Get Mystery Box with random crypto!

ወፍ ብቻ ሳይሆን አውሮፕላኑም መሳሪያ እያመላለሰበት ነው! ይልማ መርዳሳ 'ያለ እኛ ፈቃድ አየር | Getachew shiferaw

ወፍ ብቻ ሳይሆን አውሮፕላኑም መሳሪያ እያመላለሰበት ነው!

ይልማ መርዳሳ "ያለ እኛ ፈቃድ አየር ክልላችን ወፍ እንኳን አያልፍበትም" ብሎ ነበር። ወፍ ብቻ ሳይሆን መሳሪያ የጫነ አውሮፕላን መሳሪያ አራግፎ ተመልሷል። ሰሞኑን ከሱዳን በኩል ወደ ትግራይ በሌሊት አውሮፕላኖች ተመላልሰዋል። ሲጣራ ደግሞ እስካሁን ዘግይቶ "ትጥቅ ፍታ" እየተባለ ያለው ትህነግ ተጨማሪ ትጥቅ እያስገባ ነው።

ሰሞኑን አውሮፕላኖች በሌሊት ተመላልሰው ሽሬና አክሱም አርፈው መሳሪያ አራግፈው ተመልሰዋል። በአየር ክልላችን ወፍ አያልፍም የሚለው ጀኔራል ተራ ወሬ እንጅ እውነቱን አይደለም። አሊያም በእነሱ ትብብር ነው መሳሪያ የሚገባው ማለት ነው።

ነገ የሰላም ስምምነቱ ለመገምገም ስብሰባ ይደረጋል። ከስምምነቱ ማግስት ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ ግን መሳሪያ በአውሮፕላን እየገባለት "የሰላም ስምምነቱ ይከበር" ማለቱ አይቀርም።