Get Mystery Box with random crypto!

Tofik Bahiru

የቴሌግራም ቻናል አርማ fiqshafiyamh — Tofik Bahiru T
የቴሌግራም ቻናል አርማ fiqshafiyamh — Tofik Bahiru
የሰርጥ አድራሻ: @fiqshafiyamh
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.13K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-14 07:07:23 ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዓቢድ በጀነት ዛፍ ስር እንጂ እረፍት የለውም። ሙሒብ ጭማሪ በሚገኝበት ቀን [በቂያማ] እንጂ እርጋታ የለውም።»
:
ኢላሂ!
በዲንህ የምትደሰት ነፍስ ስጠን።
በዚክር የሚረካ ቀልብ ስጠን።
አስገራሚ ፍጥረትህን አይቶ የሚያስተነትን ዐይን ስጠን።
በመንገድህ መስዋኢት መሆንን ስጠን።
ነቢያትህን እና ወልዮችህን በጀነት ውስጥ ማግኘት ስጠን።
መልካም የእረፍት ቀን!
751 viewsedited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 22:51:01 «ካንተ የሚገኘው የሙእሚን ድርሻ ሦስት ዓይነት ነው: ‐
⚀ ካልጠቀምከው አትጉዳው፤
⚁ ካላስደሰትከው አታስጨንቀው፤
⚂ ካላወደስከው አታውግዘው።»
የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ አር‐ራዚይ [ረሒመሁላህ]
1.9K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 22:50:58 ሸይኽ አቡል‐ዐባስ አል‐ሙርሲይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አንድ የአላህ ባርያ ጊዜው ለአራት የተከፈለ ነው: ‐
⚀ አንደኛው የአምልኮ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ልግስና ማየት ይገባል።
⚁ ሁለተኛው የኃጢኣት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ተውበትን ማሳመር ይገባል።
⚂ ሦስተኛው የፀጋ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ተገቢው ነገር ምስጋና ማድረስ ነው።
⚃ አራተኛው ጊዜ የመከራ ነው። ይህ ትእግስትህን ይሻል።
እነዚህን አደቦች በሙሉ የጠበቀ ሰው የተሟላ ክብር እና በምርጦችም ሆነ ተርታዎች ዘንድ የመልካምነት ደረጃን ይጎናፀፋል።»
1.7K viewsedited  19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 22:53:54 «ከአንድ ሰው በስተቀር ሁሉም ሰው ጀነት ገቢ ነው ተብሎ ቢታወጅ ያ ሰው እኔ እንዳልሆን እፈራለሁ።
ከአንድ ሰው በስተቀር ሁሉም እሳት ገቢ ነው ቢባል ያ ሰው እኔ እሆናለሁ ብዬ እከጅላለሁ።»
ሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ]
:
አቡ ኑዐይም "ሒልየቱል‐አውሊያእ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ አስፍረውታል።
354 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 15:33:31 Tofik Bahiru pinned an audio file
12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 15:27:30 ሰፊና ክፍል 65
ወደ ሆድ ቢደርሱም ጾም የማያፈርሱ ነገሮች
ሚያዚያ 29/ 2015 ዓ. ል.
https://t.me/fiqshafiyamh/1157
1.0K viewsedited  12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 15:27:08
1.0K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:48:48 ነ‌ፍ‌ስ‌ን‌ መ‌ሰ‌ሞ‌ት‌

