Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-15 20:38:07 ራያ በአብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ ቀጥታ ትዕዛዝ ተወርሯል!

ትህነግ/ህወሓት በአብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ ቀጥታ እገዛ ራያን ወርሯል። በጓዳ ስምምነት መሰረት ንፁሃን ላይ ከባደ መሳሪያ ጭምር እየተኮሱ ነው!

1) ወረራ ፈፃሚው በሰላም ስምምነቱ ትጥቅ ይፍታ የተባለ አሁን ብልፅግና በጀት የሚከፍለው የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያዘው ኃይል ነው።

2) ሰሞኑን ያለ ታጣቂ ተፈናቃይ ይመጣል፣ የፌደራል መንግስቱ ይቆጣጠረዋል ተብሎ መግለጫ ተሰጥቶ ትህነግ በወረራ እንዲይዘው ተደርጓል

3) የጋራ ኮሚቴ ተብሎ የተቋቋመው በቀደም ተገናኝቷል። በጓዳ ስምምነቱ መሰረት ወርራችሁ ያዙ ተብለዋል።

4) የሰላም ስምምነቱ የአማራ ግዛቶች በአማራ ክልል ስር እንዲቆዩ በግልፅ ደንግጓል።

5) አብይ የባህርዳር ሎሌዎቹ አልነበርንም እንዲሉ ወደ አሜሪካ እንዲሄዱ አድርጎ ነው ያስወረረው።
14.9K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 15:29:42
16.6K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 15:29:37 ብልፅግና በይፋ ከኢራን ጎን ተሰልፌያለሁ እያለ ነው!

ይህ ዘገባ ሆን ተብሎ የተሰራ ነው። ከቱርክ ቀጥሎ ከኢራን ድሮን የሚያገኘው ብልፅግና ውለታውን በፕሮፖጋንዳ እየተወጣ ነው። በዚህ ፍጥነት ከኢራን ጋር መቆሙን የገለፀበት ገራሚ የፕሮፖጋንዳ ዘገባ ነው!

1) እስካሁን በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከሚገልፁት ውጭ በቁጥር ሁሉ አስቀሞጦ፣ የእስራኤል ስትራቴጅክ ቦታዎች ተጠቁ ብሎ በግልፅ በርዕስ ያስቀምጣል።

2) ይህን የፕሮፖጋንዳ ዘገባውን ታማኒ ለማስመሰል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደዘገቡት አድርጎ ያቀርባል። ዝርዝር ላይ ግን በማስረጃነት የሚያቀርበው የኢራንን የፕሮፖጋንዳ ቻናል ነው።

3) ጦርነቱ የሁለቱ አገራት ሆኖ ርዕስ ያደረገው የኢራን ቻናል ላይ የወሰደውን ሆኖ በውስጥ ዘገባው የእስራኤልን ባለስልጣን ቃል በትንሹ አካትቷል። የዘገባው አንጓ ግን ኢራን ስኬታማ ጥቃት እንዳደረገች ማሳየት ነው። ብዙ ጊዜ መሰል ዜናዎች ሲሰሩ የሁለቱም በርዕስነት የሚካተቱበት መንገድ ይገለፃል።

4) ኢቲቪ በትዕዛዝ የዘገበው ባይሆን በዚህ ደረጃ ፕሮፖጋንዳ አይሆንም ነበር። አሊያም ዜናውን ኢራን ይህን ያህል ኢላማ መታሁ አለች ብሎ በዘገብ ይችል ነበር። ይህም ፕሮፖጋንዳን ማስተጋባት ቢሆንም አሁን ከሰራው ይሻለው ነበር።

5) ኢቲቪ በዚህ መንገድ እየዘገበ ያለው የእስራኤል መንግስት በይፋዊ መግለጫ ጥቃቱን መቀልበሱን በገለፀበት፣ የአንድ የኢራን ጣቢያን እንደ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች አድርጎ በርዕስ አጉልቶ፣ ቀባብቶ ነው።

ይህ ዓለምን ያሰጋ ጦርነት ነው። ለብልፅግና ደግሞ ትርፍ አለው። ድሮን ያገኝበታል። ለዛም ነው በዚህ ደረጃ የዓለም አቀፍ ጦርነት ላይ ወገንተኝነትን የሚያሳየው።

ኢቲቪ የሚሰራው በብልፅግና ቀጥተኛ ትዕዛዝ ነው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ እያንዳንዱ ዘገባ የፖለቲካ ቃና ተሰጥቶት፣ ከብልፅግና ኃይል ተዋቅሮ እያረመ የሚወጣ ነው። የአገር ውስጡ አልበቃ ሲል ከአለም ጦርነትም አተርፋለሁ ብሎ የሚሰራው ፕሮፖጋንዳ ነው።
16.2K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 23:52:51
18.2K views20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 23:51:30 ማጭበርበሪያ!

