Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethababora
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-08 21:46:29 " በእስር ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች በሙሉ ከእስር በሚፈቱበት አግባብ ላይ ስምምነት ተደርሷል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ዛሬ ከፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽነሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረግ  መቻሉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራሮች ሼይኽ ሁሴን ጨምሮ የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እንዲሁም ከኦሮሚያ መጅሊስ ሼይኽ ሚስባን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል  ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና ከፍተኛ የፀጥታ ሐይሉ አመራሮች ተካፍለዋል።

በውይይቱ ላይ በሸገር ከተማ የፈረሱ መስጂዶችን ተከትሎ በሁለት ጁምዓዎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተወሰዱት ኢ ሰብዓዊ እና ከልክ ያለፉ የኃይል እርምጃዎች ተቀባይነት የሌላቸው እና ህዝበ ሙስሊሙን እጅግ ያሳዘነ መሆኑ ተገልፆል።

ሀገር ወዳድ እና ሰላማዊ ለሆነው ህዝበ ሙስሊም ህጋዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በማቅረቡ በምላሹ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደው የኃይል እርምጃ  በምንም መመዘኛ የሚገባው እንዳልነበር እና ጥፋት እንደሆነ ለፀጥታ አመራሮቹ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በፀጥታ ኃይሉ በኩልም የሙስሊሙን ህጋዊ ጥያቄ ሽፋን በማድረግ የራሳቸው አጀንዳ ለማራመድ የሞከሩ ኃይሎች መኖራቸውን መረጃ እንዳላቸው በማንሳት የነበራቸውን ስጋት ገልፀዋል።

በውይይቱ መቋጫ ላይ በሁለቱ ጁምዓዎች በተወሰደው የኃይል እርምጃ በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች በሙሉ ከእስር በሚፈቱበት አግባብ ላይ ከስምምነት ላይ መድረስ መቻሉ ተገልጿል።

ከህግ አግባብ ውጪ የኃይል እርምጃ የወሰዱ የፀጥታ ሀይሉ አባላትም በህግ  አግባብ እንዲጠየቁ ኮሚቴ ተዋቅሮ የማጣራቱ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ህዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸው ህጋዊ ጥያቄዎቹ በኦሮሚያ ክልል መንግስት በኩል መፍትሄ ለመስጠት ቃል በመገባቱ እና ይህም መፍትሄ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው ጨዋነቱ በትዕግስት በመጠበቅ ከመሪ ድርጅቱ መጅሊሱ ጎን በመቆም በተቋሙ የተሰጡትን መመሪያ እና የመፍትሄ አቅጣጫ በመተግበር እና በዱዓ በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ከፀጥታ አመራሩ ጋር የተደረገው ፍሬያማ ውይይት በመግባባት የተቋጨ ሲሆን በቀጣይ ባሉ ጁምዓዎች ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከር እና በዱዓ በመበርታት መደበኛ የጁምዓ ሰላቱን ብቻ እንዲያከናውን ጥሪ ቀርቧል።

በሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ አቅጣጫ የተቀመጠለት በመሆኑ በሁሉም መሳጂዶች ከቁኑት ዱዓ ውጪ  የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ባለመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደ ታዣዥነቱን በማሳየት የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ ብቻ መመለስ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።

Via ኡስታዝ አቡበከር አህመድ



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
77 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:57:59 በክቡር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱህፋ የሚመራዉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር ዉይይት ካደረጉ ቡኀላ የተሰጠ መግለጫና ማብራሪያ:-
••••••••••••••••••••••••••••••
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱህፋ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ሸመልስ አብዲሳ ጽ/ቤት በመገኘት በሸገር ከተማ እየተከናወነ ባለው የመስጊድ ፈረሳ ጉዳይ ላይ አምስት ሰዓታት የፈጀ ዉይይት አድርገናል።በዉይይቱ ላይ ከኦሮሚያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት የተገኙ እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራር አባላት  ላይ ተገኝተዋል።

