Get Mystery Box with random crypto!

'ዓነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት 'ሦስት ሰዎች ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ቤት መጡ። ስለአላ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

"ዓነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት

"ሦስት ሰዎች ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ቤት መጡ። ስለአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አምልኮ ዒባዳ ለመጠየቅ። ሲነገራቸውም ቀለል አድርገው ተመለከቱት። "ያለፈውም የሚመጣውም ግድፈታቸው ይቅር የተባለላቸው ነቢይ (በአምልኮ ክንውን) ከኛ ጋር የሚወዳደሩ አይደሉም። አሉ። ከሦስቱ አንዱ፦ "እኔ ሁሌም ሌልቱን ስሰግድ አድራለሁ" አለ። ሌላኛው፦ "እኔ ዓመቱን ሙሉ በፆም አሳልፋለሁ" ሲል ሶስተኛው ደግሞ "እኔ ከሴት እርቃለሁ እስከወዲያኛው አላገባም" በማለት ተናገረ። የአላህ
መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ እርሱ መጡና "እናንተ ናቹህ እንዲህ ... እንዲህ ያላችሁት? በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከእናንተ ይበልጥ አላህን እፈራለሁ፣ እጠነቀቀዋለሁም፥ ነገር ግን እፆማለሁ፣ ፆም እፈታለሁ። እሰግዳለሁ። እተኛለሁ። ሴትም አገባለሁ። ከእኔ ሱንና ያፈነገጠ ዓርዓያነቴን አልተከተለም" አሉ።"
(ቡኻሪ እንደዘገቡት)
- ቡኸሪ ዘግቦታ"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora