2023-01-16 17:20:09
በልደታ ክፍለ ከተማ የመሪዎች ትውውቅ ተደረገ።
የልደታ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ትውውቅ አደረገ።
የከተማው እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣የአስሩም ወረዳ ተወካዮች፣ የመስጅድ ኢማሞች ፣ ሙአዚኖችና አስተዳደሮችን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም በትውውቅ መረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሚስባህ ወርቁ የክፍለ ከተማው ምክር ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ የተጣለባቸውን አደራ(አማና) ለመወጣት ባለፉት ሶስት እና አራት ወራት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የክፍለ ከተማቸውን ማህበረሰብ ለማገልገል ተቋም በመመስረት፣ ወረዳን በማደራጅት ስኬታማ ስራ መከናወኑን ገልፀዋል።
በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምክር ቤት አባልና የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ና ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ሪያድ ጀማል ንግግር አድርገዋል።
መሪነት አገልጋይነት እንጂ ተገልጋይነት አይደለም! አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ የሚባል መርህ በሚሪነት ውስጥ የለም!
መሪነት የሚወድህንም የሚጠላህንም በእኩል ማገልገል ስትችል ብቻ ነው ያሉት የፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ካሊድ መሀመድ ናቸው።
የምክር ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል በበኩላቸው የሰላማችን መሰረት የሆነውን አንድነታችንን አስጠብቀን ህልማችን የሆነውን ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ መሰረት ያለው በሀገራዊ ጉዳይ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርግ ተቋም መመስረት አለብን በማለት ለአመራሮቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የክፍለ ከተማው ም/ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ነስሩ የስራ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በቀበረው ሪፖርትና የወደፊት እቅድ እንዲሁም መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ጥያቄዎቸ ምላሽ ተሰጥቷል።
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
118 views14:20