በዉይይቱ ላይ የልዑኩ አባላት በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዉይይቱ ላይ በሙስሊም ተወካዮች ከተነሱት ነጥቦች መካከል፡-

• በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የመስጂድ መሬትን በህጋዊ መንገድ የማግኘትና የመሥራት እንዲሁም ለተሠሩት መስጂዶች ካርታና የማስፋፊያ መሬት የማግኘት ሁኔታ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ በዝርዝር ተብራርተዋል።
• የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፕላን ዉጭ ተሠርተዋል ያላቸውን መስጂዶች ለማፍረስ ሲነሳ የሚመለከተውን የእስልምና ጉዳዮች አካላትን እንዳለወያየ፥እንዲሁም በጉዳዩ ላይ እንወያይ በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለማወያየት አለመሞከሩ ተገቢ አለመሆኑ በቅሬታ መልክ ቀርቧል።
• ሕዝበ ሙስሊሙ የሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያየዘ በተፈጠሩት ሁኔታዎች እጅጉን መጎዳቱንና ማዘኑን በማብራራት ተገቢውን ካሳና የሞራል ህክምና እንደሚያስፈልገው ተጠቅሷል፥

• የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ሆነ ሕዝበ ሙስሊሙ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ከተሞችን ለማዘመን የሚደረገውን እቅድን፥ ልማትንም ሆነ እድገትን የሚደገፍው እንጂ የሚቃወመው እንዳልሆነ ሆኖም እቅዱ በቂ የእምነት ተቋማትን ለአማኞች ማቅረብንና ሰው ተኮር መሆን እንደሚገባው ተብራርቷል።
•  በሸገር ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ያለ ፕላንና ሕጋዊነት ተሠርተዋል በሚል የፈረሱት 22(ሃያ ሁለት) መስጊዶች መሆናቸውን በመጥቀስ ለሕዝበ ሙስሊሙ የመስጊድ ጥያቄዎች በሙሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚገባ፥
• ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ከጅምሩ በመነጋገር መፍታት እየተቻለ እስከ ትናንትናው እለት ድረስ መሰል ዉይይት ሳይደረግ መስጂዶችን ወደ ማፍረስ በመገባቱ በመንግስትና በሕዝብ መካከል ቅሬታ ፈጥሮ ጉዳዩ እስከ ነፍስ መጥፋት ማምራቱ እጅግ የሚያሳዝን መሆኑን፥
• የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ ሙስሊሞችን መግደላቸውና ማቁሰላቸው ተገቢ አለመሆኑን፥እንዲሁም ንጹሃን ላይ በመተኮስ የገደሉና ያቆሰሉ አካለት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ።
• እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ በርካታ ችግሮች በዝርዝር ተብራርተዋል።

በክልሉ ፕሬዝዳንት በኩል የተጠቀሱት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1.  ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ዉይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን።

2. በተፈጠረው ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡት ሙስሊሞች ማዘናቸውን።

3. የሸገር ከተማ የሃይማኖትን እሴትን መሠረት አድረጎ እንደሚገነባ እና የእሰልምናን ጨምሮ የሌሎችም ቤተእምነቶችም ተቋማት በብዛት በሸገር ከተማ ፕላን ዉስጥ እንደተካተቱ።

4. አስፈላጊውን የቤተእምነት መሥሪያ መሬቶችን በፕላኑ መሠረት ለምዕመኑ እንደሚሰጥና በቆርቆሮ ሳይሆን የከተማዋን ፕላን የሚመጥን በርካታ ዘመናዊ መስጊዶች በከተማው እንዲሰሩ እንደሚፈልጉ።

5. በሸገር ከተማ ላይ በሀገር ደረጃ  ሊጠቀስ የሚችል ትልቅና ዘመናዊ መስጂድና ለሌሎች እምነት ተቋማት መሥሪያ ቦታ እንደሚሰጥ።

