2023-04-25 09:46:46
የሚመለከተው የመንግሥት አካል እና መጅሊስ ለ3 ዓመታት ቸል ያሉት የጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ
ሂደቱ እንዲህ ነው...
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ እና በጉንችሬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ3 አመታት በላይ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ያለምንምን እክል ኒቃብ ለብሰው በመማር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2014 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አዲስ ቅርጽና ይዘት ያላቸው እና ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ ለማራቅ በማቀድ ኒቃብ መልበስን መከልከል መነሻ ያደረጉ ችግሮች መከሰት ጀምረዋል።ሙስሊም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትኩረት ተከታትለው ወጤታማ ሆነው ሀገራቸውን እንዳያገለግሉ የሚያደርጉ እርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይተዋል። ለአብነትም:-
◎ በ 2015 መጀመሪያ አካባቢ ኒቃብ ለባሽ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በጥበቃ ኒቃብ ለብሳችሁ መግባት አትችሉም በሚል ከበር እንዲመለሱ እና እንዲገለሉ ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ (እገዜ) አካባቢ ኒቃብ ለባሽ ሴት ተማሪዎችን ኒቃብ ለብሳችኋል በሚል ዞን ድረስ በማስመጣት እና ለእስር በመዳረግ እንዲንገላቱ ተደርጓል።
◎በቀን 10/03/2015 ጉንችሬ መሰናዶ ትምህርት ቤት ላይ የሙስሊሞችን ኒቃብ ለብሰው መማርን በሚቃወሙ ሌሎች ተማሪዎች አማካኝነት የቃጠሎ እና የፕላዝማ ንብረት ዝርፊያ ሙከራ ተፈጽሞ ሳለ ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ምክንያት ዳግም በቀን 23/03/2015 የቃጠሎው ወንጀል ሊፈጸም ችሏል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ከወላጆች ጋር በተደረገ ውይይት ይህን ወንጀል የፈጸሙት ልጆቻቸው መሆኑን በማመን ኃላፊነት እንደሚወስዱ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም አስከ አሁኑ ድረስ ምንም መፍትሄ ሳይበጅለት ቀርቷል።
◎በ ጋርባዶ ትምህር ቤት የአካባቢውን ማህበረሰብ ጭምር በመቀስቀስ ገጀራ ይዞ በመውጣት እልቂት ለመፈፀም ሙከራ ተደርጓል።
◎ሙስሊም ወንድ ወጣቶችን በማሳደድ በማሽማቀቅ ከ42 እና 55 ኪ/ሜ በላይ ተወስደው እንዲታሰሩ ቀለብና ልብስ እንዳያገኙ ተደርጓል።
◎በቀን 18/05/2015 ጉንችሬ ከተማ 02 ቀበሌ የሚገኘው አል አቅሳ መስጅድ የቃጠሎ ሙከራ ተድርጎበታል።
◎ከዚህም ባሻገር በደል እየደረሰባቸው ላሉ ተማሪዎች ድጋፍ ያደርግ የነበረው የማህበረሰቡ አካል ከአካባቢው ደንብሮ እንዲጠፋ በልዩ ሃይል ማስፈራራት እንዲሁም በድብደባ ሴቶች እና ሽማግሌዎች እንዲቆስሉ እንዲታሰሩ ተደርጓል።
◎በተጨማሪም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ አድማ በማድረግ፣ ለሙስሊም መሸጥም ሆነ መለወጥ በመከከል ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ አድማ ለማድረግ ተሞክሯል።
◎ምንም እንኳን ከአካባቢ ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ጋር በተደጋጋሚ በተደረገ ውይይት የወረዳውን፣ የዞኑን እና የነዋሪዎቹን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ ተማሪዎች በነበሩበት ሁኔታ ኒቃብ ለብሰው እንዲማሩ እና ት/ቤቱም እንዲከፈት ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ውሳኔው ተፈጻሚ ሊሆን አልቻለም።
◎ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉንችሬ እና በ እገዜ ትምህርት ቤት ከሁሉም ሃይማኖቶች የተውጣጡ ከ 1800 በላይ ተማሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በትምህርት ገበታ ላይ ተገኝተው እየተማሩ ያሉት ከ 300 የማይበልጡ ተማሪዎች ብቻ ናቸው። የተቀሩት ኒቃብ ካላወለቃችሁ አትማሩም ስለተባሉ ከትምህርት ገበታ ተገፍተዋል..
በአካባቢው ላይ እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት መንግሥት እና መጅሊስ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ የአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ያመለከቱ ቢሆንም ጉዳዩ ሳይፈታ ቸል በመባሉ የዛሬውን ክስተት ሊወልዱ ችለዋል።
ኡሰታዝ ነስሩ ኸድር
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
110 views06:46