Get Mystery Box with random crypto!

Tofik Bahiru

የቴሌግራም ቻናል አርማ fiqshafiyamh — Tofik Bahiru T
የቴሌግራም ቻናል አርማ fiqshafiyamh — Tofik Bahiru
የሰርጥ አድራሻ: @fiqshafiyamh
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.13K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-25 21:37:35 Tofik Bahiru pinned a photo
18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 14:00:42
ታላቁ ዓሊም አል‐ሐቢብ ዑመር ቢን ሙሐመድ ቢን ሐፊዝ [ሐፊዘሁላህ] «ከረመዳን በኋላ ለመፈፀም የምንነይታቸው ኒያዎች ምንድን ናቸው?» በማለት ተጠይቀው እንዲህ አሉ:‐
❶ መላው እድሜያቸው ረመዳን እንደሆኑ ሰዎች ለመሆን፤
❷ በቀንም ሆነ በማታ የምናከናውናቸው ተግባራት ከረሕማን ጋር ያለንን ቁርኝት የሚገልፁ እንዲሆኑ፤
❸ በሦስቱ ዐበይት ጉዳዮች [በዒልም፣ በመልካም ትድድር እና ሰዎችን ወደ አላህ በመጣራት (በዳዕዋ)] በመልካም ሁኔታ ኡመቱን ማገልገል፤
❹ የአላህን ውዴታ መፈለግ፤ የመልክተኛውን [ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም] ደስታ መሻት።
❺ ሁሌም ከአላህ ጋር ቀልባችንን በመሰብሰብ ላይ እንድንበረታ፤ በተለይም ቁርኣን በማንበብ እና በዚክር ላይ እንድንጠነክር፤
❻ ለአላህ ከተወዳጀናቸው ወንድሞቻችን ጋር መልካም የትውውስ መድረኮችን መፍጠር፤
❼ ስድስቱን የሸዋል ጾም መጾም፤
❽ በዓመት የሚገኙትን የዓረፋ ቀን፣ የሙሐረም ወርን ዘጠኝ እና ዐስር ቀን እና መሰል ጊዜያትን በጾም ማሳለፍ፤
❾ በወር ከሦስት ቀናት ያላነሰ መጾም።
አላህ ይወፍቀን!
1.1K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:27:10 «የሰው ልጅ በዘጠኝ ፍርሃቶች ውስጥ መኖር አለበት: ‐
❶ አላህ ያለ አግባብ ራሱን ለሚያካብድበት ዒባዳው እንዳይተወው፤
❷ ጉራ የሚያበዛበት የአላህ ፀጋን እንዳይክድ እና ኩራቱ ከምስጋና እንዳያግደው፤
❸ በአላህ ፀጋዎች ብዛት እየተሞኘ ቀስ በቀስ የአላህ ቁጣ ውስጥ እንዳይወድቅ፤
❹ ነገ አላህ ዘንድ ሲቀርብ ምንዳቸውን ይጠብቅ ከነበሩት አምልኮዎቹ ከሚጠብቀው ውጪ እንዳይገጥመው፤ መልካም ሥራዎቹ ራሳቸው ከኃጢኣት ተቆጥረው እንዳያገኛቸው፤
❺ በእርሱ እና በአላህ መካከል ያሉ የሚያውቃቸው ኃጢኣቶቹን፤
❻ የሰዎችን ሐቅ፤
❼ በቀረው የእድሜው ክፍል ምን እንደሚገጥመው፤
❽ በዱንያ ውስጥ እያለ ከአኺራ የቸኮለ ቅጣት እንዳይገጥመው፤
❾ አላህ ስለርሱ የሚያውቀውን ፍፃሜ፤ በውሳኔው መዝገብ ውስጥ ስሙ የትኛው ፍፃሜ ላይ እንደተፃፈ።»
አደቡን‐ኑፉስ፥ ኢማም አል‐ሓሪስ አል‐ሙሓሲቢይ፥ ገፅ 71
https://t.me/fiqshafiyamh