6. በሸገር ከተማ ለኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚሆን መሬት እንደሚሰጥ።

7. ሸገር ከተማ ከ20 እስክ 30 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያላት፥ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካድባት ከተማ ሆኖ ለመግንባት ሕግ ወጥ ግንባታን መከላከል፥የተገነቡትን ማፍረስ እንደሚቀጥል ለዚህ ሂደት የእምነት ተቋማት ተባባሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን።

8. አዲሱ የሸገር ከተማ ፕላን ወደ ተግባር እስኪገባ ድረስ ሙሉ ለሙሉ መኖሪያ ቤቶች ባልፈረሱባቸው አከባቢዎች ለሚኖሩ ሙስሊሞች በጊዜያዊነት የሚሰግዱባቸው መስጊዶች የኦሮሚያ ክልል መጅሊስና የሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመጋገር መስጂድ መሥሪያ ቦታ እንዲያዘጋጁ።

9. የሸገር ከተማ ማስተር ፕላን በመጪው ሀምሌ ወር ወደ ተግባር ማዋል ከመጀመሩ በፊት በማስተር ፕላኑ ለእምነት ተቋማት የተዘጋጀውን ስፍራዎችን የሙስሊም ተወካዮች ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ ቀድመው ፕላኑን እንዲመለከቱና እንዲያረጋግጡ።

10. በሸገር ከተማ ሕዝቡ ሙስሊሙ ያቀረባቸውና የሚያቀርባቸው የመስጊድ ጥያቄዎች በፕላኑ መሠረት ምላሽ እንደሚሰጥ።

11. ሸገር ከተማን ጨምሮ በመላው ኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም ሲደረግ  እንደነበረው የእምነት ተቋማት እና የመቃብር ሥፍራ መስጠት እንደሚቀጥል።

12. በሸገር ከተማ ዉስጥ ካሉት ስምንት መቶ(800) የሁሉም እምነት ተቋማት መካከል 656(ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት) የሚሆኑት ከፕላን ዉጭ የተሠሩ በመሆናቸው እነዚህን የሚገነባውን ከተማ ፕላን የማይመጡትን የተለያዩ ቤተእምነቶችን ወደ በሕጋዊና ከተማውን በሚመጥኑ ተቋማት ለመተካት የሚደረገውን ሂደት የኦሮሚያ ክልል መጅሊስም ባለበት የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አቅሙን በማጠናከር በዉይይት የእምነት ተቋማቱ ራሳቸው መፍረስ ያለባቸውን እንዲያፈርሱ እንጂ ከአሁን በኋላ መንግስት በራሱ ማፍረስ እንደሚያቆም።

የእስረኞችን መፈታትና የተጎዱትን ሙስሊሞች በተመለከተ


1. ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የታሠሩትን ሙስሊሞችን መፈታትን አስመልክቶ ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ከፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች ጋር ዉይይት ይደረጋል።ያለምንም ልዩነት የታሠሩት ሙስሊሞች በጠቅላላው እንደሚፈቱ እንጠብቃለን።

2. ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአንዋር እና ኑር መስጂድ በሸገር ከተማ የፈረሱትን መስጂዶችን በመቃወም ላይ እያሉ የተገደሉ ሙስሊሞችን ቤተሰቦችን አላህ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ለሟቾች ደግሞ አላህ የሸሂደትነት(ሰማዕትነትን) ደረጃ እንዲለግሳቸው እየተማጸንን በሸገር ከተማ በፈረሱት መስጂዶች ምትክ ከሚሠሩት መስጂዶች መካከል አንዱ «የሸሒዶች መስጂድ» ተብሎ እነርሱን ለማስታወስ ይሰየማል። በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥም የሟቾችም ስም ዝርዝር በጉልህ በሚታይ መልኩ ይጻፋል።

3. ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከሸገር ከተማ ከፈረሱት መስጂዶች ጋር በተያየዘ በተፈጠሩት ሂደቶች  ጉዳት የደረሰባቸውን ሙስሊሞችን ሕዝበ ሙስሊሙ በመደገፍ ከጎናቸው በመሆን እንዲያግዝ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

ሰኔ 01 ቀን 2015



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
99 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 14:28:33
138 views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 14:28:15 ስምምነት የተደረሰባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ለማስፈጸም ሁላችንም ተግተን እንስራ!
—————————

በሸገር ሲቲ የመስጊዶች ፈረሳ የፈጠረውን ቀውስ ለመቆጣጠር በእስልምና ጉዳዮች መሪነት ብዙ ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን ከክልል መንግስቱ እና ከሌሎችም የመንግስት ኃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተደረገው ውይይት በፈረሳውና አስከትሎ በተፈጠረው የተቃውሞ ሂደት በሙስሊሙ ላይ የደረሰው በደል በስፋት ተዘርዝሮ የቀረበ ሲሆን በመንግስት ኃላፊዎች በኩልም የተፈጸመው ተግባር ስህተት መሆኑ ታምኖበት ችግሩን ለመፍታት የታሰቡ እርምጃዎች በውይይቱ ሂደት ወደፊት ወጥተዋል።

በዚህም የመስጊድ ፈረሳው በአስቸኳይ እንደሚቆምና ከፕላን ውጭ ያሉ መስጊዶች ጉዳይ ከመጅሊሱ ጋር በመሆን እንደሚታይ፣ የፊታችን ሀምሌ በሚጸድቀው የከተማዋ ፕላን ላይ መጅሊሱን በማማከር ደረጃቸውን የጠበቁ መስጊዶች እንደሚሠሩ፣ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲና ግዙፍ ማዕከላዊ መስጊድን ጨምሮ መንፈሳዊ ማዕከላት እንደሚኖሩ፣ ነዋሪ ባለባቸው አካባቢዎችም ጊዜያዊ የመስገጃ ቦታዎች እንደሚዘጋጁ ከመንግስት በኩል ቃል ተገብቷል። በተቃውሞው ሂደት የታሰሩ ሰዎች ጉዳይም ከዛሬ ጀምሮ ከጸጥታ አካላት ጋር በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች እንደሚታይ ስምምነት ላይ ተደርሷል። (ከመንግስት ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን የመፍትሄ አማራጮች በዝርዝር በመጅሊሱ መግለጫ ማግኘት ይቻላል።)

በሂደቱ የተፈጠረው ቀውስ ሙስሊሙን ለበርካታ ህመም የዳረገ እንደመሆኑ ለጉዳዩ አስቸኳይ እልባት ለማግኘት መንቀሳቀስ የግድ ነበር። ህዝበ ሙስሊሙም የተባበረ ድምጹን በማሰማት በሸሂዶቹ ደም የከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አይደለም። አሁን ላይ ደግሞ ሁላችንም ወደመፍትሄው አፈጻጸም በማተኮር የሸሂድና የተጎጂ ቤተሰቦችን መንከባከብ፣ በእስር ላይ ያሉ ወንድም እህቶቻችንን ማስፈታት እና በመንግስት በኩል ቃል የተገቡትን ነጥቦች ተከታትሎ ማስፈጸሙ ላይ ልንረባረብ እንደሚገባን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ህዝበ ሙስሊሙ በዘወትር ጨዋነቱ ይህንን የመፍትሄ ክትትል ሂደት ከሚያስተጓጉሉ አካሄዶች ተቆጥቦ ነገሮች ወደነበሩበት መረጋጋት ይመለሱ ዘንድ ጁሙዓን የመሳሰሉ የስብስብ አጋጣሚዎቻችን መሪ ድርጅታችን ባስቀመጠው አቅጣጫ ብቻ እንዲካሄዱ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን። በግልም ሆነ በቡድን በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች የመገናኛ መንገዶች የሚኖሩን ሂደቶች በተቻለ መጠን መፍትሄውን ተከታትሎ የማስፈጸም መንፈስ ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ እና ሙስሊሙን ወዳልሆነ አቅጣጫ መምራት ለሚፈልጉ አካላት በር የማይከፍት አካሄድ እንድንከተል ጥሪ እናደርጋለን። የመሪ ተቋማችንን ትእዛዝ እና የትግበራ አቅጣጫ መከተል በዚህ መሰል የቀውስ ወቅቶች እጅግ አንገብጋቢ እና ብቸኛ አማራጭ መሆኑንም ለማስታወስ እንወዳለን።

