Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው የመፃፍ ሃሳብ ነበረኝ። ጊዜም ሂማም አጠረኝ እና አልተሳካልኝም። ጁሙዐ እ | Tofik Bahiru

በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው የመፃፍ ሃሳብ ነበረኝ። ጊዜም ሂማም አጠረኝ እና አልተሳካልኝም።
ጁሙዐ እና ዒድ ከገጠመ አንዱ ሌላውን አያስቀርም። ዒዱም ጁሙዓውም ይሰገዳል። በጠንካራ ድንጋጌ ፈርዱል‐ዐይን የሆነውን ጁሙዓን በሱናነት የተደነገገው የዒድ ሶላት አያስቀረውም። ወይም ፉቀሃእ እንደሚሉት:‐
«الأقوى لا يسقطه الأضعف»
ይህ የሻፊዒያ፣ የአሕናፍ፣ የማሊኪያ ፈትዋ የሚሰጥበት አቋም ነው። በሐንበሊያም አንድ ሃሳብ ሆኖ የቀረበ ነው። የአዝሃር ፈትዋም የምትመለከቱት ነው።
እንግዳ ፈትዋዎች "ፈውዳን" (ስርዓት አልበኝነትን) ከማባባስ ውጪ የሚፈጥሩት መልካም ነገር የለም!
ዒዳችን በጁሙዐ ሶላትም ይደምቃል!
እንኳን አደረሳችሁ!