Get Mystery Box with random crypto!

የጉራጌው ይለያል ============== ጉንችሬ ላይ ያለው ጽንፈኝነት ጎጃምና ጎንደር ላይ ያ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የጉራጌው ይለያል
==============
ጉንችሬ ላይ ያለው ጽንፈኝነት ጎጃምና ጎንደር ላይ ያለውን የሚያስንቅ እየሆነ ነው።

መጀመሪያ እነርሱ ኒቃብና ጂልባብ ከተፈቀደላቸው ለኛም ነጠላ ለብሰንና የሞኣ አንበሳ ልሙጡን ባንድራ አሠርተን እንድንገባ ይፈቀድልን አሉ። አላማቸው ይሄማ አይፈቀድላችሁም፤ በቃ እነርሱም እናንተም መልበስ የለባችሁም ተብለው የሚከለከሉ መስሏቸው ነበር። ግን ተፈቀደላቸው። በዚህ አካሄድ እኩይ አላማቸውን ማሳካት ስላልቻሉ ጂልባብና ኒቃብ ከለበሱ ሙስሊሞች ጋር አንማርም ብለው ክላሱን ለቀው ወጡ።

ይህ ቪድዮ ነጠላ ለብሰው ክላሱን ለቀው እየተሳደቡ ሲወጡ የሚያሳይ ነው።


ይሄው አሁን ላይ የክልሉ፣ የዞኑና የወረዳው አስተዳደር ደግፏቸው ከ90% በላይ የሆነውን የት/ቤቱን ሙስሊም ተማሪ ከትምህርት አባረው እነርሱ ብቻቸውን እየተማሩ ይገኛሉ። ጭራሽ ቀስ በቀስ መስጅድ ወደማቃጠል ሙከራም አደጉ። ቀጣይ ምን እንደሚያደርጉ አብረን የምናየው ይሆናል። ከፌዴራል እስከ ክልል ያለ የመንግስት አካል እስካሁን በዝምታ ላይ ነው። ምን እስከሚፈጠር እንደሚጠብቅ ማወቅ አልተቻለም።

እጅግ በጣም አሳፋሪ የድንቁርናና የጽን'ፈኝነት ጥግ!

አሁንም ቢሆን የሚመለከተው የመንግስት አካል ቸልተኝነቱን ወደ ጎን በመተው ከሙስሊሞች የጸዳች ጉራጌን ለመመስረት ያለመ የሚመስለውን አደገኛ የጠርዘኝነት አካሄድ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ሳይዛመት በጊዜ ሊቀጨው ይገባል። ሳይቃጠል በቅጠል!


ሙራድ ታደሰ

https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora