Get Mystery Box with random crypto!

አርሶ አደሩን እንደጨፈጨፉ እየነገሩን ነው! አርሶ አደሩን ቤት ለቤት እየገቡ፣ ባገኙበት ቦታም ሁ | Getachew shiferaw

አርሶ አደሩን እንደጨፈጨፉ እየነገሩን ነው!

አርሶ አደሩን ቤት ለቤት እየገቡ፣ ባገኙበት ቦታም ሁሉ ይገድላሉ። ቤቱን ፈትሸው ህጋዊ መሳሪያውን ቀምተው ይሰበስባሉ። የፋኖ አስመስለው ዜና ይሰሩበታል። ፋኖ መትረየስ፣ ስናይፐርና ዲሽቃ በታጠቀበት ሁኔታ ምንሽር፣ አብራራው፣ ጓንዴና አልቤን መሳሪያን ፋኖን ገድለን የማረክነው እያሉ በይፋ የፈፀሙትን ወንጀል ዜና ያደርጋሉ።

ፋኖ ሲያንስ ክላሽ ከፍ ሲል ዲሽቃና ሌላም ታጥቋል። ይህ የቃታ ብረት አርሶ አደሩን እየገደሉ ቤቱን ፈትሸው የሰበሰቡት ነው። እየነገሩን ያለው አርሶ አደሩን መጨፍጨፋቸውን ነው!