ድንቅ ንግግር ከኢማም ኢብኑ ቀዪም አል‐ጀውዚያ [ረሒመሁላህ]: ‐
«ረቡል‐ዓለሚን ዘንድ ትልቅ ደረጃ ያለው ሰው ነፍሱን ለአላህ የሰሞተ [ስሞታ ያደረገ] ሰው ነው።»
:
ነፍስህን አላህ ፊት ስትወቅስ ምልክት አለው: ‐
❶ ነፍስህ ወደ ሐራም ስትጎተጉትህ "ሐስቢየላህ ወኒዕመል ወኪል" ብለህ ወደርሱ ትሸሻለህ።
❷ ነፍስህ በዒባዳ ላይ ስትሳነፍ "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለትን ታበዛለህ። በስንፍናህ ላይ የአላህን እገዛ ትጠራለህ።
❸ ከኃጢኣት ምህረት እንደምትለምነው ሁሉ ከዒባዳ በኋላም ኢስቲግፋር እና ተጨማሪ ዒባዳ ታስከትላለህ። በተለይም በቀልብህ ውስጥ በነፍስህ መደነቅ፣ አምልኮህን አብዝተህ መመልከት ሲሰማህ ኢስቲግፋር ታበዛለህ። ምንም ብትሰራ ከአላህ ሐቅ አንፃር ስራህ ሁሉ ትንሽ እንደሆነ ለነፍስህ ትነግራለህ።
❹ በኃጢአት ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች ሲገጥሙህ አላህ በዲንህ እንዳይፈትንህ ትለምነዋለህ።
❺ ነፍስህን እንዲያበጅልህ፣ ኻቲማህን እንዲያሳምርልህ ዱዓእ ታበዛለህ።
እንዲህ ትለዋለህ: ‐
«ኢላሂ! ነፍሴን ላንተ እሰሙታለሁ። አስተካክልልኝ!
አላህ ሆይ! ነፍሴን እገራት ዘንድ አግዘኝ።
አላህ ሆይ! ከነፍሴ ተንኮል ጠብቀኝ። አንተ አናታቸውን ከምትይዛቸው [ከምትቆጣጠራቸው] ተንቀሳቃሾች ሁሉ ተንኮል ጠብቀኝ።
አላህ ሆይ! በዒባዳ ላይ የተረጋጋች፣ ቀደርህን የወደደች ነፍስ ስጠኝ።
አላህ ሆይ! ነፍሴን ከሰውም ሆነ ከአጋንንት ሰይጣናት ውስወሳ አፅዳልኝ።»
አሚን!
https://t.me/fiqshafiyamh
1.2K viewsedited  05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 18:35:15 አላህ እና ተወዳጃችንን [ﷺ] በሴቶች በኩል ፈልጉ…
አራት ሴቶች በሙእሚን ወንድ ልብ ውስጥ ቦታ አላቸው። እናቱ፣ ሚስቱ፣ እህቱ እና ሴት ልጁ።
የመጀመሪያዋ የአላህ ውዴታ ከርሷ ውዴታ ጋር የተቆራኘ ነው።
ሁለተኛዋን ማክበር የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ኑዛዜ ነው።
ሦስተኛዋን በዝምድናው የቀጠላት አላህ ከእዝነቱ ጋር ይቀጥለዋል።
አራተኛዋን በመልካም ኮትኩቶ ማሳደግ ጀነት የሚያደርስ መንገድ ነው።…
ሴቶችን ተንከባከቡ አላህ በመልካም እንክብካቤው ያካብባችኋል።
https://t.me/fiqshafiyamh
1.2K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 13:17:55 "ኢኽላስ ማለት ኢኽላስን አለማየት ነው!"
=========================
መስለማ ኢብኑ ዐብዱል‐መሊክ አሚር የሆነበት ሰራዊት በግንብ የታጠረ የሮሞችን ከተማ ከቧል። ከተማዋ ግን ግንቧ ከፍ ያለ፣ በሮቿም በሚገባ የተዘጉ በመሆኑ ሙስሊሞች አጥሩን አልፈው መግባት ተሳናቸው። አጥሩ ላይ ያደፈጡት ቀስተኞች በቀስት በመደብደብ አላስቀርብ አሏቸው። የሮሞቹ ኃይል አመዘነ። ሙስሊሞቹ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቁ።
:
ሙስሊሞች ከበው በቆዩበት አንዱ ሌሊት ላይ ከሙስሊሞቹ መሀል አንዱ ወታደር ለማመን የሚቸግር ዘዴ ፈጠረ!…

