Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2022-06-15 17:03:07 #ማስታወቂያ

በቻይና ሀገር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ለነበራችሁ ተማሪዎች!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ይሄንን ተከትሎ የቻይና መንግስት ባወጣው የኮቪድ- 19 ፕሮቶኮል ምክንያት በአጋጣሚ ወደሀገራችሁ መጥታችሁ መመለስ ላልቻላችሁ ተማሪዎች መንግስታችንና ቻይና ሀገር የሚገኘው ኤምባሲያችን ወደ ቻይና ተመልሳችሁ ያቋረጣችሁትን ትምህርት እንድትከታተሉ እየሰሩ ይገኛል።

ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘው ፎርም መሰረት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ በሚከተለዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት ፎርሙን ሞልታችሁ በተከታዩ ኢሜይል አድራሻ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ
ይህ ማስታወቂያ የሚመለከተው በኢትዮጵያ መንግስት የተላኩትን ብቻ ነው።

Link- https://moe.gov.et/AddReso

Email፡ daddiketema@gmail.com, educationattache@ethiopianembassy.org.cn

ትምህርት ሚኒስቴር
4.7K viewsedited  14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 17:02:47
3.3K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 17:02:23 በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ።
-----------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ( ፕሮፌሰር) አዲስ ከተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

አዲስ የተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና የቦርድ አባላቱ ሃላፊነታቸውን አውቀው በባለቤትነትና በእውቀት እንዲመሩ ለማስቻል ያለመ ነው።

በቀጣይም በዩኒቨርስቲ የትምህርት ጥራት ፣ የሀብት ብክነት መከላከል እና የዩኒቨርስቲ አስተዳደር ነፃነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአዲሱ ሪፎርምም የስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የዩኒቨርስቲ የመስክ ልየታ ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማጠናከር አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን መሾሙ ይታወሳል።
3.6K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 15:19:26
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ያለማንም ተጽእኖ ዝንባሌያቸውንና ችሎታቸውን ብቻ ተከትለው የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን  መርጠው እንድማሩ ማማከርና መደገፍ ለዘላቂ የህይወት ስኬታቸውም ሆነ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ውጤታማንት ወሳኝነት እንዳለው ተገለጸ፡፡
===============================

ትምህርት ሚኒስቴር ከአሜሪካን ኢምባሲ ጋር በመተባበር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ዝንባሊያቸውን እንዲለዩ፥ እንዲያዳብሩና በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን እንዲመርጡ የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ መምህራንን ለሚያዘጋጁ ከ70 የመንግስትና የግል ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ መምህራንና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ያለማንም ተጽእኖ ችሎታቸውን ብቻ ተከትለው የከፍተኛ ትምህርት የሙያ መስካቸውን  መርጠው እንዲማሩ የሚያስችል የማማከርና የመደገፍ አገልግሎት መስጠት ለዘላቂ የህይወት ስኬታቸውም ሆነ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ውጤታማነት ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኢምባሲ የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች ከፍተኛ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ዝንባሌያቸውን እንዲለዩ፥ እንዲከተሉና እንዲያሳድጉ ማድረግ የሚያስችል የማማከርና ድጋፍ አገልግሎት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ይበልጥ ተጠናክሮ እንድሄድ እያበረከተ ላለው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ  አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡
3.6K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 15:19:23 በአሜሪካ ኢምባሲ የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ተክለሚካኤል ተፈራ ተቋማቸው በተለይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የማማከርና የመደገፍ አገልገሎት በስፋትና በጥልቀት ተጠናክሮ እንዲሰጥ ለማስቻል ለሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው  የአቅም ግንባታ ስልጠና  ዘዴን በተመለከተ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትን መልምሎ ወደ ማዕከል በመጥራት፥ በቀጥታ በበይነመረብ በማግኝት፥ የተለያዩ ግብኣቶችን በመስጠት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የስልጠናው ይዘት ሳይንሳዊ እውነታንና የሀገራት ተሞክሮዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን በመክፈቻውም ወቅት አሜርካን ኢምባሲ 560 የተለያዩ የእንግልዝኛ ቋንቋ ማዳበሪያ መጽሃፍትን ለትምህርት ሚኒስቴር አበርክቷል፡፡
                       
3.3K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 21:56:14
ሳውዝ ዌስት አካዳሚ በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 200 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ፡፡

የአካዳሚው ማነጅንግ ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው ከተማ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት ድጋፉ በትምህርት ቤቱ እየተንቀሳቀሱ ካሉ ተጓዳኝ ትምህርቶች መካከል የበጎ አድራጎት ክበብን በማጠናከር የተሰበሰበ ነው ብለዋል ፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ መዝገቡ ቢያዝን በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት አካዳሚው ላበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቀርበዋል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት አቶ መዝገቡ እንደተናገሩት የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት የስራ አጋርነትን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡

ድጋፉም በተለያዩ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ለወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ግንባታ ይውላል ብለዋል አቶ መዝገቡ፡፡
2.6K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 16:08:54
"ሁሉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ገፆችን እያየን ነው።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቃችሁ ትኩረታችሁን ትምህርታችሁ ላይ ብቻ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ ይህንን በመረዳት ከተሳሳቱ መረጃዎች ራሳችሁን በማራቅ ሌሎች እንዳይሳሳቱ የማድረግ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን የትምህርት ሚኒስቴር ትክከለኛ የመረጃ ማሳረጫዎች የሚከተሉት መሆናቸውን እናሳውቃለን

ፌስቡክ-https://www.facebook.com/fdremoe

ቴሌግራም - https://t.me/ethio_moe

ሊንክድኢን- https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia

ትዊተር- https://twitter.com/fdremoe?t=dFhfr8QytU_6LqQuVUIp2A&s=09

ከእነዚህ ውጭ ባሉ አድራሻዎች እኛን የሚመለከቱ አሳሳች መረጃዎች ስታገኙ እንድትጠቁሙንም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
10.4K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:36:07
የተማሪዎች፣ የመምህራና ወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ ቀን ተከበረ፡፡
--------------------------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር ከቅን ኢትዮጵያ ማህበር ጋር በመተባብር አገር አቀፍ የመምህራን፣ የተማሪዎችና የወላጆች የመደናነቅና የመመሰጋገን ቀን ለሁለተኛ ጊዜ አከበረ።

የቅን ኢትዮጵያ ማህበር መስራች የሆኑት ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና እንደተናገሩት የመድረኩ ዓላማ የተማሪዎች፣ የመምህራና ወላጆች የመመሰጋገንና የመደናነቅ ባህል ይበልጥ ለማሳድግ ታስቦ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ቶሎሳ ትምህርት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ይዘው የሚወጡት ዲፕሎም ወይም ዲግሪ ባሻገር በትምህርት ቤት ቆይታ በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ለቤተሰብ እና ለአገር ኃላፊነት ብቁ ለመሆን የሚዘጋጁበት ሂደት ነው።

ትምህርት ቤቶች የአስተዋዮች፣ የአስታራቂዎች፣ የመካሪዎችና የጨዋዎች ማሳደጊያ ማዕከል መሆን እንደሚገባም ዶ/ር ቶሎሳ ተናግረዋል።

“በመሐከላችሁ ሆነ በዘመናችሁ ማንም ከቋንቋው፣ ከብሔሩ፣ ከፆታው፣ ከችሎታው ከማንነቱ የተነሳ የሚገለል፣ የሚሰደድና አድማ የሚደረግበት ኢ-ሰብዓዊነት ስለሆነ በፍፁም መኖር የለበትም”፡- ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና ።

መምህራንና ወላጆችም ተማሪዎች ፍቅርን፣ መከባበርን፣ ቅንነትን፣ይቅርታ መጠየቅን፣ እውነትንና መልካምነት እንዲማሩ ለማድረግ ኃላፊነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በዕለቱም ተማሪዎች፣ መምህራንና ለወላጆች ላበረከቱት የቅንነትና የመልካምነት አስተዋጽኦ የመመሰጋገንና የመደናነቅ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
3.3K viewsedited  13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 19:01:13
ማስታወቂያ

የመቁረጫ ነጥብ በሟሟላት በትምህርት ሚኒስቴር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ ከግንቦት 8-10 ባሉት ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡና ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን ምዝገባ እንድታደርጉና ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናስታውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
1.6K viewsedited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 10:42:29
ኢትዮጵያ በምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ የአውሮፓ ህብረት የሆራይዘን ፈንድ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ።
-------------------

በአውሮፓ እና በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ጠንካራ የምርምር ትብብር ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ምክክር እየተደረገ ነው።

በመድረኩም የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ በሚደረግበት ዙሪያም ውይይት ተካሂዷል።

በአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ረጅም ጊዜ የቆየውን የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በምርምርና በኢኖቬሽን ዘርፍ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በትምህርት፣ በጤና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የአውሮፓ ህብረትና ኢትዮጵያ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቀዳሚ ምርጫ መሆኗን ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን ቢኖር (ፒ ኤች ዲ) ተመራማሪዎች መንግስት የሚመድበውን በጀት ብቻ መጠበቅ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ውስጥ በመሳተፍ ከፍተኛ የምርምር ድጋፎችን ማሸነፍና ማምጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ምክክሩ የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ልዑካን ጽሕፈት ቤት በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ስላለው እቅድ ለማስተዋወቅ፣ ከአውሮፓ ህብረት የሆራይዘን የምርምር አሸናፊዎችን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈልና እድሉን ማግኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
3.6K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