Get Mystery Box with random crypto!

የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ  ም/ቤት 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአንድ መቶ ሚሊዮን | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ  ም/ቤት 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 10/2015
...
በሀርላ ሆቴል ሲካሄድ የነበረው  የሀረሪ  ክልላዊ መንግስት እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ  አንድ መቶ ሚሊዮን ብር አመታዊ በጀት በማፅደቅ ተጠናቋል። በጉባዔው ረቂቅ የክልሉ መጅሊስ ሕግ  ቀርቦ በጉባዔው አባላት ሰፊ  ውይይት ተደርጎበት የፀደቀ ሲሆን በቀጣይም የክልሉ  መጅሊስ ሕግ ሆኖ  ያገለግላል ።
..
ጉባዔው  የሶስት የኦዲትና ቁጥጥር አባትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን  በተጨማሪ የሀረሪ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ  ምክር ቤትን እንዲያገለግሉ ለሀጂ መሀመድ ሀሺም ፣ ለአባገዳ አህመድ ዩሱፍ ፣ ለሀጂ ነስረዲን አሊ ፣ ለሼይኽ መሀመድ ቃዲ እና ለሀጂ አህመድ ኢብሮሽ  የግልግል ሸንጎ አባትን ሹመት አፅድቋል።
...
የሀረሪ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የእስልምና ምክር ቤቱን  ስራ  ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን  እና የክልሉን ሙስሊም ተጠቃሚነት  ለማረጋገጥ   11 አባላት ያሉት የአማካሪዎች ቦርድ አባላትን ማለትም፦

1ኛ.አቶ ተወለዳ አብዶሽ
2ኛ.አቶ ያሲን አብዱላሂ
3ኛ.ዶ/ር አብዱላሂ ወዚር
4ኛ. ኡስታዝ ረመዳን ተማም
5ኛ.አቶ ሀምዛ ሽመልስ
6ኛ.አቶ መሀመድ አብዱረህማን
7ኛ. ሼህ አብዱረህማን መሀመድ
8ኛ. አቶ ሙስጠፋ መሀመድ
9ኛ.አቶ ፊላ አህመድ
10ኛ.ሼህ አልዪ መሀመድ
11ኛ.ሼህ ጀማል መሀመድን በመምረጥ ጉባዔውን  አጠናቋል።

መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።

ሀሩን ሚዲያ



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora