Get Mystery Box with random crypto!

ሕዝብ ደንበኛ አማራጭ አለው! የትህነግ ወረራ ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃንን አፈናቅሏል። ይህ ሁሉ ን | Getachew shiferaw

ሕዝብ ደንበኛ አማራጭ አለው!

የትህነግ ወረራ ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃንን አፈናቅሏል። ይህ ሁሉ ንፁሃን የተፈናቀለው የትህነግ ታጣቂዎች "ጠላት" በሚል በስም ዝርዝር ጭምር ንፁሃንን ስላጠቁ፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ዘረፋ ስለፈፀሙና ስለገደሉ ጭምር ነው! ተፈናቃይ እንዲመለስ ወዘተ የሚለው የብልፅግና ኮሚቴ ወዘተ ስለእነዚህ ንፁሃን ግድ አይሰጠውም።

ነገር ግን ሕዝብ በዚህም በዛም እየተጠቃ አይኖርም። አሁን ደንበኛ አማራጭ አለው። ከመሳደድ በጣም በትንሹ ፋኖን ተቀላቅሎ ራሱን ያድናል። በጓዳ ውሎ የሚያስጠቃውንንም፣ አጥቂውንም ለመፋለም አማራጭ ለመፈለግ ይገደዳል። አማራጩ ደግሞ በተሻለ በሚያምነው መልኩ የተዘጋጀ ነው።