Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-07 14:06:14
13.1K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 14:05:56 የጠለምት አማራ አደባባይ ወጥቶ የሰሞኑን አስተዳደር ማፍረስና ህዝብ ለዳግም የትህነግ ባርነት አሳልፎ መስጠት ሴራ "አንቀበለውም" ብሏል። "አማራ ነን አልን እንጅ አማራ እንሁን ብለን አልጠየቅንም" ሲሉ ሰልፈኞቹ ተቃውሞ አሰምተዋል።
12.8K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 16:43:46
17.7K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 16:43:36 የታሰበው ይህ ነው!

የብልፅግና የሴራ ውሳኔ በአደባባይ የተገለጠበት የትህነግ መግለጫ!

ብልፅግና ያለ ምንም በጀት ከህዝብ ገንዘብ ሰብስቦ ልማት ሲሰራ የከረመውን የወልቃይት አስተዳደር ለማፍረስ ከወሰነ ሰንብቷል። ትህነግ/ህወሓት ደግሞ "ከብልፅግና ጋር በተስማማሁት መሰረት" ብሎ ለወልቃይትና ጠለምት አመራር አዋቅሮ እነዛን ወደር የለሽ ጨፍጫፊዎች ሊመለሱ ዝግጅት ላይ ናቸው ብሏል። የወልቃይት አማራ ከቀየው እንዲወጣ በይፋ በመግለጫው የዘር ፍጅት ማስጠነቀቂያ ጨምረውበታል።

ትህነግ ዛሬ በፌስቡክ ገፁ ባጋራው፣ ሚዲያዎቹ በዘገቡት ከብልፅግና ጋር ተስማምቸበታለሁ ብሎ ያዋቀረው የወልቃይትና ጠለምት አመራር ነኝ ባይ መግለጫ እስከ ቀበሌ ድረስ አደረጃጀቶችን አዋቅሬያለሁ ብሏል። ብልፅግና አስተዳደሩን አፍርሸ በገለልተኛ ወዘተ እያለ ቢቀልድም አላማው ትህነግ አመራር አዋቅሮ እንዲረከበው ማድረግ ነው። ከሌላ የተሰማ አይደለም። ትህነግ በይፋ ገልፆታል። የወልቃይትና ጠለምት ጉዳይ ላይ የተደረገው ለራያና አበርገሌም ተመሳሳይ ነው።

ብልፅግና በጓዳ ስምምነቱ መሰረት የአማራ ግዛቶችን ለትህነግ/ህወሓት አሳልፎ ለመስጠት በወሰነው መሰረት ትህነግ በይፋ ለግዛቶቹ እስከ ቀበሌ አመራር አደራጅቶ እየጠበቀ መሆኑን በመግለጫው አሳውቋል። በስብሰባዎቹም ብልፅግና ጋር በተስማሙት መሰረት የተደረገ እንደሆነ መግለፃቸው ታውቋል። የተፈለገው ይህ ነው።

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የትህነግ ታጣቂ ትጥቅ መፍታት ቢሆንም ያ ጨፍጫፊ ታጣቂም ትህነግ ለአማራ ግዛቶች አዋቅሬዋለሁ ያለው አስተዳደር አካል ሆኖ ለመግደል እንደሚላክ ተገልፆአል። በቅርብ ብልፅግና ቀስ በቀስ ህዝብን ለማለማመድ በአክቲቪስቶቹ ባሰራጨው ውሳኔ የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚመለሱ ገልፆአል። አላማውም ትህነግ ያዋቀረውን አመራር ተከትለው ጨፍጫፊዎቹ ከእነ ትጥቃቸው ስለሚገቡ ነው። ብልፅግና ሰሞኑን በውሳኔ ስም ውስጥ ለውስጥ ያሰራጨው አላማም ለዚህ የትህነግ ገዳይ ቡድን መደላድል መፍጠር ነው። በአደባባይ ትህነግ የገለፀው፣ በመግለጫ ያወጀው እውነት ነው!

ብልፅግና በጓዳ የተዋዋለውን ትህነግ ትግርኛ የሚችል የሌለ ያህል እየተሰማው በአደባባይ ያጋልጠዋል። ይህ መድረክም የብልፅግና የሴራ ውሳኔ በአደባባይ የተጋለጠበት ነው።
16.2K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 20:24:22
14.3K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 20:24:03 በኮረም፣ ዛታ፣ ወፍላ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ትህነግ የሚፈፅመው ትንኮሳ እንዲቆም፣ የሕዝብ ምርጫ እንዲከበር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል። ለዳግም ባርነት ተላልፈን አንሰጥም ብሏል። በአላማጣና ሌሎች አካባቢዎችም በተመሳሳይ በርካታ ሕዝብ የተገኘባቸው ሰልፎች ሲደረጉ ሰንብተዋል።
14.3K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 14:41:08
16.0K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 14:40:56 በብልፅግና ይሁንታ የተፈፀመ ወ*ረ*ራ ነው!

