለው!

የትህነግ ወረራ ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃንን አፈናቅሏል። ይህ ሁሉ ንፁሃን የተፈናቀለው የትህነግ ታጣቂዎች "ጠላት" በሚል በስም ዝርዝር ጭምር ንፁሃንን ስላጠቁ፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ዘረፋ ስለፈፀሙና ስለገደሉ ጭምር ነው! ተፈናቃይ እንዲመለስ ወዘተ የሚለው የብልፅግና ኮሚቴ ወዘተ ስለእነዚህ ንፁሃን ግድ አይሰጠውም።

ነገር ግን ሕዝብ በዚህም በዛም እየተጠቃ አይኖርም። አሁን ደንበኛ አማራጭ አለው። ከመሳደድ በጣም በትንሹ ፋኖን ተቀላቅሎ ራሱን ያድናል። በጓዳ ውሎ የሚያስጠቃውንንም፣ አጥቂውንም ለመፋለም አማራጭ ለመፈለግ ይገደዳል። አማራጩ ደግሞ በተሻለ በሚያምነው መልኩ የተዘጋጀ ነው።
13.7K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 17:51:31 ትህነግ መቸም አይድንም!

ትጥቅ ያልፈታው ታጣቂው በጦርነቱ ወቅት አማራን በመስደብ ሲቀሰቅስበት የነበረውን ሰሞኑን እንደ አዲስ እየቀሰቀሰበት ነው። አማራን "አህያ" እያለ እየሰደበ "ሁመራን እንይዛለን" እያለ እየጨፈረ ያለው ትጥቅ ያልፈታው ጨካኝ ነው።

ራያ ላይ በርካቶችን ያፈናቀለው ይህ በጥላቻ የተነከረ ኃይል ነው። ወደ ጠለምትና ወልቃይት እንዲገባ የሚፈለገው ይህ በአማራ ጥላቻ የጦዘ ትህነግ ነው!

ሰሞኑን በየማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ጭምር እንደ አዲስ እየቀሰቀሱበት ነው። ወልቃይትና ጠለምት ማዶ ሆነው የሚጨፍሩበት ይህን ፀረ አማራ ጥላቻ ነው። ይህ ኃይል እድል ቢያገኝ ከማይካድራና ጭና የባሰ ጭፍጨፋ እንደሚፈፅም ጥርጥር የለውም!
15.4K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 21:50:53
13.5K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 21:50:40
13.2K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 21:50:24 የኦሮሚያው ኢንተርሃሙዬ!

የዚህ ኃይል ተልዕኮ ይህ ነው! ኦሮሚያ ውስጥ አማራውን ማሳደድ፣ ሀብቱን ማውደምና መዝረፍ ነው። የኦሮሚያው ገዳይ ቡድን ሰራዊት ነው። የኦሮሚያው ኢንተርሃሙዬ ነው!
13.5K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 13:13:21 የአዲስ አበባ ወጣትን የሚያሳስረው ሳይገረፍ ለፈለፈ!

የባልደራስ አባላትንና ሌሎች የአዲስ አበባ ወጣቶችን የሚያሳስረው ጆሮ ጠቢ "አቤት! እኔው ነኝ" ብሏል!

አዋሽ አርባ ኤየተሰቃዩ የሚገኙት የአዲስ አበባ ልጆች፣ ኦሮሚያ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች የሚሰቃዩት የባልደራስና ሌሎች አደረጃጀት የተሳተፉ በሙሉ ስምና አድራሻቸው ለአሳሪዎች ተላልፎ ተሰጥቶ ነው ለስቃይ የተዳረጉት። አሳሳሪው ደግሞ የወጣቶችን ስምና አድራሻ አሳልፎ ከመስጠት አልፎ "ሽብር፣ ሁከት የምትፈጥሩ እረፉ" እያለ በይፋ እያስፈራራ ቪዲዮ እየሰራ ነው።
14.7K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