Get Mystery Box with random crypto!

በብልፅግና ይሁንታ የተፈፀመ ወ*ረ*ራ ነው! ትህነግ የራያ ቀበሌዎችን በወ*ረ*ራ ይዟል። ንፁሃን | Getachew shiferaw

በብልፅግና ይሁንታ የተፈፀመ ወ*ረ*ራ ነው!

ትህነግ የራያ ቀበሌዎችን በወ*ረ*ራ ይዟል። ንፁሃን ተገድለዋል። ለዚህ ወ*ረ*ራ የብልፅግና ይሁንታ አለበት።

1) ትጥቅ ፈትቷል ብለው ሲዋሹበት የከረሙት ኃይል ነው ጥቃት የፈፀመው። ንፁሃንን እየገደለ ያለው የትህነግና ብልፅግና የጓዳ ውል መሰረት ትጥቅ እንዳይፈታ የተደረገ ኃይል ነው።

2) የራያ አላማጣ አመራሮች በግልፅ እንደተናገሩት ትህነግ በራያ ቀበሌዎች ወረራ ሲፈፅም መከላከያ ቢያውቅም ዝምታን መርጧል። ግዴታውን ያልተወጣው ወ*ረ*ራው የብልፅግና ይሁንታ ያለበት በመሆኑ ነው። ከወራት በፊት ከሌሊቱ 5 ሰዓት መሰል ሙከራ ተደርጎ ሳይሳካ ሲቀር የብልፅግና ይሁንታ እንደነበረበት በመረጃ ተረጋግጧል።

3) በዋነኛነት የወ.ረ.ራ ቅስቀሳው እየተደረገ የሚገኘው መከላከያ ሚኒስትር አብርሃ በላይ በጀት በመደበለት ሚዲያ ነው። ግዕዝ ሚዲያ የተሰኘው የሚደገፈው በመከላከያ ሚኒስትሩ ነው። ከአብርሃም በላይ ጋር ፎቶው የሚታየው ግለሰብ ነው የሚፅፍበት። የግል አክቲቪስቱ ነው። አብርሃ በላይ በኢቲቪ ትግርኛ ፕሮግራም እየመጣ ከሚናገረው የቀረውን በዚህ ገፅ ነው የሚያስተላልፈው። ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የጦርነት አዋጅ ባልተለየ አብርሃ በላይ የጦርነት ቅስቀሳ ላይ ነው። አብርሃ የአብይ የቅርብ ጓደኛ ነው። ብልፅግና ነው። ይህ የሚሆነው በአብይ አህመድ ይሁንታ ነው።

4) አብይ አህመድ ይህን የሚያደርገው ከእነ ደብረፅዮን ቡድን ጋር የስልጣን ሽኩቻ ያለበት ጌታቸው ረዳ የሚመራው ኃይል ራያና ወልቃይትን ይዞ ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ይህ ካልተቻለ ትግራይና አማራ ተጋጩ ተብሎ "አንተም ተው አንተም ተው" በሚመስል አስታራቂነት አካባቢው መጀመሪያ በፌደራል፣ ቀጥሎ የትህነግ ሰዎች ያሉበት አስተዳደር እንዲዋቀር ነው። አብይ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን እንዲይዝ ይፈልግ እንጅ ትህነግ ላይ በጉዳዩ የደብረፅዮንና የጌታቸው የሚባል የለም። በጉዳዩ ትህነግ ልዩነት የለውም።

5) ትህነግ ትጥቅ እንዲፈታ በተወሰነበት ኃይል ወ*ረ*ራ እየፈፀመ፣ ብልፅግና ወስኖ ተፈናቃዮች ተመልሰው ነገሮ ግን ጌታቸው ረዳ "አማራ ካልወጣ ተፈናቃይ አይመለስም" እያለም ብልፅግና ጉዳዩን በመቃወም የይምሰል መግለጫ አልሰጠም። አማራ ላይ ሲሆን በሀሰት አጀንዳ የሚዘምቱት እነ ለገሰ ቱሉና ባልደረቦቻቸው ምንም ያላሉት ወረ*ራው ስለተፈለገ ነው።

6) አብይ አህመድ ለህዝበ ውሳኔ በሚል አካባቢዎችን በይሁንታ ቢያስወርርም ትህነግ ደግሞ መሃል አገሩ ተተራምሷል ብሎ ጊዜው አገር ለመመስረት ምቹ ነው ብሎ እየሰራ ነው። ከኤርትራና አማራ ጋር ድርድር በሞከረበት ሁኔታ አሁን ኤርትራና የአማራ ይውጡልኝ የሚለው ምቹ ነው። ባለው ጊዜ ለአገር ምስረታ ሩጫ ነው። ትህነግ የብልፅግናን የህዝበ ውሳኔ ቂልነት መጠቀሚያ አድርጎ ስለ አገር ምስረታ እየተጣደፈ ነው።