Get Mystery Box with random crypto!

'እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም' የፋኖን ዜና ሲሰሩ ከስህተታቸው የተማሩ የሚመስለው የዋህ | Getachew shiferaw

"እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም"

የፋኖን ዜና ሲሰሩ ከስህተታቸው የተማሩ የሚመስለው የዋህ ይኖራል። እነሱ ግን ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ነው የሚፈልጉት። የፋኖን ዜና ሰርተው ተመልክተህ ዘወር ስትል የኦሮሞ ብልፅግና የአማራን ግዛታዊ አንድነት ለመበታተን ያመጣው ህዝብ የማያውቀው ጥያቄ ሲያበኩ ታገኛቸዋለህ። ዋናው አላማቸው ይህ ፀረ አማራነት ስለሆነ።

ይህ የህዝብ ጥያቄ እንዳልሆነ ይታወቃል። ነገር ግን መቀሌና ናዝሬት ቢሮ ተከፍቶላቸው፣ በጀት ተመድቦላቸው አብሮ የኖረና የተዋለደ ህዝብን ለማጋጨት የሚሰሩት ኃይሎች አላማ ነው። የትህነግ/ህወሓት አፈቀላጤዎችም የህዝብ ግንኙነቶቻቸው ናቸው።

የትህነግ አፈ ቀላጤዎች ፋኖን "በመከላከያ ታዝሎ ገብቶ" እያሉ ያለ ስሙ ያጠለሹት ነበር። አሁን ወደ አዲስ አበባ መመለሻ እድል ካገኘን ብለው ስሙን በመልካም ሲጠሩ እውነት የሚመስለው ካለ እባብነታቸውን የዘነጋ መሆን አለበት።

ትህነግ አማራውን ለማጋጨት በሚል በልዩ ዞንና ወረዳ ከፋፍሎታል። ይሁንና በሰላም እየኖረ ነው። በአስተዳደር መከፋፈሉ ስላልበቃ በሀሰት ትርክት ወደ ፖለቲካ ቅራኔ እንዲገባ ሰርተውበታል። የኦሮሞ ብልፅግና ከልክ በላይ እጁን አስገብቶ ህዝብን እርስ በእርስ ለማጋጨት እየሰራ ነው። በዚህ አላማ ሁለቱም አንድ ናቸው። የትህነግ ክፉዎችም ላይ ላዩን ስለ አማራና ትግራይ ህዝብ አንድነት እያወሩ፣ በእውኑ ግን የአማራውን ግዛት አንድነት መፈታተንን ቀጥለውበታል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ትግራይ ውስጥ በርካታ ማንነት ያለው ህዝብ እያለ አንድም ልዩ ወረዳና ዞን ሳይፈጥሩ ነው። ፋኖ የእንድርታን፣ የተንቤንን፣ የኢሮብን፣ የሽሬን ወዘተ ጥያቄ አንስቶ አላቦካም።