Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-10-10 09:27:17
ዛሬ ጠዋት መስከረም 30/2015 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ በደረሰዉ ጉዳት እናዝናለን፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡ ሁኔታቸዉንም መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ በመሆኑ ወላጆች እንዳይደናገጡ እንጠይቃለን፡፡

ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ በመሆኑ እየገለጽን ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ሁኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የምናሳዉቃችሁ ይሆናል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር!
1 view06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 07:36:42
በመላ ሀገራችን ዛሬ የሚጀምረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
1.0K viewsedited  04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 22:46:37 #ማስታወቂያ

ለነፍሰጡሮች   እና ለሚያጠቡ እናት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ ተዘጋጅቷል፡

ለመፈተን ወደዩኒቨርሲቲ ከመጡ ተፈታኞች መካከል ወደ ተቋማቱ እንደደረሱ የወለዱ አሉ።  እነዚህ ወላድ ተፈታኞች የቤተሰብ እንክብካቤና ፈተናውን ለመፈተንም አካላዊ ማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው፡፡

በመሆኑም በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ የሚፈተኑ መሆኑ ታውቆ ቀድሞ በተላለፈው መመሪያ መሠረት በመጀመሪያው ዙር መፈተን የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
2.8K views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 18:39:29 በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ገለጻ ተሰጠ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጁ ሰባት የፈተና መስጫ መዕከላት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች መስከረም 29/2015 ዓ/ም ገለፃ ተሰጥቷል፡፡

በዕለቱ ተፈታኞች መከተል ስላለባቸው የፈተና ሥነ-ምግባርና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ የተሰጣቸው ሲሆን የፈተና ሕግና ደንቦችን አለማክበር በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በወጣው መመሪያ መሠረት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይም በዛሬው ዕለት ለፈታኝ መምህራን አጠቃላይ ገለፃ በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ማዕከላት ተሰጥቷል።

በበይነመረብ በተካሄደ መርሃ ግብር ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድና የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ፈታኝ መምህራን የተጣለባቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በፍጹም ኃላፊነት እንዲወጡ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid021zuhguLn2Pw1Fv5ZbcLmsY88fNJuXNnVCmo3wS8Sfkb13TL2EpteNXDUmp2nwkjal&id=100064396371463&sfnsn=mo
3.9K viewsedited  15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 18:23:39
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ  ሰጥቷል።
-------------------------------
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ተመድበው የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለሚፈተኑ ከ25,000 በላይ  የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ  ተማሪዎች ስለፈተናው አሰጣጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) የሰጠ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎችም በሚሰጣቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰረት መመራት እንደሚገባቸው ተብራርቷል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫው ተማሪዎች ማድረግ ስለባቸውና ስለሌለባቸው ጉዳዮችበፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ መሰጠት የሚጀምር ይሆናል።
3.6K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 15:42:42
የኒቨርስቲዎች በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ኦረንቴሽን እየሰጡ ነው።
----------------------------------------
ዩኒቨርስቲዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን ለተመደቡ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞች፣ ማየት ለተሳናቸው ተፈታኝ አንባቢዎችና ለመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች ኦሬንቴሽን እየሰጡ ነው።

ዩኒቨርስቲዎቹ በተመሳሳይ ለተፈታኝ ተማሪዎችም ስለ ፈተና ሰርዓቱ ኦረንቴሽን በመስጠት ላይ ናቸው።

የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ከመስከረም 26 ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ሲገቡ መቆየታቸው ይታወሳል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከነገ ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል።

ምስል - የወለጋ,ቡሌሆራ እና የወልድያ ዩኒቨርስቲ
3.8K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 14:58:00
ወልድያ ዩኒቨርስቲ በፈተናው አተገባበር ዙርያ ኦሬንቴሽን ሰጥቷል።
-------------------

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞች፣ ማየት ለተሳናቸው ተፈታኝ አንባቢዎችና ለመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።

