Get Mystery Box with random crypto!

የታሰበው ይህ ነው! የብልፅግና የሴራ ውሳኔ በአደባባይ የተገለጠበት የትህነግ መግለጫ! ብልፅግና | Getachew shiferaw

የታሰበው ይህ ነው!

የብልፅግና የሴራ ውሳኔ በአደባባይ የተገለጠበት የትህነግ መግለጫ!

ብልፅግና ያለ ምንም በጀት ከህዝብ ገንዘብ ሰብስቦ ልማት ሲሰራ የከረመውን የወልቃይት አስተዳደር ለማፍረስ ከወሰነ ሰንብቷል። ትህነግ/ህወሓት ደግሞ "ከብልፅግና ጋር በተስማማሁት መሰረት" ብሎ ለወልቃይትና ጠለምት አመራር አዋቅሮ እነዛን ወደር የለሽ ጨፍጫፊዎች ሊመለሱ ዝግጅት ላይ ናቸው ብሏል። የወልቃይት አማራ ከቀየው እንዲወጣ በይፋ በመግለጫው የዘር ፍጅት ማስጠነቀቂያ ጨምረውበታል።

ትህነግ ዛሬ በፌስቡክ ገፁ ባጋራው፣ ሚዲያዎቹ በዘገቡት ከብልፅግና ጋር ተስማምቸበታለሁ ብሎ ያዋቀረው የወልቃይትና ጠለምት አመራር ነኝ ባይ መግለጫ እስከ ቀበሌ ድረስ አደረጃጀቶችን አዋቅሬያለሁ ብሏል። ብልፅግና አስተዳደሩን አፍርሸ በገለልተኛ ወዘተ እያለ ቢቀልድም አላማው ትህነግ አመራር አዋቅሮ እንዲረከበው ማድረግ ነው። ከሌላ የተሰማ አይደለም። ትህነግ በይፋ ገልፆታል። የወልቃይትና ጠለምት ጉዳይ ላይ የተደረገው ለራያና አበርገሌም ተመሳሳይ ነው።

ብልፅግና በጓዳ ስምምነቱ መሰረት የአማራ ግዛቶችን ለትህነግ/ህወሓት አሳልፎ ለመስጠት በወሰነው መሰረት ትህነግ በይፋ ለግዛቶቹ እስከ ቀበሌ አመራር አደራጅቶ እየጠበቀ መሆኑን በመግለጫው አሳውቋል። በስብሰባዎቹም ብልፅግና ጋር በተስማሙት መሰረት የተደረገ እንደሆነ መግለፃቸው ታውቋል። የተፈለገው ይህ ነው።

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የትህነግ ታጣቂ ትጥቅ መፍታት ቢሆንም ያ ጨፍጫፊ ታጣቂም ትህነግ ለአማራ ግዛቶች አዋቅሬዋለሁ ያለው አስተዳደር አካል ሆኖ ለመግደል እንደሚላክ ተገልፆአል። በቅርብ ብልፅግና ቀስ በቀስ ህዝብን ለማለማመድ በአክቲቪስቶቹ ባሰራጨው ውሳኔ የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚመለሱ ገልፆአል። አላማውም ትህነግ ያዋቀረውን አመራር ተከትለው ጨፍጫፊዎቹ ከእነ ትጥቃቸው ስለሚገቡ ነው። ብልፅግና ሰሞኑን በውሳኔ ስም ውስጥ ለውስጥ ያሰራጨው አላማም ለዚህ የትህነግ ገዳይ ቡድን መደላድል መፍጠር ነው። በአደባባይ ትህነግ የገለፀው፣ በመግለጫ ያወጀው እውነት ነው!

ብልፅግና በጓዳ የተዋዋለውን ትህነግ ትግርኛ የሚችል የሌለ ያህል እየተሰማው በአደባባይ ያጋልጠዋል። ይህ መድረክም የብልፅግና የሴራ ውሳኔ በአደባባይ የተጋለጠበት ነው።