2022-07-11 19:23:13
ተክቢራ በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ
===================
«በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት (ከዒዱል‐አድሓ እለት ቀጥለው ባሉት ሦስት ቀናት) የሚደረገው ተክቢራ የግድ ከፈርድ ሶላት በኋላ መሆን አይጠበቅበትም። [በመርሳት ወይም በሌላ ምክንያት] ቢተወውም በተመቸው ጊዜ ሊያደርገው ይችላል።»
ኢማም ነወዊይ "ሚንሃጅ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት ሶላት ቀዷእ ሲያወጣ፣ መደበኛ ሱና ሶላቶችን ሲጨርስ፣ ማንኛውም ዓይነት ሱና ሲሰግድ አስከትሎ ተክቢራ ማድረግ ይወደዳል የሚለው [የኢማም ሻፊዒይ] ሀሳብ እጅግ የተሻለ (አዝሀር) የሆነው ሃሳብ ነው።»
ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይሰሚይ "ቱሕፋ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዳሰፈሩት: ‐ «ለምሳሌ: ‐ ከዱሓ ሶላት፣ ከዒድ ሶላት እና ከመሳሰሉት ሶላቶች በኋላ፣ ልቅ ከሆኑ ሱና ሶላቶች በኋላ፣ እንደውም ከጀናዛ ሶላት በኋላ ሳይቀር ተክቢራ ይደረጋል። ምክንያቱም ተክቢራ የጊዜው ዓርማ ነው።»
"ሙኽተሶሩ ባፈድል" በበኩሏ እንዲህ ትላለች: ‐
«ከሐጀኛ ውጪ ያለ ሰው ሁሉ ከፈርድም ሆነ ከሱና ሶላት በኋላ ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱ ትኩስም ይሁን ቀዷእ ወይም የጀናዛ ሶላት ምንም ልዩነት የለም። ተክቢራውን ከረሳ ሲያስታውስ ያድርገው።»
የዒድ ተክቢራ በህብረት ብቻ የሚደረግ የሚመስላቸውም ሰዎች ይኖራሉ። ነገርግን ስህተት ነው። ተክቢራው በግልም በጀመዓም እንደሚደረግ ይታወስ።
:
ዒድ ይደጋግመን። በጤናና በሰላም አመት ከአመት ያድርሰን ያድርሳችሁ።
ዒድ ሙባረክ!
https://t.me/fiqshafiyamh
1.3K viewsedited 16:23