Get Mystery Box with random crypto!

ሸይኽ አቡል‐ዐባስ አል‐ሙርሲይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አንድ የአላህ ባርያ ጊዜው | Tofik Bahiru

ሸይኽ አቡል‐ዐባስ አል‐ሙርሲይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አንድ የአላህ ባርያ ጊዜው ለአራት የተከፈለ ነው: ‐
⚀ አንደኛው የአምልኮ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ልግስና ማየት ይገባል።
⚁ ሁለተኛው የኃጢኣት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ተውበትን ማሳመር ይገባል።
⚂ ሦስተኛው የፀጋ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ተገቢው ነገር ምስጋና ማድረስ ነው።
⚃ አራተኛው ጊዜ የመከራ ነው። ይህ ትእግስትህን ይሻል።
እነዚህን አደቦች በሙሉ የጠበቀ ሰው የተሟላ ክብር እና በምርጦችም ሆነ ተርታዎች ዘንድ የመልካምነት ደረጃን ይጎናፀፋል።»