237 views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 04:30:54 Tofik Bahiru pinned «የሸዋል ጾም ======= ከአቡ አዩብ አል‐አንሷሪይ [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን ጾሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው ይህ ዓመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል። ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን የጾመ ከዚያም ከፊጥር በኋላ ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው አመቱን በሙሉ…»
01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 04:30:43 Tofik Bahiru pinned «ስለ ሸዋል ጾም ተጨማሪ ሃሳቦች ================= عَنْ أَبي أَيوبِ رضي الله عنه، أَنَّ رسولَ اللَّهِ [ﷺ] قَالَ: مَنْ صَامَ رَمَضانَ ثُمَّ أَتَبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كانَ كصِيَامِ الدَّهْرِ رواهُ مُسْلِمٌ. وفي رواية "فكأنما صام السنة كلها" «ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን…»
01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 04:30:35 ስለ ሸዋል ጾም ተጨማሪ ሃሳቦች
=================
عَنْ أَبي أَيوبِ رضي الله عنه، أَنَّ رسولَ اللَّهِ [ﷺ] قَالَ: مَنْ صَامَ رَمَضانَ ثُمَّ أَتَبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كانَ كصِيَامِ الدَّهْرِ رواهُ مُسْلِمٌ.
وفي رواية "فكأنما صام السنة كلها"
«ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው እድሜውን (ደህር) ሁሉ እንደጾመ ይሆንለታል።»
ሙስሊም አቡ አዩብ አል‐አንሷሪን በመጥቀስ ዘግበውታል።
በአሕመድ ዘገባ: ‐ «አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል።»
:
⚀ ትርጉም: ‐ «ሁሌም ከረመዳን በኋላ ስድስት የሸዋል ቀናት የጾመ ሰው እድሜውን በሙሉ ፈርድ ጾም እንደጾመ ይቆጠርለታል ማለት ነው።»
ኢብኑ ቃሲም ዐለት‐ቱሕፋ፥ ቅፅ 3፥ ገፅ 457

«የስድስቱን ቀን ጾም እያለፈ ከጾመ ደግሞ የጾመበት አመት ላይ ዓመቱን በሙሉ [ፈርድ] እንደጾመ ይቆጠርለታል። ካልጾመ ግን ዐስሩን ወር ብቻ እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ቡጀይሪሚ ዐለል‐ኸጢብ፥ ገጽ 2682

ወይም የመጀመሪያውን ዘገባ ከሁለተኛው ጋር በማመሳከር "ደህር" ማለት "ዓመት" ማለት ነው ልንል እንችላለን።
:
