2023-04-02 07:40:12
ረ͟መ͟ዳ͟ን͟ 1͟1͟ ላ͟ይ͟ ነ͟ን͟
የመግፊራው ክፍል መጀመሪያ ላይ!
በመግፊራው ሊያከናንበን ተሰናድቶ እየተቀበለን ነው። የአላህን ምህረት ለማግኘት ምን እናድርግ?…
ለዛሬ ኢስቲግፋርን በጭንቅላታችን፣ በቀልባችን እና በልሳናችን ላይ እናድርግ!
ከኢስቲግፋሮች አለቃ (ሰይ‐ዪዱል‐ኢስቲግፋር) እንጀምር!…
:
«اللهم أنت ربي لا إله إلا أنت، خلقتني وأنا عبدك، وأنا على عهدك ما استطعت. أعوذ بك من شر ما صنعت. أبوء لك بنعمتك علي وأبوء بذنبي فاغفر لي ذنوبي. فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت»
«አላሁም‐መ አንተ ረብ‐ቢ ላ ኢላሀ ኢል‐ላ አንተ። ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መስተጦዕቱ። ከሰራሁት ነገር ክፋት ባንተ እጠበቃለሁ። አቡኡ ቢኒዕመቲከ ዐለይ‐የ። ወአቡኡ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ ዙኑቢ። ፈኢን‐ነሁ ላ የግፊሩዝ‐ዙኑበ ኢል‐ላ አንተ።»
:
ትርጉም: ‐ አላህ ሆይ አንተ ጌታዬ ነህ። ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። ፈጥረኸኛል። እኔም ያንተ ባርያ ነኝ። እኔ በቻልኩት መጠን ላንተ በገባሁት ቃልኪዳን እና በገባህልኝ ቃል በመተማመን ላይ ፅኑ ነኝ።
የዋልክልኝን ፀጋ እለፈልፋለሁ (አምናለሁ)። ኃጢኣቴንም እለፈልፋለሁ። ጌታዬ ሆይ ኃጢኣቴን ማረኝ። ከአንተ በስተቀር ኃጢኣትን የሚምር የለምና።
:
በሐዲስ እንደተጠቀሰው: ‐ «ይህንን ኢስቲግፋር በውስጡ ያለውን መልእክት ከማመን ጋር በጧት ብሎት ከማምሸቱ በፊት ከሞተ የጀነት ሰው ይሆናል። በሌሊት ይህንን ብሎ ከመንጋቱ በፊት ከሞተም የጀነት ሰው ይሆናል።»
ቡኻሪ፣ ቲርሚዚ እና ነሳኢ ዘግበውታል።
https://t.me/fiqshafiyamh
1.1K viewsedited 04:40