2023-04-28 07:26:33
የ͟ተ͟ዘ͟ለ͟ለ͟ው͟ ገ͟ፅ͟
ምን እንደምንሰራ፣ እንዴት እንደምንሰራ እንማራለን።…
ባወቅነው ለመስራት እንለፋለን። የስራውን ክብደት ተሸክመን በትእግስት እንታገላለን። ያለንን ፀጋ ሁሉ ለመልካም ስራዎቻችን እናውላለን።
ነገርግን ምን መነየት አለብን? እንዴት መነየት አለብን? ኒያችን እንዳይበላሽ ምን ማድረግ አለብን?…
እንዲህ አይነቱ ትምህርት አስተማሪም ተማሪም የሌለው፣ መድረክ ያልተገኘለት አንገብጋቢ ነገር ሆኗል።
እየለፋን እንኖራለን። እየደከምን እንሞታለን። በኒያችን ጉዳይ ሳንነቃ፣ የሚያነቃም ሳይገኝ ድፍርስ ስራችንን ይዘን፣ ስንኩል መንገድ ተከትለን ወደ አኺራ እንሄዳለን።
* * *
ደጋጎቹ ስለ ሥራ ከሚያወሩት በላይ ስለ ኢኽላስ ያወሩ ነበር። ኢማም ሰውሪይ [ረሒመሁላህ] «ሰዎች ያዩትን ስራዬን እንዳለ አልቆጥረውም።» ይሉ ነበር።…
በእርግጥ ስለ ኢኽላስ ስናወራ እጅግ ረቂቅ ስለሆነ ስውር ነገር እያወራን ነው። ሥራ በሰዎች አድናቆት ስላገኘ ኢኽላስ የለውም አይባልም። በአንፃሩ ሰውየው ማንም ባላየው ሥራው ላይ ኢኽላስ የሌለው አስመሳይ [ሙራኢ] ሊባል ይችላል።
ኢኽላሱን ለማሳካት ብዙ ዘመን የደከመና የለፋ እንኳን ኢኽላስን እየፈለገ ይኖራል እንጂ "ሙኽሊስ" ነኝ ብሎ የኢኽላስ ቀበሌ ገዢ መሆን አይቻለውም። ዐስር አመት፣ ሃያ አመት፣ ሃምሳ አመት፣ ከፈለግህ መቶ አመት በለው… ኢኽላስን ፍለጋ ብቻ ብትደክም የእውነት ሙኽሊስ መሆንህን ማረጋገጥ እንኳን አትችልም።
አዎን! ጉዳዩ ከባድ ነው!
ለምሳሌ: ‐ እድሜ ልክህን እጅህ ባፈራው ነገር ሁሉ ስትደግፈው፣ ስትመፀውተው፣ ስትረዳው የነበረን ሰው አስብ። ለአላህ ብለህ እንዳደረክለት ልብህ ይነግርሃል። አንተም የሰው ምስጋና ያልሻህበት፣ ዱንያዊ ምንዳ ያልከጀልክበት መልካም ስራ ጥራ ብትባል አስቀድመህ የምትጠራው መልካም ሥራህ ይኸው ምፅወታ እንደሆነ ታምናለህ።
ከዚያም ከእለታት በአንድ ቀን ያ ብዙ የዋልክለት ሰው ሥር የሚያውል ጉዳይ ገጠመህ። ነገርግን ሰውየው ካንተ ጉዳይ ይልቅ እንዳንተው የተቸገረ በውል የማያውቀው ሌላ ሰው ገጠመውና ካንተ ጉዳይ የዚያን አስቀደመ። ምን ይሰማሃል?!…
ሶደቃህ ትዝ ይልሃል!… የዋልክለትን ውለታ ታስባለህ!… ከጉዳይህ ይልቅ የሌላኛውን ሰው ጉዳይ ማስቀደሙ ያንገበግብሃል!…
ይኸው በቀላሉ ስንት ዓመት ሙኽሊስ ነኝ ያልክበት ሙግት አፈር በላ ማለት ነው!…
ኢኽላስ እንደዚህ ነው። ዛሬ ላይ ሆነህ የማትለብሰው ዘውድ ነው። መቼም ለነፍስህ የማትሞግተው ሩቅ ነገር ነው። ኢኽላስ ዘመን፣ መከራ፣ ችግር፣ የሁኔታዎች ለውጥ የሚገልፀው ማንነት ነው!
አላሁም‐መ‐ጅዐልና ሙኽሊሲነ ለክ!
https://t.me/fiqshafiyamh
1.4K views04:26