⚁ በዚህ መሰረት ከረመዳን በኋላ ስድስቱን በመጾም ሰውየው የሚያገኘው ጥቅም ዓመቱን በሙሉ ፈርድ እንደጾመ መቆጠሩን ነው። አለበለዚያ አመቱን በሙሉ ሱና እንደጾመ ይቆጠርለታል ማለት ነው ካልንማ በሌላው ወር ከሚገኘው ትሩፋት የተለየ ነገር በሸዋል አይገኝም ማለት ይሆንብናል።
ለምሳሌ: ‐ ረመዳንን ጾሞ ከዙል‐ቀዕዳ ወር ስድስት የጨመረ ሰውም አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል። በቀላሉ የረመዳንን ጾም በዐስር አባዝተን የ10 ወር ጾም ስድስቱን እንዲሁ በ10 አባዝተን የሁለት ወር ጾም በማድረግ የዓመት ሱና ጾም ጾመናል ማለት ይቻላል። ነገርግን የሸዋል ጾም ከሌላው ይለያል። ዓመቱን ሙሉ ፈርድ እንደጾምን እንዲታሰብልን ያደርጋል። በዚህ ምክንያት ነው ሸዋል ተለይቶ የተነገረን።
:
⚂ ረመዳን በሃያ ዘጠኝ ቀን ቢያልቅም እንኳን ሰውየው የተጠቀሰውን ምንዳ ማግኘቱ አይቀርም።
ኢማም ኢብኑ ሙለቅ‐ቂን ቱሕፈቱል‐ሙሕታጅ፥ ቅፅ 5፥ ገፅ 229 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «የሰውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሐዲስ በነሳኢይ 'ሐሰን' በሆነ ሰነድ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የረመዳን ወርን መጾም በዐስር ወር ይባዛል። የስድስቱ ቀን ጾም ሁለት ወር ይሆናል። ይኸውም ዓመት ሙሉ እንደመጾም ይቆጠራል።»

ይህ ሐዲስ እንደሚያመለክተው የረመዳን ወር ሙሉ [ሰላሳ ቀን] ቢሆንም ጎዶሎ [ሃያ ዘጠኝ ቀን] ቢሆንም ልዩነት እንደማይፈጠር ነው። የረመዳን ወር መነባበር የሚገኘው ቀኑን ታሳቢ በማድረግ ሳይሆን ወሩን በማሰብ መሆኑን ሐዲሱ ይጠቁመናል።»
የኢማም ኢብኑል‐ሙለቅ‐ቂን ቃል እዚህ ድረስ ነበር።
:
⚃ ረመዳንን ጾሞ ከሸዋል ወር ስድስቱን ያስከተለ ሰው ዓመቱን በሙሉ ፈርድ እንደጾመ ይቆጠራል። አመቱን ሳይጨርሰው ቢሞት እንኳን ያልደረሰበት የዓመቱ ክፍል ምንዳው ይከተለዋል።
«አካላዊ ዒባዳ ሰውየው ከሞተ በኋላ ሰው ተክቶት ሳይፈፅምለት ምንዳው በራሱ ተከትሎት መቀጠሉ የሚገርም [እንግዳ] ነገር ነው!»
ኢማም ኢብኑል‐ሙለ‐ቅ‐ቂን፥ ቅፅ 5፥ ገፅ 230
https://t.me/fiqshafiyamh
214 views01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 20:41:37 የሸዋል ጾም
=======
ከአቡ አዩብ አል‐አንሷሪይ [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን ጾሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው ይህ ዓመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል።
ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን የጾመ ከዚያም ከፊጥር በኋላ ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠራል። አንድን መልካም ስራ የሰራ ሰው በዐስር አምሳያዎቹ ይባዛለታል።» ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