ትህነግ የራያ ቀበሌዎችን በወ*ረ*ራ ይዟል። ንፁሃን ተገድለዋል። ለዚህ ወ*ረ*ራ የብልፅግና ይሁንታ አለበት።

1) ትጥቅ ፈትቷል ብለው ሲዋሹበት የከረሙት ኃይል ነው ጥቃት የፈፀመው። ንፁሃንን እየገደለ ያለው የትህነግና ብልፅግና የጓዳ ውል መሰረት ትጥቅ እንዳይፈታ የተደረገ ኃይል ነው።

2) የራያ አላማጣ አመራሮች በግልፅ እንደተናገሩት ትህነግ በራያ ቀበሌዎች ወረራ ሲፈፅም መከላከያ ቢያውቅም ዝምታን መርጧል። ግዴታውን ያልተወጣው ወ*ረ*ራው የብልፅግና ይሁንታ ያለበት በመሆኑ ነው። ከወራት በፊት ከሌሊቱ 5 ሰዓት መሰል ሙከራ ተደርጎ ሳይሳካ ሲቀር የብልፅግና ይሁንታ እንደነበረበት በመረጃ ተረጋግጧል።

3) በዋነኛነት የወ.ረ.ራ ቅስቀሳው እየተደረገ የሚገኘው መከላከያ ሚኒስትር አብርሃ በላይ በጀት በመደበለት ሚዲያ ነው። ግዕዝ ሚዲያ የተሰኘው የሚደገፈው በመከላከያ ሚኒስትሩ ነው። ከአብርሃም በላይ ጋር ፎቶው የሚታየው ግለሰብ ነው የሚፅፍበት። የግል አክቲቪስቱ ነው። አብርሃ በላይ በኢቲቪ ትግርኛ ፕሮግራም እየመጣ ከሚናገረው የቀረውን በዚህ ገፅ ነው የሚያስተላልፈው። ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የጦርነት አዋጅ ባልተለየ አብርሃ በላይ የጦርነት ቅስቀሳ ላይ ነው። አብርሃ የአብይ የቅርብ ጓደኛ ነው። ብልፅግና ነው። ይህ የሚሆነው በአብይ አህመድ ይሁንታ ነው።

4) አብይ አህመድ ይህን የሚያደርገው ከእነ ደብረፅዮን ቡድን ጋር የስልጣን ሽኩቻ ያለበት ጌታቸው ረዳ የሚመራው ኃይል ራያና ወልቃይትን ይዞ ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ይህ ካልተቻለ ትግራይና አማራ ተጋጩ ተብሎ "አንተም ተው አንተም ተው" በሚመስል አስታራቂነት አካባቢው መጀመሪያ በፌደራል፣ ቀጥሎ የትህነግ ሰዎች ያሉበት አስተዳደር እንዲዋቀር ነው። አብይ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን እንዲይዝ ይፈልግ እንጅ ትህነግ ላይ በጉዳዩ የደብረፅዮንና የጌታቸው የሚባል የለም። በጉዳዩ ትህነግ ልዩነት የለውም።

5) ትህነግ ትጥቅ እንዲፈታ በተወሰነበት ኃይል ወ*ረ*ራ እየፈፀመ፣ ብልፅግና ወስኖ ተፈናቃዮች ተመልሰው ነገሮ ግን ጌታቸው ረዳ "አማራ ካልወጣ ተፈናቃይ አይመለስም" እያለም ብልፅግና ጉዳዩን በመቃወም የይምሰል መግለጫ አልሰጠም። አማራ ላይ ሲሆን በሀሰት አጀንዳ የሚዘምቱት እነ ለገሰ ቱሉና ባልደረቦቻቸው ምንም ያላሉት ወረ*ራው ስለተፈለገ ነው።

6) አብይ አህመድ ለህዝበ ውሳኔ በሚል አካባቢዎችን በይሁንታ ቢያስወርርም ትህነግ ደግሞ መሃል አገሩ ተተራምሷል ብሎ ጊዜው አገር ለመመስረት ምቹ ነው ብሎ እየሰራ ነው። ከኤርትራና አማራ ጋር ድርድር በሞከረበት ሁኔታ አሁን ኤርትራና የአማራ ይውጡልኝ የሚለው ምቹ ነው። ባለው ጊዜ ለአገር ምስረታ ሩጫ ነው። ትህነግ የብልፅግናን የህዝበ ውሳኔ ቂልነት መጠቀሚያ አድርጎ ስለ አገር ምስረታ እየተጣደፈ ነው።
15.4K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 16:05:39
13.9K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 16:05:26
13.7K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