Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-10-06 08:13:20
የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን የተደረገውን ዝግጅት ተመለከቱ
----------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን የተደረገውን ዝግጅት ጎበኝተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መሰንበቱን ጠቁመዋል።

በተለይም ለተማሪዎች የሚሆን የምግብ፣ የመኝታ፣ የመመገቢያ እና የመፈተኛ ስፍራዎችን የማዘጋጀት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን በመፈተኛ ክፍሎች፣ በምግብ ቤት ዝግጅት እና በተማሪዎች ማደርያ ዙሪያ አስቀድመው የተደረጉት ዝግጅቶች አጥጋቢ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ያደረገው ዝግጅት ሰፊ፣ አስፈላጊና መሠረታዊ ጉዳዮች የተሟሉበት መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት መታዘባቸውን አብራርተዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0qJhjZn1AcZRWoLcMCuKGbMRuq5e8z8xje1WYcAJes8V4Pw92h2z3f7k46WjajPdbl&id=100064682287722
4.5K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 15:47:11
#ማስታወቂያ

መስከረም 30/2015 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ሆኖም የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን እና የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ መደረጉን በአክብሮት እየገለጽን የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አዉቃችሁ በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻ /Orientation/ እንድትከታተሉ እናሳስባለን ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር !
7.5K viewsedited  12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 13:57:41
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ(ዶ/ር) የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ያደረገውን የቅድመ ዝግጅት ጎበኙ
_____________________________________________

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ያደረገውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ትናንት ማምሻውን ተመልክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲፈተኑ መደረጉ ዓላማዎች ተማሪዎች ፈተናን በራሳቸው ሰርተው ማለፍ የሚችሉበትን ባህል መመለስ እና ፈተናን ከማጭበርበርና ከስርቆት ነጻ የማድረግ መሆኑን ገልጸዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ ፈተናን በመስረቅ ወይም የተሳሳቱ መልሶችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው እንዳይሰሩ የሚደረግበትንና የሚደርስባቸውን የስነ ልቦና ጫና ለማስቀረት እንደሚያስችል ዶ/ር ፋንታ አስረድተዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ እንደሚያስፈትን ጠቅሰው፤ ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ሥራውን በአካል ተገኝተው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይ የተማሪዎችን የመፈተኛ፣ የመኝታና የመመገቢያ ክፍሎች መጎብኘታቸውን ገልጸው ጥሩ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ፈተናው ያለምንም እንከን በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን በየደረጃው ያለው አመራር ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክተዋል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0PF1uMDKgHVngTZRh5LV5oGRWgEENbsJVn4tjUgXtv7j74RFW4iDRBXd6EVfLrYNXl&id=100064682287722
ምንጭ;- የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት
3.9K views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 11:33:16
በከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት እና በሙያ ማህበራት ለሚዘጋጁ የምርምር ጆርናሎች ግምገማና እውቅና ስርዓት በማበጀት የምርምር ጆርናሎችን ተቀባይነት፣ ጥራት እና እይታን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር በብሄራዊ ምርምር ጆርናሎች ግምገማና እውቅና አሰጣጥ ስርዓት ፣ ወቅታዊ ሁኔታና ተስፋዎቻቸው ዙሪያ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በምርምር ተቋማት እና በሙያ ማህበራት የሚሰሩ ምርምሮችንና የጥናት ህትመቶችን ለዓለም ተደራሽ በማድረግ ቅቡልነታቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

በአገሪቱ የከፍተኛ የትምህርትና ምርምር ተቋማት እና በሙያ ማህበራት በምርምር ስራ የሚሳተፉ በርካታ ምሁራንና ተመራማሪዎች ቢኖሩም በአለም አቀፍ ምርምር ጆርናሎች ላይ የሚደረገው አስተዋጽኦ ግን አነስተኛ መሆኑን ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች ጥራትና ደረጃቸውን ጠብቀው በአገሪቱ በሚቋቋም የምርምር ጆርናሎች ድረ-ገጽ እና መረጃ ቋት ውስጥ እንዲመዘገቡና ተደራሽ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡


https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0314JQCwEhNR7XsysbXNFJ8XzvBrNt1QKhqCYi22fAa6tBuix2w8hwHGViC2g2dpkcl&id=100064682287722
4.3K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 16:38:04 Dear Colleagues,

We in the Communication Department of the MoE are pleased to inform you that the below is our TikTok account and you can follow it.

@Official Moe_Ethiopia

Kind Regards,
1.7K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 08:34:59
ከ900ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፈተናሉ
------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከመስከረም 30 ጀምሮ በሁለት ዙር በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 976ሺህ 18 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚፈተኑ ተፈታኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት በ300 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።

በጸጥታና በሌሎችም ምክንያቶች ፈተናውን መውሰድ የማይችሉ ተማሪዎች ደግሞ በአንድ ወር ጊዜው ውስጥ በሁለተኛ ዙር በተመሳሳይ ፈተናውን እንደሚወስዱ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ህብረተሰቡም መንግስት የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ የወሰደውን እርምጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልጆቻቸውን ወደፈተና ጣቢያዎች ከመላክ ጀምሮ በፈተናው የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይመጡ በመከልከል ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናው በዩኒቨርስቲ መሰጠቱ የፈተና ስርቆትን እንደሚያስቀር ገልፀዋል።

ለሂደቱ ስኬታማነትም ተማሪዎች ፣ ወላጆች፣ የደህንነትና ጸጥታ አካላት፣ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤትና ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ተቋማት፣ የሚዲያ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጉዳዩ የተሻለች አገርን የመገንባት በመሆኑ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል።
999 views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:23:08
በ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጠ
--------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ማብራሪያና መግለጫ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለጹ ሲሆን ሂደቱ ተማሪዎች በራስ ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆኑበት ነው ብለዋል።

ከዚህም መካከል የፈተናው ዝግጅትና ህትመት በቴክኖሎጂ ታግዞ በከፍተኛ ጥንቃቄና ከደህንነት ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ መከናወኑን በመግለጫቸው  ተናግረዋል።

እስከ አሁን በነበረው የቅድመ ዝግጅት ሂደትም ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የስራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመግለጫው ሀገር አቀፍ ፈተናው በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያው ዙር  የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች  ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02,2015 ዓ.ም ፈተናውን ሲወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከ ጥቅምት 8,2015 ዓ.ም እስከ 11,2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተፈታኞችም  ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን በፊት ባሉት ሶስት ቀናት በሚፈተኑበት ዩኒቨርስቲዎች መገኘት እና ኦረንቴሽን መውሰድ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።

ከፈተናው ቀን በፊት ባሉት ቀናት ተማሪዎችን ወደ ፈተና ቦታ የማምጣት እና ፈተናው እንዳለቀም ተማሪዎችን ወደየመጡበት አካባቢ የመመለስ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0pKFsuU6QmsRisTRV1DQy7BdQhc82vQRde7t6ZQTdvU3BuU3AX5RmGbcbGe5YGdjVl&id=100064682287722
2.0K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 12:09:50
የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በፈተና ወቅት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ተግባራት
3.9K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:12:53
7.7K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 08:22:56
እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!

የኢሬቻ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) የማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስ ተደርጎ በመመዝገቡ ከሀገራችን አልፎ የዓለም ቅርስ ሊሆን ችሏል፡፡

መልካም የኢሬቻ በዓል!
ትምህርት ሚኒስቴር!
6.4K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