:
የመልካም ስራ ምንዳው በዐስር ይባዛል። ስለዚህ የረመዳን ጾም በዐስር ሲባዛ ዐስር ወራት ይሞላል። የሸዋል ስድስት ቀናት በዐስር ሲባዙ ስድሳ ቀናት ይሆናሉ። ሁለት ወር ማለት ነው። ስለዚህ ሰውየው ሙሉ አመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።
:
የዒድ ማግስትን ማስከተል
=================
በሁለቱ ሐዲሶች መሰረት ስድስቱን ቀን ከዒዱ ቀን ማግስት ጀምሮ በመሀል ምንም ክፍተት ሳይኖር መጾም እንደሚወደድ ያመለክታሉ። ሻፊዒዮቹ ይህንን ሃሳብ ይመርጣሉ። ምክንያቱም በዚህ መንገድ መልካም ስራን በማከታተሉ ጾሙን እንዳይተወው ያግዘዋል። በሰፊው የሀገራችን ክፍል ከአባቶቻችን ጀምሮ የለመድነው አካሄድም ይህንን መሰረት ያደረገ ነው።
:
በእርግጥ ሐዲሶቹ ቀናቶቹን አከታትሎ መደርደር መልካም መሆኑን በይበልጥ የሚያመለክት ስሜት ቢኖራቸውም ቀናቶቹን አለያይቶ እያረፉ መጾም ችግር እንደሌለውም ይጠቁማሉ።
ስለዚህ ከዒዱ ዋዜማ አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ የጾመ ሰውም ሆነ አዘግይቶ ሰብስቦ በማከታተል ወይም እያረፈ ነጣጥሎ የጾመ ሰው ሱናውን አግኝቷል። ይህ ሻፊዒዮቹ፣ አሕመድ እና አብዝሀኞቹ ዑለሞች ዘንድ የተረጋገጠ ሃሳብ ነው።
:
ሐነፊዮቹ ተመራጭ ያደረጉት ሃሳብ ስድስቱን የሸዋል ቀናት መጾም ችግር የለውም [ይወደዳል ሳይሆን] የሚለውን ሃሳብ ነው። በእርግጥ ከሐነፊዮች ከፊሎቹ አከታትሎ መጾም ይጠላል ያሉበት ሁኔታም ነበር። ለዚህ ድምዳሜ ምክንያት ያደረጉት ከሸዋል ስድስት ቀን መጾም ከረመዳን ጋር እንዳይመሳሰል ወይም ተጨማሪ ግዳጅ እና ድንጋጌ እንዳይመስል መስጋታቸውን ብቻ ነው። ከኢማም ማሊክም ተመሳሳይ ሃሳብ ተሰንዝሯል። ነገርግን የዒድን ቀንን በማፍጠር ከረመዳን ጋር የመመሳሰል ስሜቱ ስለሚጠፋ ሸዋልን መጾሙ ችግር የለውም የሚለውን ሀሳብ ብዙዎቹ ሐነፊዎች መርጠውታል። "አልሂዳያ" "አልጋያ" የተሰኙ መፅሀፍቶቻቸው ይህንን አብራርተዋል።
:
በርግጥም ከላይ የጠቀስናቸው ሐዲሶች የስድስቱ የሸዋል ቀናት ጾም ተወዳጅ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ሐዲሶቹ መከራከሪያ ለመሆን ብቁ የሆኑ ግልፅ መረጃዎች ናቸው። ስለዚህ ሳንጠራጠር በዚሁ መንገድ መጓዝ እንችላለን።
:
ከሌላ ኒያ ጋር ማቆራኘት
===============
የስድስቱ ቀን ጾም ላይ ቀዳእን ጨምሮ በመነየት መጾም ይፈቀዳል። ሰውየው የሁለቱንም ምንዳ ያገኛል። ኢማም ሲዩጢይ [ረዐ] 'አል‐አሽባህ ወን‐ነዟኢር' በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐ "ለምሳሌ በዐረፋ ቀን ከዐረፋ ጾም ጋር ቀዷእን፣ የስለት ጾምን፣ ከፋራን… በአንድ ላይ ነይቶ መጾም አስመልክቶ እንደሚፈቀድና ምንዳውም እንደሚገኝ አል‐ባሪዚይ ፈትዋ ሰጥተዋል። እንደውም እለቶቹን ልቅ በሆነ የጾም ኒያ ቢያሳልፈውም የስድስቱን የሸዋል ጾም ምንዳ ያገኛል ብለዋል። እርሳቸው የሸዋልን ጾም በተሒይ‐የቱል‐መስጂድ ሶላት መስለውታል።"
