Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-03-11 18:00:00
18.1K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 17:59:51 አንድም የአማራ ተወካይ እንዳይገኝ ተደርጓል!

በአፍሪካ ህብረቱ የስምምነቱ መገምገሚያ ስብሰባ ላይ አንድም የአማራ ተወካይ እንዳይገኝ ተደርጓል። በስምምነቱ ወቅት ያልነበረው ደብረፅዮን እንኳ ሲገኝ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው የተደራደሩት የአማራ ተወካዮች እንዳይገኙ ተደርገዋል። ይህ የጀመረው ከድርድሩ ማግስቴ በተደረገው የኬንያው ስብሰባ ሲሆን ያ ስብሰባ የትህነግና ኦህዴድ የጓዳ ስምምነት በግልፅ የተፈፀመበት ነው።
18.4K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:22:20
13.2K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:22:14 ወፍ ብቻ ሳይሆን አውሮፕላኑም መሳሪያ እያመላለሰበት ነው!

ይልማ መርዳሳ "ያለ እኛ ፈቃድ አየር ክልላችን ወፍ እንኳን አያልፍበትም" ብሎ ነበር። ወፍ ብቻ ሳይሆን መሳሪያ የጫነ አውሮፕላን መሳሪያ አራግፎ ተመልሷል። ሰሞኑን ከሱዳን በኩል ወደ ትግራይ በሌሊት አውሮፕላኖች ተመላልሰዋል። ሲጣራ ደግሞ እስካሁን ዘግይቶ "ትጥቅ ፍታ" እየተባለ ያለው ትህነግ ተጨማሪ ትጥቅ እያስገባ ነው።

ሰሞኑን አውሮፕላኖች በሌሊት ተመላልሰው ሽሬና አክሱም አርፈው መሳሪያ አራግፈው ተመልሰዋል። በአየር ክልላችን ወፍ አያልፍም የሚለው ጀኔራል ተራ ወሬ እንጅ እውነቱን አይደለም። አሊያም በእነሱ ትብብር ነው መሳሪያ የሚገባው ማለት ነው።

ነገ የሰላም ስምምነቱ ለመገምገም ስብሰባ ይደረጋል። ከስምምነቱ ማግስት ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ ግን መሳሪያ በአውሮፕላን እየገባለት "የሰላም ስምምነቱ ይከበር" ማለቱ አይቀርም።
14.3K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 12:07:14
14.5K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 12:07:01 "እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም"

የፋኖን ዜና ሲሰሩ ከስህተታቸው የተማሩ የሚመስለው የዋህ ይኖራል። እነሱ ግን ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ነው የሚፈልጉት። የፋኖን ዜና ሰርተው ተመልክተህ ዘወር ስትል የኦሮሞ ብልፅግና የአማራን ግዛታዊ አንድነት ለመበታተን ያመጣው ህዝብ የማያውቀው ጥያቄ ሲያበኩ ታገኛቸዋለህ። ዋናው አላማቸው ይህ ፀረ አማራነት ስለሆነ።

ይህ የህዝብ ጥያቄ እንዳልሆነ ይታወቃል። ነገር ግን መቀሌና ናዝሬት ቢሮ ተከፍቶላቸው፣ በጀት ተመድቦላቸው አብሮ የኖረና የተዋለደ ህዝብን ለማጋጨት የሚሰሩት ኃይሎች አላማ ነው። የትህነግ/ህወሓት አፈቀላጤዎችም የህዝብ ግንኙነቶቻቸው ናቸው።

የትህነግ አፈ ቀላጤዎች ፋኖን "በመከላከያ ታዝሎ ገብቶ" እያሉ ያለ ስሙ ያጠለሹት ነበር። አሁን ወደ አዲስ አበባ መመለሻ እድል ካገኘን ብለው ስሙን በመልካም ሲጠሩ እውነት የሚመስለው ካለ እባብነታቸውን የዘነጋ መሆን አለበት።

ትህነግ አማራውን ለማጋጨት በሚል በልዩ ዞንና ወረዳ ከፋፍሎታል። ይሁንና በሰላም እየኖረ ነው። በአስተዳደር መከፋፈሉ ስላልበቃ በሀሰት ትርክት ወደ ፖለቲካ ቅራኔ እንዲገባ ሰርተውበታል። የኦሮሞ ብልፅግና ከልክ በላይ እጁን አስገብቶ ህዝብን እርስ በእርስ ለማጋጨት እየሰራ ነው። በዚህ አላማ ሁለቱም አንድ ናቸው። የትህነግ ክፉዎችም ላይ ላዩን ስለ አማራና ትግራይ ህዝብ አንድነት እያወሩ፣ በእውኑ ግን የአማራውን ግዛት አንድነት መፈታተንን ቀጥለውበታል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ትግራይ ውስጥ በርካታ ማንነት ያለው ህዝብ እያለ አንድም ልዩ ወረዳና ዞን ሳይፈጥሩ ነው። ፋኖ የእንድርታን፣ የተንቤንን፣ የኢሮብን፣ የሽሬን ወዘተ ጥያቄ አንስቶ አላቦካም።
14.8K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 11:53:03 ይታወቃል!

