Get Mystery Box with random crypto!

ነ‌ፍ‌ስ‌ን‌ መ‌ሰ‌ሞ‌ት‌ ድንቅ ንግግር ከኢማም ኢብኑ ቀዪም አል‐ጀውዚያ [ረሒመሁላህ]: ‐ « | Tofik Bahiru

ነ‌ፍ‌ስ‌ን‌ መ‌ሰ‌ሞ‌ት‌

ድንቅ ንግግር ከኢማም ኢብኑ ቀዪም አል‐ጀውዚያ [ረሒመሁላህ]: ‐
«ረቡል‐ዓለሚን ዘንድ ትልቅ ደረጃ ያለው ሰው ነፍሱን ለአላህ የሰሞተ [ስሞታ ያደረገ] ሰው ነው።»
:
ነፍስህን አላህ ፊት ስትወቅስ ምልክት አለው: ‐
❶ ነፍስህ ወደ ሐራም ስትጎተጉትህ "ሐስቢየላህ ወኒዕመል ወኪል" ብለህ ወደርሱ ትሸሻለህ።
❷ ነፍስህ በዒባዳ ላይ ስትሳነፍ "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለትን ታበዛለህ። በስንፍናህ ላይ የአላህን እገዛ ትጠራለህ።
❸ ከኃጢኣት ምህረት እንደምትለምነው ሁሉ ከዒባዳ በኋላም ኢስቲግፋር እና ተጨማሪ ዒባዳ ታስከትላለህ። በተለይም በቀልብህ ውስጥ በነፍስህ መደነቅ፣ አምልኮህን አብዝተህ መመልከት ሲሰማህ ኢስቲግፋር ታበዛለህ። ምንም ብትሰራ ከአላህ ሐቅ አንፃር ስራህ ሁሉ ትንሽ እንደሆነ ለነፍስህ ትነግራለህ።
❹ በኃጢአት ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች ሲገጥሙህ አላህ በዲንህ እንዳይፈትንህ ትለምነዋለህ።
❺ ነፍስህን እንዲያበጅልህ፣ ኻቲማህን እንዲያሳምርልህ ዱዓእ ታበዛለህ።
እንዲህ ትለዋለህ: ‐
«ኢላሂ! ነፍሴን ላንተ እሰሙታለሁ። አስተካክልልኝ!
አላህ ሆይ! ነፍሴን እገራት ዘንድ አግዘኝ።
አላህ ሆይ! ከነፍሴ ተንኮል ጠብቀኝ። አንተ አናታቸውን ከምትይዛቸው [ከምትቆጣጠራቸው] ተንቀሳቃሾች ሁሉ ተንኮል ጠብቀኝ።
አላህ ሆይ! በዒባዳ ላይ የተረጋጋች፣ ቀደርህን የወደደች ነፍስ ስጠኝ።
አላህ ሆይ! ነፍሴን ከሰውም ሆነ ከአጋንንት ሰይጣናት ውስወሳ አፅዳልኝ።»
አሚን!
https://t.me/fiqshafiyamh