ማንኛውም ሰው መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዐና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሶላት ቢሰግድ ተሒያን ቢነይትም ባይነይትም የተሒያውን ምንዳ እንደማያጣው፣ ፈርድ ወይም ሱና ሲሰግድ አብሮ ተሒያን መነየት እንደሚፈቀድለት ሁሉ የሸዋል ጾምም በዚሁ አኳያ መታየት አለበት እያሉ ነው።
ምክንያቱም ተሒይ‐የቱል መስጂድ ያስፈለገው ሰውየው መስጂድ ሲገባ ከመቀመጡ በፊት ሶላት እንዲሰግድ ማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ በማንኛውም ሶላት ይህንን ማሳካት ስለሚችል ተሒያውን ያገኘዋል።
የተሒይ‐የቱል መስጂድ ድንጋጌን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "እያንዳንዳችሁ መስጂድ ስትገቡ ሁለት ረከዐ ሳትሰግዱ አትቀመጡ።"
በሸዋል ወር ያሉት የስድስት ቀናት ጾምንም አል‐ባሪዚይ እና በርካታ መሰሎቻቸው እንደዚሁ ተመልክተውታል።
በዚህ መሰረት ሱና ጾም በፈርድ ውስጥ መካተት እንደሚችል ዐሊሞች [በተለይ ሻፊዒዮች] ጠቁመዋል። ነገርግን ፈርድ ጾም በሱና ጾም ኒያ ውስጥ መካተት አይችልም።
:
ስለዚህ ሴቶች በረመዳን በወር አበባ ምክንያት ያመለጣቸውን ከሸዋል ጾም ጋር በአንድ ላይ በመነየት ቀዳቸውን መክፈል ይችላሉ ማለት ነው።
ነገርግን በቅድሚያ ቀዷቸውን ቢከፍሉ ከዚያም ሸዋል ሳይወጣባቸው የሸዋልን ጾም ቢጾሙ፤ ወይም በተቃራኒው መጀመሪያ የሸዋል ስድስቱን ጾም አስቀድመው ቢጾሙ ከዚያም ቀዳቸውን አስከትለው ቢከፍሉ የተሻለ ነው። ምክንያቱም ደርቦ በመጾም ምንዳ ያገኛል ማለት ነጣጥሎ በመጾም የሚገኘውን የተሟላ ምንዳ ያገኛል ማለት አይደለም። ነጣጥሎ በተለያዩ ጊዜያት ኒያውን ሳያደራርብ የጾመ ሰው ኒያዎችን አደራርቦ ከጾመ ሰው የበለጠ ምንዳ አለው።
:
ኢማም ረምሊይ [ረዐ] እንዲህ ይላሉ: — "በሸዋል ወር ቀዳእን፣ ስለትን እና ሌሎች ጾሞችን የጾመ ሰው የሸዋል ሱና ጾምን ምንዳ ያገኛል። ይህ አባቴ [ረሒ] አል‐ባሪዚን፣ አል‐አስፈዊን፣ አን‐ናሺሪን፣ አል‐ፈቂህ ቢን ሷሊሕ አል‐ሐድረሚን እና ሌሎችንም ዋቢ በማድረግ የሰጡት ፈትዋ ነው። ነገርግን ረመዳንን በስድስት የሸዋል ቀናት ጾም አስከትሉት የተባለበትን የተሟላ ምንዳ አያገኝም።"
:
የስድስቱ ቀናት የሸዋል ጾም በፈርዱ ላይ የተከሰተን ጉድለት ይሞላል። የረመዳን ጾም ተቀባይነት ማግኘቱን ይጠቁማል። ምክንያቱም መልካም ስራ ተቀባይነት ማግኘቱን ከሚጠቁሙ ምልክቶች መሀል አንዱ ወዲያው መልካም ስራን ማስከተል ነው። ሰውየው አላህን ማምለክ እንደማይሰላች ማረጋገጫም ይሆናል።
የሸዋል ጾምም ሆነ የማንኛውም ሱና ጾምን ኒያ በሌሊት ብቻም ሳይሆን እስከ ዙህር ባለው ሰዓት ማስገኘት ይቻላል።
:
በመልካም ነገር ላይ እንተጋገዝ። እንዘያየር። በሸዋል ጾም አደራ እንባባል።
መልካም ዒድ!
