2023-05-09 17:26:13
በእጁ ያረጀና የተቀደደ ጫማ አንጠልጥሎ ወደ ኸሊፋ መህዲ ቢሮ ዘለቀ
"ይህ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጫማ ነው። በስጦታ መልክ ሰጥቼሀለው ተቀበለኝ" በማለት እጁን ዘረጋ። ኸሊፋው የተሰጠውን ጫማ ተቀብሎ ሳመና እግሮቹ ላይ እያጠለቀ አስር ሺህ ዲርሃም እንዲሰጠው አዘዘ።
ሰውዬው ብሩን ይዞ ከቤተመንግስቱ አፈትልኮ እንደወጣ ኸሊፋው በዙርያው ወደተሰበሰቡት መኳንንት ዞሮ፡-
"ረሱል ይህን ጫማ እንኳን ሊለብሱት እንዳላዩት አውቃለሁ። ሳልቀበል ብመልሰው ጎሳውን ሰብስቦ የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጫማ በስጦታ ብሰጠው አልቀበልም አለ ይላቸዋል። አብዛኛው ማህበረሰብ ዘረኛ ስለሆነ አምነው ይቀበሉታል። በዚህ ምክንያት ፊትና እንዳይቀሰቀስ ምላሱን በአስር ሺህ ዲርሀም ገዝተነዋል" በማለት ተናገረ።
ምንጭ
البداية والنهاية لابن كثير
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
132 views14:26