Get Mystery Box with random crypto!

ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ዓቢድ በጀነት ዛፍ ስር እንጂ እረፍት የለው | Tofik Bahiru

ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዓቢድ በጀነት ዛፍ ስር እንጂ እረፍት የለውም። ሙሒብ ጭማሪ በሚገኝበት ቀን [በቂያማ] እንጂ እርጋታ የለውም።»
:
ኢላሂ!
በዲንህ የምትደሰት ነፍስ ስጠን።
በዚክር የሚረካ ቀልብ ስጠን።
አስገራሚ ፍጥረትህን አይቶ የሚያስተነትን ዐይን ስጠን።
በመንገድህ መስዋኢት መሆንን ስጠን።
ነቢያትህን እና ወልዮችህን በጀነት ውስጥ ማግኘት ስጠን።
መልካም የእረፍት ቀን!