http://t.me/fiqshafiyamh
741 viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:05:02
በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው የመፃፍ ሃሳብ ነበረኝ። ጊዜም ሂማም አጠረኝ እና አልተሳካልኝም።
ጁሙዐ እና ዒድ ከገጠመ አንዱ ሌላውን አያስቀርም። ዒዱም ጁሙዓውም ይሰገዳል። በጠንካራ ድንጋጌ ፈርዱል‐ዐይን የሆነውን ጁሙዓን በሱናነት የተደነገገው የዒድ ሶላት አያስቀረውም። ወይም ፉቀሃእ እንደሚሉት:‐
«الأقوى لا يسقطه الأضعف»
ይህ የሻፊዒያ፣ የአሕናፍ፣ የማሊኪያ ፈትዋ የሚሰጥበት አቋም ነው። በሐንበሊያም አንድ ሃሳብ ሆኖ የቀረበ ነው። የአዝሃር ፈትዋም የምትመለከቱት ነው።
እንግዳ ፈትዋዎች "ፈውዳን" (ስርዓት አልበኝነትን) ከማባባስ ውጪ የሚፈጥሩት መልካም ነገር የለም!
ዒዳችን በጁሙዐ ሶላትም ይደምቃል!
እንኳን አደረሳችሁ!
1.0K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 05:19:34 በዒድ ቀን መስራት ያለብንን ❿ ነገሮች እናስታውስ: ‐
❶ ዘካቱል‐ፊጥር፤
❷ ድምፅን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረግ፤
❸ ገላ መታጠብ፤ አዲስ ወይም ምርጥ ልብሳችንን መልበስ፤ ሽቶ መቀባት፤ ጥርስን መፋቅ፤
❹ ለሶላት ከመውጣታችን በፊት ተምር ወይም ሌላ ነገር መብላት፤
❺ ወደ ዒድ ሶላት ሜዳ ተሰብስበን በህብረት ተክቢራ ደምቀን መሄድ፤
❻ ሶላታችንን መስገድ፤ ኹጥባ ማዳመጥ፤
❼ በዜማ እና በሌላ ጨዋታ ዒዱን ማድመቅ፤
❽ የሄዱበትን መንገድ ቀይሮ መመለስ፤
❾ በዒዱ ቀን ዓቅመ ደካማዎችን መዘየር፤ በደስታ እንዲያሳልፉት ማገዝ፤
❿ በዚህ የደስታ ሰዓት እንኳን በግፍ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በተለይም ፊሊስጢኖችን በዱዓ ማሰብ።
:
በድል ጨረቃ ታጅበን፣ በኢስላም ልዕልና ደምቀን፣ በሀገራችን ሰላም ተውበን፣ በአንድነት እና በፍቅር ከአመት አመት ያድርሰን!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
http://t.me/fiqshafiyamh
1.1K views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:19:37 የዒድ ሌሊት እና የጁሙዐ ሌሊት ከተጋጠሙ የየትኛውን ሌሊት ዚክር እናስቀድም? የዒዱን ዚክር (ተክቢራ) ወይስ የጁሙዓውን ዚክር (ሶለዋት፣ ከህፍ…)
:
ሸይኽ ዐሊ አሽ‐ሸብራሙሊሲይ እንዲህ ይላሉ: ‐
«የዒድ ሌሊት ከጁሙዓ ሌሊት ጋር ከገጠመ የዒድ ተክቢራውን፣ ከሱረቱል‐ከህፍ፣ ከሶላት ዐለነቢው ጋር አቆራኝቶ ይፈፅመዋል።
ሌሊቱን በተለያዩ ሰዓት እነዚህን ሦስቶቹን በማከናወን ይጨርሰዋል።
በራሱ ምርጫ የፈለገውን ያስቀድም።
ነገርግን ተክቢራውን ማስቀደም መልካም ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱም ተክቢራ የእለቱ ዓርማ ነው።»

«ሓሺየቱ አሽ‐ሸርቃዊ ዐለት‐ተሕሪር» ላይ እንደተጠቀሰው ከሆነ «ሌሊቱን ሙሉ ለሙሉ በተክቢራ ማሳለፍ ይበልጣል።»
:
አል‐ቀውሉል‐ሙፊድ ፊ አሕካሚል‐ዒድ
2.1K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