Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜያዊ አስተዳደሩ አረጋግጧል። ግን የታሰሩት 122 ብቻ አይደሉም! ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነ | Getachew shiferaw

ጊዜያዊ አስተዳደሩ አረጋግጧል። ግን የታሰሩት 122 ብቻ አይደሉም!

ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ተይዘው ያልተለቀቁ ከአንድ ሺህ በላይ እስረኞች መቀሌ ጨለማ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ሲገለፅ ቆይቷል። አማራ ክልል ላይ "ጥቁር ክላሽ" እያለ ሰበብ የሚፈልገው መቀሌ ላይ ወታደሮቹ በቀን አንድ ዳቦ እየተጣለላቸው በሚሰቃዩበት ሁኔታ ነው።

በትህነግ/ህወሓት ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር 122ቱን ፈትቻለሁ ብሏል። እስር ላይ ያሉት ግን ከአንድ ሺህ በላይ ናቸው። አገዛዙ የሰላም ስምምነት ወዘተ ሲል በጀት የለቀቀለት በስሬ ያለ ነው የሚለው የእነ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር ግን በልመና የተወሰኑትን ብቻ ነው የፈታለት። አማራ ክልል ላይ ምንም ሳይፈጠር ሰበብ ሲፈልግ "አስገድጀ ወደ ድርድር አስመጥቸዋለሁ" የሚለው ትህነግ ግን እስካሁን በልመና ሁሉንም አልፈታለትም። ያውም አገዛዙ ትግራይ ውስጥ ኃይል አለኝ እያለ።

እስካሁን ስንለው የቅየነውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ወጥቶ አረጋግጧል። 122 ፈትቸለታለሁ ብሏል። ሌሎቹን በመደራደሪያነት ይዞለታል።