በኦሬንቴሽኑ ላይ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማን ጨምሮ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከፈተናዎች አገልግሎት ተመድበው የመጡና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተገኝተዋል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ እንደሃገር የተሰጠንን ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በብዙ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ሁነን እስከዚህ ድረስ ያለውን ምዕራፍ በተሳካ ሁኔታ ለመስራት ችለናል ብለዋል።

በቀጣይ በጋራ በመስራት ፈተናው በሰላምና በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ሁላችንም የተሰጠንን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ ልንወጣ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

የእያንዳንዱ ተግባርና ኃላፊነት ምን እንደሆነ በፈተናው ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ሽመልስ ሳህሉ አማካኝነት ለተሳታፊዎች ገለጻ ተደርጓል።
3.5K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 13:56:58
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ95 በመቶ በላይ የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን አሳወቀ ።
---------------------------------------------

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም ካምፓሶቹ  ከ25,000 በላይ በመጀመሪያ ዙር ከሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ ከ95% በላይ ተፈታኞችን መቀበሉን ገልጿል ።

የዪኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቀነኒሳ ለሚ (ዶ/ር) ከመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች ውስጥ ከ95%በላይ የሚሆኑት ያለምንም ችግር ወደ ዩኒቨርስቲው በሰላም መግባታቸውን ገልጸዋል ።

በመውሊድ በዓል ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲው ያልገቡ ቀሪ ተማሪዎችን በዛሬው እለት እየተቀበሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ለፈታኞች፣ለሱፐር ቫይዘሮች እንዲሁም ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ስለ ፈተና አሰጣጡ  ኦሬንቴሽን በትላትናው እለት መሠጠቱን የገለፁት ም/ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለተፈታኝ ተማሪዎች ኦሬንቴሽን እንደሚሠጣቸው ገልጸዋል ።

ም/ፕሬዝዳንቱ ለተፈታኝ ተማሪዎች የመልካም እድል ምኞታቸውንም ገልፀዋል።
3.8K viewsedited  10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 11:43:24
በህዳሴ ግድብ፣ አረንጓዴ አሻራ እና የስንዴ ምርት ያየነውን ውጤት በትምህርት ጥራት እንደግመዋለን - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

----------------------------------------------

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ፈታኝ መምህራንን በበየነ መረብ አግኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈተና ስርዓቱ በባለፋት አመታት ባልተገባ ሁኔታ የተለያዬ ፍላጎት ባላቸው አካላት ለችግር የተጋለጠ እንደነበር ጠቅሰው ዘንድሮ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ በተደረገው ጥረት የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሃላፊነታቸውን በታማኝነት እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው እስካሁን በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የነበረው ዝግጅት የተሳካ እንደሆነ ገልጸው በተጀመረው መንገድ በስኬት እንዲጠናቀቅ ፈታኝ መምህራንን ጨምሮ በሂደቱ ድርሻ ያላቸው አካላት በመተባበርና በፍጹም የሃላፊነት ስሜት እንዲሰሩ አሳስበዋል ።

አሁን በሁሉም 12ኛ ክፍል ፈታኝ ዩኒቨርስቲዎች ለፈታኞች ገለጻ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ የተፈታኞች ገለጻ የሚደረግ ይሆናል።
4.3K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:12:09
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ጋር በጋራ እራት ተመገቡ።

ፕሮፌሰሩ ቀን በነበራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ተማሪዎቹ የተሳፈሩባቸው ባሶች በመግባት ጭምር የጎበኙ ሲሆን በእራት ሰዓት በነበራቸው ቆይታ " የጉዟቸውን ሁኔታ ማየት፣ የሚበሉትን በልተን ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ስለሚገባን ያንን እያደረግን ነው። ወላጆች የልጆቻቸው ደህንነት ሳያሳስባቸው በሙሉ ልባቸው እንዲተማመኑብን እንፈልጋለን" ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከተማሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ተማሪዎችን አበረታተዋል። የህይወት ልምዳቸውንም አጋርተዋል።
2.1K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