ከሰዎች ተነጥሎ በመደበቅ መሬቱን ውስጥ ለውስጥ መቆፈር ጀመረ። ወደ ውስጥ መሸጋገሪያ ሊሆን የሚችል ቦይ አበጀ። ሥራውን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ግን ለማንም ሳይናገር ከሰራዊቱ ጋር ተቀላቀለ።
:
በሚቀጥለው ቀን እንደተለመደው ሙስሊሞች ለውጊያ ተሰናዱ። ይህ ጀግና የቆፈረው ቦይ ውስጥ በመግባት የከተማዋን በር ከፈተ።
ሙስሊሞቹ ግርርር ብለው ወደ ከተማው ገቡ። አጥሩ ላይ በመውጣት ወደ ውስጥ ዘለቁ። ሮሞች በድንጋጤ የተዋጡት የተክቢራ ድምፅ በከተማው ውስጥ በቤተመንግስቱ ሜዳ ላይ ሲሰሙ ነው! በአንድ ጀግና ምክንያት ሙስሊሞቹ ድል ተጎናፀፉ!
:
ከውጊያው በኋላ መስለማ ኢብኑ ዐብዱል‐መሊክ ሰራዊቱን ሰበስቦ ከፍ ባለ ድምፅ "በከተማው በር ላይ ቦዩን የቆፈረው ማን ነው!? ወደኛ ይምጣና እንሸልመው!" በማለት ተጣራ።
ማንም አልወጣም!…
ጥሪውን ደገመው!…
"በከተማው በር ላይ ቦዩን የቆፈረው ማን ነው!? ወደኛ ይምጣና እንሸልመው!" አለ።
ማንም ሰው አልወጣም!
የሰውየው ማንነት ሳይታወቅ ታደረ። በጧት መስለማ የትላንቱን ጥሪ ደገመው። "በከተማው በር ላይ ቦዩን የቆፈረው ማን ነው!? ወደኛ ይምጣና እንሸልመው!"
አሁንም እንደትላንቱ ማንም አልወጣም!…
ሦስተኛ ቀን ሆነ። መስለማ እንዲህ አለ: — "ቦዩን የቆፈረው ሰው በቀንም ሆነ በማታ ወደኔ እንዲመጣ ምዬበታለሁ!"…
:
ሌሊት ላይ አሚሩ በድንኳኑ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ፊቱን የሸፈነ አንድ ሰው ወደ ውስጥ ዘለቀ። መስለማ "ቦዩን የቆፈርከው አንተ ነህ?" አለ።
ሰውየውም "የቦዩ ቆፋሪ አሚሩ መሀላውን በማፍረስ እንዳይያዝ ሊያጠራው ይፈልጋል። ነገርግር ሦስት መስፈርቶች አሉት።" አለ።
"መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው?" አለ፤ መስለማ።
"⑴ ስሙን ላትጠይቅ።
⑵ ፊቱን ላታስከፍት።
⑶ ሽልማት ላትሰጠው።" አለ።
መስለማ "መስፈርቶቹን ተቀብያለሁ።" አለ።
ሰውየውም "የቦዩ ቆፋሪ እኔ ነኝ።" አለውና ከድንኳኑ በመውጣት በሰራዊቱ ድንኳን ውስጥ ተሰወረ።
መስለማ በእምባ ተሞልቶ ከተቀመጠበት በመነሳት ተከታዩን አንቀፅ አነበበ: —

مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا۟ مَا عَٰهَدُوا۟ ٱللَّهَ عَلَيْهِ فَمِنْهُم مَّن قَضَىٰ نَحْبَهُۥ وَمِنْهُم مَّن يَنتَظِرُ وَمَا بَدَّلُوا۟ تَبْدِيلًا
"ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ፡፡ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ፡፡ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም፡፡"
:
መስለማ ከዚህ ክስተት በኋላ በሱጁዳቸው ላይ "አላህ ሆይ ከቦዩ ባለቤት ጋር ቀስቅሰኝ። አላህ ሆይ ከቦዩ ባለቤት ጋር ቀስቅሰኝ።" ይሉ ነበር።
:
የዚህ ታሪክ ፍሬ ሃሳብ:
——— ——— ———
⚀ ለአላህ ካልሆነ ለምንም ነገር ቢሆን መጨረሻው አፈር ነው!
⚀ በአላህና ባንተ መሀል ማንም ያልገባበት መልካም ሥራ ደብቀህ አስቀምጥ። ከቻልክ ከራስህም ደብቀው። ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ወቅት ይጠቅምሃል!
⚀ በርካታ የሰለፍ ሰዎች አንድ ሰውም ቢሆን ያየውን ሥራቸውን ውድቅ ነው ብለው በማሰብ ከምንም አይቆጥሩትም ነበር!
⚀ ኢኽላስ የመልካም ስራዎች ህይወት ነው። ያለ ኢኽላስ ስራዎቻችን ሁሉ ህይወት አልባ ቅርጾች ናቸው!
⚀ ኢኽላስ በህይወት የተኖረ፣ አንተም መፈፀም የምትችለው እውነታ እንጂ የማይጨበጥ፣ በሰው ዓቅም ሊፈፀም የማይችል ልዩ ነገር አይደለም። በልምምድ ኢኽላስን መላበስ ይቻላል!
1.3K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