ደብረፅዮን የሚመራው ትህነግ/ህወሓት የወልቃይት፣ ራያ፣ ጠለምትና አበርገሌ ወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮችን መልምሎ ትግራይ ውስጥ ፅ/ቤት ከፍቶላቸዋል። ከስር እንደሚታየው በአማራ ግዛቶች ስም የፌስቡክ ገፅ ከፍተው የሚያስተዳድራቸው ትህነግ/ህወሓት እንደሆነ አድርገው፣ ሽሬና መቀሌ የወረዳና የቀበሌ እንዲሁም ከተማ አደረጃጀቶች እንደሆኑ አድርጎ ባነር አሳትሞ እየሰበሰበ፣ በአካባቢዎቹ ስም ህገወጥ ማህተም ቀርፆ ደብዳቤ እየፃፈ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ደግሞ "ተፈናቃዮች ይመለሱ" ይላል።

ሰሞኑን በነበረው ስብሰባ ሞንጆሪኖና የትህነግ ጀኔራሎች ትህነግ/ህወሓት ያለምንም ልዩነት የተስማማበትን እስከነ መዋቅሩ መመለስ አቋም እንዲያራምዱ ተደርጎ፣ እነ ደብረፅዮን ከዚህ ሀሳብ የሚለዩ መስለው ቀርበዋል። ጌታቸው ረዳም ሆነ ደብረፅዮን በዚህ ጉዳይ ከጀኔራሎቹ ጋር ልዩነት የላቸውም። የቤት ስራ ነው የተከፋፈሉት። በውይይት የተወሰኑት እንዲሳተፉ ቀሪው የተለየ አቋም የያዘ መስሎ በተግባር እንዲሰራ ነው። በዚህ ማጭበርበሪያ መሰረት ከብልፅግና ጋር እየተሰበሰቡ ነው። ብልፅግና የአማራን ርስቶች በዚህ ሂደት አሳልፎ ለመስጠት እየሰራ ነው።
16.5K views20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 12:52:28 "ፎርማት" ተደርጎ ተከራዬ!

እኔ አይደለሁም ያልኩት። አለቃው ነው። እንደ አመታዊ የፋይናንስ ሪፖርት ቁጠሩት። ኤርሚያስ ለገሰ መከራየቱን አለቃው ቴድሮስ ፀጋዬ በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል። እነ ቴድሮስም ከሌላ ቀምተው ነበር የተከራዩት። አሁን ባለጊዜ ጨምሮ ወሰደው።

ትህነግ ኤርሚያስን በቴድሮስ በኩል ነበር የሚያዘው። አሁን አለቃው በብስጭት "ፎርማት ተደርጎ ተከራይቷል" ብሏል። ያው እነ ቴድሮስ (አንዱ የትህነግ ክንፍ) ኪራዩን መክፈል ስላልቻሉ ሌላ ተከራየው። የፖለቲካ ገበያው ሲሞቅ ዋጋ አስወደደ።

በእርግጥ ቴድሮስ ይህን ያለው በድሮው ዕዝ ስለማይሰራለት እንጅ ኤርሚያስ በሌሎች ቡድኖች በኩል ለትህነግ እየሰራ ነው። ደሞዝ ጨምሩኝ ብሎ ካልሆነ ከዛ ሰፈር ያለው የረዥም ጊዜ ውል ነው። ግን ፖለቲካው ተለዋዋጭ ስለሆኑ ሁለት ቦታ ተቀጥሯል። ፖለቲካው ሲገለባበጥም ቋሚ ገቢ ይኖረዋል። እየተገለባበጠ መስራት ነው።

ከወራት በፊት እንደፃፍኩት ኤርሚያስ ሬድዮ ነው። ባትሪ ያለው እስከመጨረሻው ከፍቶ ያስጮኸዋል። እስካሁን ይህን ራዲዮ ከፋች የነበረው ቴድሮስ አሁን በሌላ ሰው እጅ ነው ብሏል። የማስታወቂያ ከሰጡት በመሃል በመሃል ይዘፍንላቸዋል። የተሻለ የሚከፍለው ከሆነ ልዩ ዞንም፣ ልዩ ወረዳም የፈለገ ይከራየዋል። የሀሰተኛ ፖስተሮችም ቢሆን ካገኙት ማሪያምን እየሰደበ ፕሮግራም ከመስራት ወደኋላ አይልም።

ኤርሚያስ በቀጥታ ስርጭት ተሸጠ ተለወጠ ሲባል ደፍሮ የድሮ አለቃውን አይናገርም። ምክንያቱም በርካታ መረጃ ተይዞበታል።
20.4K viewsedited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 11:51:56
16.8K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 11:51:45 የተፈለገው ይሄ ነው!

