Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethababora
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-29 21:55:41 በጉንችሬ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ አንዲደረግ ልዑኩ አሳሰበ ።

ሚያዚያ 21/15

በኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት መሪነት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ አሰተዳደር   በሙስሊም ተማሪዎች  ከኒቃብ አለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳ የቆየ ችግር በዘላቂነት ከሚመለከታቸው  ጋር ተነጋግሮ  ለመፍታት  ልዑካን ቡድን ልኳል።

  በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው በተከሰው ችግር ምክንያት   ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን መነሻ በማድረግ ሶስት አባላት ያሉት  ልዑኩ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ና ሕዝቦች  ክልላዊ መንግስት ከሚመለከታቸው  የቢሮ ኃላፊዎችወደ ቦታው ለመሄድ መንግስት አስፈላጊውን ሁኔታዎች እንዲያመቻችና  ከክልሉ የሃይማኖት  ተቋማት አባቶች  ጋር  ለሁለት ቀናት ጥልቅ ውይይት አድርጓል ።

በተደረገው ውይይት  መሠረት ችግሩ የነቃብ አለባበስ ብቻ ሳይሆን  ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ  ይዘት ያለውና በአካባቢው  ተፈጥሮ በነበረው  የሠላም  ችግር በሰዎች ና በንብረት ላይ ሰፊ ጉዳት በማስከተሉ  ችግሩን በዘላቂነት  መፈታት  እንዳለበት  ቡድኑ ተገንዝቧል።

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ተፈጥሮ የነበረውን የሠላም ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ውይይት ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት እስልምና  ጉዳዮች  ከፍተኛ ምክር ቤት ና የክልሉ የሃይማኖት  ተቋማት ጉባዔ  ከሚመለከታቸው  የመንግስት አካል ጋር በመነጋገር በቀጣይ ሳምንታት  በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ  ሕዝባዊ የውይይት መድረክ  እንዲያዘጋጁ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ከስምምነት ላይ  ደርሰዋል።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
125 views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 16:40:43 ለልጆች የሚደረግ መለኮታዊ ጥበቃ!

ከኢብኑ አባስ (رضي ﷲ عنهما) ተይዞ:  እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ለሀሰንና ለሁሰይን እንዲህ እያሉ ጥበቃ ያደርጉላቸው ነበር፦

﴿أُعِيذُكُمَا بِكَلِمَاتِ اللَّهِ التَّامَّةِ مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ  وَهَامَّةٍ ، وَمِنْ كُلِّ عَيْنٍ  لَامَّةٍ﴾

“ምሉዕና ፍፁም በሆኑት የአላህ ቃላት ከሰይጣናት ሁሉና ከእኩይ ሰው (ተንኮል) እንዲሁም ጎጅ ከሆነ ዓይን ሁሉ እጠብቃችኃለሁ፡፡”

ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2060



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
143 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:13:12
ከሰሜኑ ጦርነት በኃላ ወሎ በጥቅሉ (ደቡብና ሰሜን) ለምክክር ሒደን ነበር። በአንደኛው ውይይታችን መጅሊሱ ውስጥ ያሉ አንድ ዑለማ ያስገረማቸውን ጉዳይ አጫወቱን። ይኸውም በሀይማኖቶች ጉባኤ በኩል ውይይት ለማካሔድ ከተለያዩ የእምነት ሰዎች ተወክለው ሲሄዱ አብረዋቸው የሚሄዱት ፓስተሮች ስማቸው የሙስሊም የሆነና በእስልምና አካባቢ ማደጋቸው የሚያስታውቅ መሆኑን አይተው ግራ ተጋብተው እንደነበር ገለጹልን።

የዚህ ምክንያቱ በርካታ ሊሆን ይችላል። ከኛ በላይ አካባቢው ላይ ያሉ ብርቱ ወንድሞችና ዑለሞች ብዙ የማናቃቸውን መግፍኤዎችን ሲዘረዝሩ ሰምተናል። ያለፈው አልፏል፥ ዋናው ነጥብ ይህ ስጋት ህዝባችን ላይ አሁንም አለ ወይ? የሚለው ነው። ብዙውን ጊዜ የሚሽነሪው እንቅስቃሴ ዟሂር ካለመሆኑ አንጻር በተለይም የገጠሩን አካባቢ በጥንቃቄ መመልከት ወሳኝ ነው። የትም ቦታ ቢሆን አንድም ሰው እንኳን ከፍሮ ማየት እንደ ሙዕሚን ይረብሻል።

Yahya ibnu nuh
143 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:21:31 "አቡሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ

"በሰማያት ውስጥና በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በርሱ ይቆጣጠራችኋል፡፡ ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡"
- ቡኸሪ ዘግቦታ"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
149 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:11:29
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 9 #ሸዋል 1444 ሂ
140 views03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:03:41 ቁሞ ቀርነት !

