Get Mystery Box with random crypto!

ብልፅግና በይፋ ከኢራን ጎን ተሰልፌያለሁ እያለ ነው! ይህ ዘገባ ሆን ተብሎ የተሰራ ነው። ከቱርክ | Getachew shiferaw

ብልፅግና በይፋ ከኢራን ጎን ተሰልፌያለሁ እያለ ነው!

ይህ ዘገባ ሆን ተብሎ የተሰራ ነው። ከቱርክ ቀጥሎ ከኢራን ድሮን የሚያገኘው ብልፅግና ውለታውን በፕሮፖጋንዳ እየተወጣ ነው። በዚህ ፍጥነት ከኢራን ጋር መቆሙን የገለፀበት ገራሚ የፕሮፖጋንዳ ዘገባ ነው!

1) እስካሁን በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከሚገልፁት ውጭ በቁጥር ሁሉ አስቀሞጦ፣ የእስራኤል ስትራቴጅክ ቦታዎች ተጠቁ ብሎ በግልፅ በርዕስ ያስቀምጣል።

2) ይህን የፕሮፖጋንዳ ዘገባውን ታማኒ ለማስመሰል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደዘገቡት አድርጎ ያቀርባል። ዝርዝር ላይ ግን በማስረጃነት የሚያቀርበው የኢራንን የፕሮፖጋንዳ ቻናል ነው።

3) ጦርነቱ የሁለቱ አገራት ሆኖ ርዕስ ያደረገው የኢራን ቻናል ላይ የወሰደውን ሆኖ በውስጥ ዘገባው የእስራኤልን ባለስልጣን ቃል በትንሹ አካትቷል። የዘገባው አንጓ ግን ኢራን ስኬታማ ጥቃት እንዳደረገች ማሳየት ነው። ብዙ ጊዜ መሰል ዜናዎች ሲሰሩ የሁለቱም በርዕስነት የሚካተቱበት መንገድ ይገለፃል።

4) ኢቲቪ በትዕዛዝ የዘገበው ባይሆን በዚህ ደረጃ ፕሮፖጋንዳ አይሆንም ነበር። አሊያም ዜናውን ኢራን ይህን ያህል ኢላማ መታሁ አለች ብሎ በዘገብ ይችል ነበር። ይህም ፕሮፖጋንዳን ማስተጋባት ቢሆንም አሁን ከሰራው ይሻለው ነበር።

5) ኢቲቪ በዚህ መንገድ እየዘገበ ያለው የእስራኤል መንግስት በይፋዊ መግለጫ ጥቃቱን መቀልበሱን በገለፀበት፣ የአንድ የኢራን ጣቢያን እንደ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች አድርጎ በርዕስ አጉልቶ፣ ቀባብቶ ነው።

ይህ ዓለምን ያሰጋ ጦርነት ነው። ለብልፅግና ደግሞ ትርፍ አለው። ድሮን ያገኝበታል። ለዛም ነው በዚህ ደረጃ የዓለም አቀፍ ጦርነት ላይ ወገንተኝነትን የሚያሳየው።

ኢቲቪ የሚሰራው በብልፅግና ቀጥተኛ ትዕዛዝ ነው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ እያንዳንዱ ዘገባ የፖለቲካ ቃና ተሰጥቶት፣ ከብልፅግና ኃይል ተዋቅሮ እያረመ የሚወጣ ነው። የአገር ውስጡ አልበቃ ሲል ከአለም ጦርነትም አተርፋለሁ ብሎ የሚሰራው ፕሮፖጋንዳ ነው።