ትህነግ ወደራያና ወልቃይት ተፈናቃይን አልመልስም ብሏል። ከእነ ሙሉ መዋቅሬ ነው የምመለሰው ብሎ እየሰራ ነው። ብልፅግና ሰሞኑን ያለ በጀት ከህዝብ ገንዘብ ሰብስበው ልማት የሚሰሩትን አስተዳደሮች አፈርሳለሁ ያለ ሲሆን ትህነግ እስከ ቀበሌ ድረስ አመራር፣ የፓርቲ መዋቅር፣ ፀጥታ አደራጅቶ እየጠበቀ ነው። ትግራይ ውስጥ ቁጭ ብለው የራያና ወልቃይት እስከ ቀበሌ ድረስ መዋቅር ተብለው ተዘጋጅተው መግለጫ እየሰጡ፣ መታወቂያ እያደሉ፣ በማህተም ደብዳቤ እየፃፉ ይገኛሉ። ብልፅግና ይህን ያውቃል።

የተፈለገው የህዝብ አስተዳደርን አፍርሶ ለትህነግ ማስረከብ ነው። የመጀመሪያው ትህነግ የሁመራ ፅ/ቤት ብሎ ያደራጀው መዋቅር የሚጠቀምበት ገፅ ማስረጃ ሲሆን ሁለተኛው የአላማጣ ከንቲባ ብሎ ማህተም አስቀርፆ ደብዳቤ የሚፅፍበት ነው። ሁሉም ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች፣ ከተሞች መሰል መዋቅር አዘጋጅቶ ህጋዊ አስመስሎ እየሰራው ነው።

"ተፈናቃይ ይመለስ" ማለቱን ተከትሎ ደግሞ "ኬር ኢትዮጵያ" በሚባል ድርጅት ድጋፍ በርካታ መታወቂያ ተዘጋጅቷል። ራያና ወልቃይትን የማያውቀውን ጨምሮ በርካታ ህዝብ መታወቂያ ተሰጥቶት እናሰፍራለን እያሉ ነው።

አንድም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ግዴታውን ሳይወጣ፣ በስምምነቱ መሰረት በአማራ ክልል እንዲቆዩ የተደነገገላቸውን አካባቢዎች አሳልፎ ለመስጠት በተሰራው ደባ የልብ ልብ የተሰማው ትህነግ ለአካባቢዎቹ በህገወጥ ማህተምና ደረሰኝ የሚጠቀም ሙሉ መዋቅር አዘጋጅቷል። ብልፅግና ይህን ያውቃል። ወንጀል ግን አይመስለውም። የህዝብ አስተዳደር የሚያፈርሱት ግን ለዚህ ህገወጥ ቡድን አሳልፎ ለመስጠት ነው!
19.7K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 18:06:16 ከአንተ ኢሳያስ አፈወርቂን ይቅር ቢሉት ይቀላቸዋል!

ኤርሚያስ ለገሰ ትህነግ "ይቅር" ይለኛል ብሎ የትህነግ የወልቃይትና ራያ አስመላሽ ኮሚቴ ሆኖ ከርሟል። ሰሞኑን በይፋ አብይን ደግፎ ተናግሮ ተናደውበታል። በሙዚቃ አቀናብረው ያስቀመጡትን እያወጡለት ነው። ለጊዜው በከፈሉህ ትሰራለህ እንጅ መቸም አይለቁህም። አንተን ከሚምሩህ ኢሳያስን በቀላሉ ይቅር ይሉታል።
14.9K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 17:30:09 ይለይላችኋ! ምን አገባን!

የፖለቲካው አሰላለፍ ሲለይለት ግልጥ እያለ ይመጣል! ቴድሮስ ፀጋዬ ኤርሚያስ ከኦሮሞ ብልፅግና ጋር ሲገናኝ ደርሶበት ካባረረው ቆይቷል። ለኤርሚያስ ቴድሮስ ነበር ከህወሓት ጋር መገናኛ ገመዱ፣ አሁን አማራጭ ፍለጋ የትግራይ አክቲቪስት በየቀኑ ያቀርባል። ያም ሆኖ ኤርሚያስ አልተረፈም። ፖለቲካው ከረር ሲል የኦሮሞ ብልፅግና አጀንዳውን ሲያመጣ ፀቡ ግልፅ እየወጣ ነው።

በነገራችን ላይ ኤርሚያስ "አንተምኮ ወገን አለህ" ተብሎ የኦሮሞ ብልፅግናን በይፋ ከወገነ ቆይቷል። ትህነግን ደግሞ ለጥቅም። ዞሮ ዞሮ ይለይላችሁ! የሚያገባን ነገር የለም!
14.2K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