2023-01-17 21:10:45
ከሰሞኑ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት የሀድያ ዞን ጭንጎ ወረዳ ታላቅ ኮንፈረንስ በዛሬው እለት መካሔዱ ተገለጸ
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 9/2015
...
❐ በኮንፈረሱ ከ4,000 እስከ 5,000 የሚሆን ሰው ተገኝተዋል ተብሎ ይገመታል።
❐ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤትችን የሚወክሉ ልዑካንም ጉዳቱን ለመታዘብ በቦታው ተገኝተው ነበር።
❐ ሀሩን ሚዲያ ክስተቱን ከመነሻው ጀምሮ የተከታተለ ሲሆን ሙሉውን ፕሮግራም ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
ከሰሞኑ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት የሀድያ ዞን ጭንጎ ወረዳ ታላቅ ኮንፈረንስ በዛሬው እለት መካሔዱ ተገለጸ። ጉዳዩን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ልዑካን ቡድን አባላት በቦታው በመገኘት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው እለት በቦታው ታላቅ ኮንፈረንስ በማካሔድ ከህዝቡ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም ህዝቡ የደረሰበትን በደልና ግፍ ለልዑካን ቡድኑ እና ለመንግስት አካላት የገለጸ ሲሆን አጥፊዎቹ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድም ጠይቋል።
...
በኮንፈረንሱ ከመንግስት በኩል የተገኙ የዞኑ ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ሳምኤል ሽጉጤ፣
የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ የግጭት አፈታት ባለሙያ እንዲሁም የወረዳው ፀጥታ ሀላፊ የተገኙ ሲሆን በመጅሊስ በኩል ከፌዴራል መጅሊስ ልዑካን በተጨማሪ የክልሉ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ም/ቤት፣ የዞኑ መጅሊስ ሰብሳቢና ስራ አስፈፃሚወች እንዲሁም የሀገር ሸማግሌዎች ተገኝተዋል።
...
በውይይቱ ላይ የተገኙት የመንግስት ኃላፊዎች አስፈላጊውን ማጣራት ከተደረገ በኋላ በአጥፊዎቹ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጹ ሲሆን የክልሉ እና የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የሀይማኖት ጉባኤ ተወካዮች የፌደራል እና የክልል መጅሊስ ተወካዮች የሚያደረጉት ውይይት እስከ ነገ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል። በውይይታቸው መጨረሻ በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል።
...
ሀሩን ሚዲያ
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
92 views18:10