Get Mystery Box with random crypto!

ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fethababora — ፈትህ አባቦራ መስጂድ
የሰርጥ አድራሻ: @fethababora
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-04 11:55:45 የሩቅ ሚስጥር ቁልፎች…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مِفْتَاحُ الْغَيْبِ خَمْسٌ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا اللَّهُ، لَا يَعْلَمُ أَحَدٌ مَا يَكُونُ فِي غَدٍ، وَلَا يَعْلَمُ أَحَدٌ مَا يَكُونُ فِي الْأَرْحَامِ، وَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَاذَا تَكْسِبُ غَدًا، وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ، وَمَا يَدْرِي أَحَدٌ مَتَى يَجِيءُ الْمَطَرُ﴾

“የሩቅ ሚስጥር (ገይብ) አምስት ናቸው። አላህ እንጂ ደግሞ ሌላ ማንም አያውቃቸውም። እነሱም፦ ነገ ምን እንደሚከሰት አንድም ሚያውቅ የለም። በመሀፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ሚያውቅ አንድም የለም። የትኛውም ነፍስ ነገ ምን እንደምትሰራ አታውቅም። የትኛውም ነፍስ የት ቦታ እንምትሞት አታውቅም። ዝናብ መቼ እንደሚዘንብ ሚያውቅ አንድም የለም።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 1039



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
150 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 06:26:33
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 11 #ሸዋል 1444 ሂ
35 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 06:26:04 "ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) በሶላት ውስጥ ስለመዟዟር ጠየቅኳቸው፡- ‹‹ይህ ሰይጣን የአንድ ባሪያን ሶላት የሚሰርቅበት አንዱ መንገድ ነው፡፡›› አሉኝ፡፡
(ቡኻሪ ዘግበውታል) - ቡኸሪ ዘግቦታ"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
35 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:20:32
95 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:20:16 ዳዕዋው ሴቶች በሴቶች ነው። የተሰጣትም ርዕስ ስለ ሰደቃ። በቁርአንና በሐዲስ እያዋዛች የተሰበሰቡትን ሴቶች ቀል አርጥባ እንደጨረሰች ታዳሚዎቹ ያላቸውን መስጠት ጀመሩ።
የገጠማትን ክስተት ከአንደበቷ እንስማው

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

"አንዲት ሴት ወደተቀመጥኩበት መጣችና የለበሰችውን የአንገት ጌጥ አውልቃ ልትሰጠኝ እጇን ዘረጋች። ዙርያው በአልማዝ የተጌጠና በዳይመንድ ያሸበረቀ ውድ ስለነበር ለመቀበል አንገራገርኩ። እርሷ ግን ውብ ጌጧን እንድቀበላት አስገደደችኝ"

ለየቲሞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለመሸፈን የሰበሰብነውን ጌጣጌጥ ይዘን ወደ መሸጫ ሱቁ አመራን። ሽያጩን የምንፈፅምለት የመስጂዱ ጀመዓ ስለነበር ዋጋ ተስማምተን አልማዙን ከወርቁን ለመነጣጠል ይፈለቅቀው ጀመር። በውስጡ የተጠቀለለ ነገር አገኘ። በአረበኛ ቃላቶች የተፃፈ ወረቀት ላይ ሲህር የተሰራበት ፀጉሯ ተጠቅልሏል። ምን ጉድ ነው ብለው እየተዓጀብን አስቤዛና አልባሳቱን ለየቲሞች አከፋፍለን ተመለስን።

ከሳምንት በኋላ ይህን ጌጥ ሰደቃ የሰጠችን ሴት አጠያይቃ ወደቢሮዬ ዘለቀች ሰላምታን ከተለዋወጥን በኋላ ስለራሷ እንዲህ በማለት መናገር ጀመረች
"በአላህ እምላለሁ ከባለቤቴ ጋር በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ከተኛን አስራ ስድስት ዓመታትን አሳልፈናል። የቤተሰባችን ፍቅርና ሰላም ተናግቶ የስቃይ ህይወት መኖር ከጀመርን ድፍን አስራ ስድስት አመታት ተቆጥረዋል። ይህንን ጌጥ ሰደቃ ከሰጠሁ በኋላ ግን ቤተሰባችን በአንድ ማዕድ ተሰብስቦ በፍቅር እራታችንን ተመገብን። ከባለቤቴም ጋር በደስታ አንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ተኛን ጌጡን በጣም ከምንዋደድ ጓደኞቼ የተሰጠኝ ስጦታ ነበር" አለችኝና ስቅስቅ ብላ አነባች።

የገዛ ጓደኞቿ ሲህር አሰርተው እሷንም ቤተሰቧንም ሲያናጉት እንደኖሩ በሰደቃዋ ሰበብም አላህ ሊፈውሳት እንደፈለገ ተረዳሁ። በእርግጥም ውድ ዋጋ ያወጣ ነበር።
"ጠላትህን አንድ ጊዜ ወዳጅህን ደግሞ መቶ ጊዜ ተጠንቀቀው" የሚለው አባባል በአይምሮዬ አቃጨለ" በማለት ገጠመኟን ትቋጫለች።

ማስታወሻ
ከታች ያለው ምስል ለሌላ እንስት ከጫማዋ ሶል ስር ሲህር አሰርተው በስጦታ መልክ የሰጧት ነው



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
101 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 16:54:48 መህዲ ማነው?

‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››
(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።
(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።
(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።
(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።
(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።
(አል-ቂያማህ አስ-



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
131 views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 14:00:42 ኡስታዝ ኢስማዒል ያሲን
እስቲቃማ
ዛሬ እሁድ ከዙሁር ቡኋላ
በፈትህ አባቦራ መስጂድ
የተደረገ ዳእዋ ነው
አዳምጡት
129 viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 07:29:06
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 10 #ሸዋል 1444 ሂ
136 views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 06:29:25 "አቢ ዐብባስ ዐብደላህ ኢብኑ ዐብባስ ኢብኑ ዐብደል ሙጠሊብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ፡-
‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በሐዲሰል ቁድስ ተከታዩን ተናግረዋል
‹‹አላህ መልካምና ክፉ ተግባራትን ጽፏል ይህንኑ አብራርቷልም አንዲትን መልካም ተግባር ለመፈጸም ያሰበና ያልፈጸማት ልዑልና ቅዱስ የሆነው አላህ ከርሱ ዘንድ አንድ ሙሉ መልካም ተግባር (የመልካም ተግባር ምንዳ) ይጻፍለታል፡፡ አስቦ ከፈጸማት ደግሞ ከእስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም በላይ መልካም ተግባራትን ይጻፍለታል፡፡ ክፉ ተግባር አስቦ ካልፈጸማት አላህ ከርሱ ዘንድ አንድ ሙሉ መልካም ተግባር ይጻፍለታል፡፡ ግን አስቦ ከፈጸማት አንድ ክፉ ተግባር ብቻ ይጻፍበታል፡፡»

(ቡኻሪና ሙስሊም)
- ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።


https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
135 views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:57:05
150 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