ሰሞኑን በአድስ አበባ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት መምህራን በየወረዳው በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ ። ታዲያ ይህ ስብሰባ ሰፋ ያለና የሙሉ ቀን ስብሰባ በመሆኑ ቡፌ ጭምር ተዘጋጅቶ ለሙስሊምና ክርስቲያን መምህራን ተለይቶ እየተደረገ ነበር ።

ምሳ ሰአት ላይ ቀኑ ጁሙአ በመሆኑ ሙስሊም መምህራን በሙሉ መስጅድ ሂደው ሲመለሱ ለምሳ መሰለፍ ይጀምራሉ ። በዚህ ጊዜ አስተናጋጆቹ " ምሳው ስላለቀ ተበተኑና ወደ ስብሰባው ግቡ " የሚል ይናገራሉ ። በዚህ ጊዜ ሙስሊም መምህራኖቹ " መመገቢያ ኩፖን ሰጥታችሁን ብዛታችንና የስም ዝርዝራችን ቀድሞ ደርሷችሁ ውጭ ምሳ እንዳንበላ ካደረጋችሁን በሗላ ለኛ የተዘጋጄው ምግብ የት ሂዶ ነው አልቋል የምትሉን ? ምንስ በላው ? ብለው ሲያፋጥጧቸው አዘጋጆቹ በትእቢት ከመልስ ይልቅ ወደ ንትርክ በመግባታቸው ሙስሊም መምህራኖቹ ስብሰባውን ረግጠው ሂደዋል ። ይህ የሆነው በኮልፌ ቀራንኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ ሁለት የትምህርት ቤቶች ስብሰባ ላይ ነው ።

ጉዳዩ ምሳ የመብላት ያለመብላት ሳይሆን በዚህ ተራ ነገር እንኳ ምን ያክል ቁሞ ቀሮች እንዳሉና ዛሬም ሀይማኖት ለይተው ንቀታቸውን የሚያሳዩ ጋጠወጦች አለመጥራታቸውን ማሳያ ነው ።

አንድም የተመገበ ሙስሊም መምህር ሳይኖር የሙስሊሞቹ ምግብ አልቋል ማለት ጥላቻቼውን ይችን አጋጣሚ ተጠቅመው ለማሳየት የሄዱበትን አሳፋሪ ድርጊት ያሳያል ።

አሁንም መስሪያ ቤቶች በተለይ የትምህርትና የአገልግሎት ተቋማት ከእንደዚህ አይነት ቁሞቀሮች መፅዳት አለባቸው ።

Seid mohammed alhabeshi



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
165 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:38:15 ሴት ልጅ የዲን እውቀት ካልቀሰመች ባሏን ታሰቃያለች ። ልጆችን ታበላሻለች ። ሕዝብን ታጠፋለች ።
ኢብኑል ቀይም
173 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 08:50:24 "ሀኪም ኢብኑ ሀዝም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ
(ሠ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ " በላይ የሆነች (ሠጪ) እጅ
በታች ከሆነችው (ከተቀባዩዋ) ትበልጣለች። ምፅዋትን
በስሮቻችሁ ባሉ ቤተሠቦቻችሁ ጀምሩ። ከምፅዋት ሁሉ
መልካሙ ሠጭውን ችግር ላይ በማይጥል መልኩ
የተፈፀመ ነው። የተቆጠበ፥ ቁጥብ ያደርገዋል። የተብቃቃ
አላህ መብቃቃትን ይቸረዋል።"
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
- ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
9 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 19:30:04
99 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 19:29:31 የነዚህ ፎቶዎች ድምር በጉንችሬ እየሆነ ስላለው ነገር ምን መልእክት ያስተላልፍላችኃል?

ፎቶ 1:-አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቲሸርት ለብሰው ደብተር በእጃቸው ይዘው የሚንቀሳቀሱ 'ተማሪዎች'
ፎቶ 2:-በህብረት ነጠላ ለብሰው በእጃቸው ደብተር ይዘው የሚንቀሳቀሱ 'ተማሪዎች'
በጉንችሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ:-
ፎቶ 3:-በትምህር ቤቱ ጊቢ ውስጥ ነጠላ እና አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የለበሱ 'ተማሪዎች'
ፎቶ 4:-በትምህርት ቤቱ በአንዱ መማሪያ ክፍል ውስጥ ደብተር ተዘርግቶ ትምህርት እየተሰጠ ባለበት ሁኔታ ነጠላ ለብሰው ቆመው ክፍል ውስጥ የሚታዩ 'ተማሪዎች'
ፎቶ 5:-አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቲሸርት የለበሱ ወደ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዳይገቡ ለመከልከል የተሰለፋ ሰዎች/'ተማሪዎች'
ፎቶ 6:-ኢስላም ያዘዘውን እና በህገ-መንግስት የሀይማኖት ነፃነት ዋስትና የተሰጠውን የመጎናፀፊያ ልብስ በመልበሳቸው/በመደገፋቸው ምክንያት ት/ቤት አትገቡም ተብለው የተከለከሉ ተማሪዎች።
*ከተራ ቁ 1-5 የተደረደሩ ፎቶዎች ላይ የ'ተማሪዎቹ' ስሜት የሚያንፀባርቀው:-
1)የአጥቂነት እና የማን አለብኝነት ስሜት
2)መዋቅራዊ ሽፋን እና ከለላ በሚሰጣቸው አካል የመተማመን ስሜት
3)አለባበሳቸው ለልዩ ተልኮ ያደረጉት እንጂ ለሐይማኖታቸው ካላቸው ቀናኢነት በመነሳት ዘውትር የሚያደርጉት አለመሆኑን
ፎቶ 7:-የክልሉ ርእሰ መስተዳድር
ፎቶ 8:-የክልሉ የፀጥታ ኃላፊ
ፎቶ 9:-"ከዚህ በፊትም ልጆቻችንን በተመሳሳይ የአለባበስ ስርአት አስተምረን ለወግ ለማእረግ አብቅተናል አዲስ የተፈጠረ ነገር የለም። አሁንም ልጆቻችን በሀይማኖታቸው ሳይሸማቀቁ የመማር መብታቸው ይከበር" በሚል ድምፃቸውን ያሰሙ የጉንችሬ እናቶች።

Ustaz mohammed abate


https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
95 viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