በሌላ በኩል በመንግስት ኃላፊዎች በኩል ቃል የተገቡትን የመፍትሄ ሀሳቦች ከዳር ማድረስ ችግሩ ይፈታ ዘንድ ቁልፍ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን የመንግስት የጸጥታ ኃላፊዎች ይህንኑ ያገናዘበ አካሄድ ሊሄዱ ይገባል። የሰላም ቀንዲል በሆነው የህዝበ ሙስሊሙ መስጊዶች ከእንግዲህ ወዲህ አንድም ጠብታ ደም ሊፈስ አይገባምና ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ጉዳት ከሚያደርስ አካሄድ ፈጽመው እንዲቆጠቡ በጥብቅ ልናሳስብ እንወዳለን።

ለመስጊድ ክብር ሲሉ ደማቸውን ላፈሰሱት ሸሂዶቻችን መታወሻ በሸገር ሲቲ በሚገነባው "የሸሂዶች መስጊድ" ስያሜ ሁሌም በዱዓ እንድናስታውሳቸው ያበቃን ዘንድ አላህን እንለምናለን! በቀጣይ ወቅቶች ሁላችንም ከሸሂድና ተጎጂ ቤተሰቦች ጎን በመቆም ጉዳታቸው ይጠግግ ዘንድ እስልምና ጉዳዮች ይፋ ባደረጋቸው የባንክ ሂሳቦች እርዳታ በማሰባሰብ እና በመንከባከብ በኩል እንበራታ! አላህ ለዲኑ የተከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ይቀበል! አገራችንንም ሰላም ያድርግልን! አሚን ያረበል ዓለሚን!

Ustaz abubeker ahmed
141 views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 13:34:58 ከወሳኝ ጥቅል የሆነ ነቢያዊ ዱዓዎች ውስጥ!

ከአብደላህ ቢን መስዑድ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር፦


﴿اللَّهُمَّ إنِّي أسْأَلُكَ الهُدى والتُّقى، والعَفافَ والغِنى. وفي روايةٍ: والعِفَّةَ﴾

“አላህ ሆይ! መቀናትን፣ ጥንቅቁነትን፣ ጥብቅነትንና ራስን መቻልን እጠይቅሃለው።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 6761



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
143 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 11:31:18 ትግላችን ይቀጥላል። ወንጀሎች ለህግ እንዲቀርቡ ፤ በንፁሀን ወንድሞቻችን ላይ ቃታ የሳቡ እጆች በፍትህ አደባባይ እስኪቀርቡ ድረስ መሪ ድርጅታችን በሚሰጠን አቅጣጫ እንታገላለን።

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ።
163 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 11:27:21 «ደግሜ ደጋግሜ ልጆቻችንን አላህ ሸሂድነታቸውን ይቀበላቸው። የሚገነቡት መስጅዶች በሸሂዶች ስም ይሆናል።»
ሸህ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
158 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 10:42:02
የፌደራል መጅሊስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል።

በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ ልዑክ  ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የኦሮሚያ ክልል የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከቀኑ 9:00 እስክ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ አምስት ሰዓታት የፈጀ ሰፊ ዉይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ስለሆነም መጅሊሱ በዛሬው ዕለት መግለጫ ይሰጣል።
164 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 06:43:07
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 19 #ዙልቀዓዳ 1444 ሂ
168 views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 06:21:51 "አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ)

"ሁለት የብርዳማ ወቅት ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ገባ" ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
- ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
169 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