ታደሰ ወረደ ጦርነቱ እንዳበቃ እንደወለልህ የፃፍኩትኮ ወዲያው ነው። አመስግኖሃል። አግዘን ብሎሃል። ዜና ልትሰራበት አይደለም የሚደዌሉልህ። በትዕዛዝ ያሰሩሃል። ይታወቃል።

በተለይ ወልቃይት ላይ እንድትሰራ፣ የሰራህላቸውን "የስኳድ ሰነድ" እየደጋገምክ እንድትናገርላቸው ገልፀውልሃል። በመፅሀፍህ "ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል" የተሰኘውን የናዚ ፕሮፖጋንዳ ተጠቅመህ "ስኳድ" ስትል የምትውለው ቀብድ ተቀብለህ የሰራኸውን ሰነድ ነው። የትህነግ /ህወሓት ጀኔራሎቹም፣ ፖለቲከኞቹም ትኩረት አድርግልን ብለውህ ነው። ይታወቃል ባትናገረውም!

ሴኮ ቱሬ በድሮን ቢሞት፣ ድሮን የማያሰጋው ሴኮ አገኝተናል እያሉህ ነው።
15.9K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 22:48:38 ኤርሚያስ ብልፅግና ለሚዲያው ለሰጠው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል! ሌላ ከመጠየቁ በፊት መሆኑ ነው። ቀብድ።

"ሚዲያ እየሰራሁ ያለሁት በገዥው ፓርቲ ድጋፍ ነው። ፕሮግራሜን የሚያስተዋውቁትም ኢዲተሬም የብልፅግና ሰዎች ናቸው።" ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ
12.6K viewsedited  19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 18:41:44
18.2K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 18:41:40 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “ዳኛው ይነሱልኝ” ብሎ በመጠየቁ አንድ ሺሕ ብር እንዲቀጣ ተፈረደበት


ጋዜጠኛ ተመስን ደሳለኝ የቀረበበትን ይግባኝ ከሚመለከቱት ዳኞች መሃል የግራ ዳኛው አቶ መሐመድ አሕመድ ከዚህ ቀደም በዚሁ መዝገብ በሰጡት የተሳሳተ ትዕዛዝ ምክንያት “በቀጣይ ትክክለኛ ፍትሕን ሊሰጡኝ ስለማይችሉ ይነሱልኝ” ሲል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ በዛሬው ቀን ትእዛዝ ሰጥቶበታል፡፡


ጋዜጠኛ ተመስገን ቅሬታውን ያቀረበው ጥር 7/2016 ዓ.ም ሲሆን፤ ውሳኔ ለመስጠት ለጥር 28/2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁንና፣ በጥር 28ቱ ቀጠሮ እንዲነሱ “አቤቱታ የቀረበባቸው ዳኛ ስልጠና ላይ ስለሆኑ ውሳኔ አልሰጠንም” በሚል ለዛሬ የካቲት 21/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከችሎት እንዲነሱ ቅሬታ የቀረበባቸው ዳኛ “አልነሳም” ብለዋል፡፡


በዛሬው ቀጠሮም፣ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ሸምሱ ሲርጋጋ በንባብ ባሰሙት ትዕዛዝ “እንዲነሱ የተጠየቁት ዳኛ መልካም ስብዕና ያለቸው መሆኑን” በመጥቀስ ጥያቄውን ውድቅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ትእዛዝን በተመለከተ አስተያየቱን የገለጸው ጋዜጠኛ ተመስገን “የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እኔን ስጋት ላይ የጣለ ነው” ብሏል፡፡ ጋዜጠኛው ለዚህ ቅሬታው “መሰረታዊ ነው” ያለውንም ነጥብ አስቀምጧል፡፡ “ያቀረብኩት አቤቱታ፣ ዳኛው ከዚህ ቀደም በሰጡት ትዕዛዝ ዐቃቢ ሕግ ያልጠየቀውን ዳኝነት እንዲካተት አድርገው ከሳሽን ያለአግባብ በመጠቅማቸው፣ እኔን ጉዳት ላይ የሚጥል ትዕዛዝ መስጠታቸውን የተመለከተ ነው፡፡ ስለዚህም ፍርድ ቤቱ በቀረበለት ቅሬታ መሰረት ‹ዳኛው ስህተት ሠርተዋል ወይስ አልሠሩም?› ወይም ‹ከሳሽ ያለአግባብ ጠቅመዋል ወይስ አልጠቀሙም?› የሚለውን መመርመር ሲገባቸው፤ ይህን ዋንኛ ጉዳይ ወደጎን ብሎ የቀድሞ ስብእናቸውን መነሻ በማድረግ ቅሬታዬን ውድቅ መደረጉ እጅጉን አስደንግጦኛል፡፡” ብሏል።


ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው ያቀረበውን ተጨባጭ ቅሬታ ወደጎን ትተው፤ “ዳኛው ይነሱልኝ” የሚል ቅሬታውን ስላቀረበ አንድ ሺሕ ብር መቀጮ እንዲከፍል ተፈርዶበት፣ የተባለውን ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ግቢ ሊወጣ ችሏል፡፡
ጋዜጠኛው ላይ የቀረበውን የይግባኝ መልስ ለመስማት ለመጋቢት 16/2016 ዓ.ም ቀጠሮ ተስጥቷል፡፡
17.6K viewsedited  15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