Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 82.27K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-10-08 17:55:47
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ሲቀበል የዋለ ሲሆን አሁን ተፈታኞች ሁሉም ተጠቃለው ገብተዋል።
3.2K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 17:35:50
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበሉን ቀጥሏል፡፡
----------------------
ዩኒቨርሲቲው በሦስተኛ ቀን ውሎው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ነው

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮ-ጅቡቲ ምድርባቡር የድሬደዋ ጣቢያ በመገኘት ለተማሪዎቹ አቀባበል አድርገዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲምን እንደተናገሩት ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ከገቡበት ሰዓት አንስቶ የመኝታ ክፍልና የምግብ አገልግልትን እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግልቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ነገ እሁድ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ስታዲየም ለተፈታኝ ተማሪዎች የፈተናውን አስጣጥና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ምንጭ;- የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ህዝብ ግንኙነት
2.9K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 17:26:36
የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

---------------------------------------------------
ፈተናውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።

ተፈታኞችም ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ወደ ዩኒቨርስቲው እየገቡ ይገኛሉ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ዩኒቨርስቲው ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያደረገውን ዝግጅት እና አቀባበል ተመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ምልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ9 ካምፓሶቹ ከ38 ሺህ በላይ ተፈታኞቹን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

#ምስጋና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
2.6K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 17:44:39
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከወላይታ ዞን እና ከሀድያ ዞን የተመደቡ ከ19 ሺህ የሚበልጡ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
--------------------------------------------
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠናቀቂያ ፈተና እንዲወስዱ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የመጀመሪያ ዙር የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በመግባት ላይ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ከወላይታ ዞን እና ከሀድያ ዞን የተመደቡ ከ19 ሺህ የሚበልጡ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ለተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል፣ የምግብ እና የመኝታ፣ የሕክምና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸው ተገልጿል።
1.7K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 17:43:00
ዲላ ዩኒቨርስቲ ከ16 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
-----------------------------------------

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በሁለት ዙር በጥቅሉ ከ 20 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስፈትን ሲሆን፣ አሁን ላይ በመጀመሪያ ዙር የሚፈተኑ ከ16 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

የመፈተኛ ክፍል ዝግጅት፣ የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ እና የህክምና አገልግሎት መስጫ የስራ ክፍሎች ዝግጅትም ተጠናቋል።

ከትላንት ጀምሮም ከደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን እና አጎራባች አካባቢዎች እንዲሁም ከሲዳማ ክልል ተፈታኝ ተማሪዎችን፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እየመጡ ያሉ ፈታኝ መምህራንን እና የፈተና አስፈፃሚ ባለሙያዎችን እየተቀበለ ይገኛል።
1.6K viewsedited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 16:28:13
ከ70 በመቶ በላይ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመውሰድ ወደ ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ገብተዋል
--------------

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ እስካሁን ከ70 በመቶ በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ገብተዋል።

የሰላሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገናነው ጎፋ ዛሬ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው ዝግጅት አጠናቆ ከመስከረም 26 ጀምሮ ተፈታኞችን በመቀበል ላይ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው የመኝታ ክፍሎችን፣ የመመገቢያ እና የመፈተኛ ክፍሎችን አዘጋጅቶ በአሁን ወቅት ወደ 70 በመቶ የሚሆኑ ተፈታኞችን ተቀብሎ አገልግሎት መጀመሩን ዶ/ር ገናነው ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲው በአጠቃላይ 8,789 ተፈታኝ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
2.2K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 14:42:27
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
----------------------------------------------

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም  የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር ማህበራዊ ሳይንስ  ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል( ዶ/ር ) ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ዝግጅት  ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው ተፈታኝ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ዩኒቨርስቲው በመጀመሪያ ዙር 12,587 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞችን ተቀብሎ የሚያስፈትን መሆኑን ገልፀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛየመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ከ ትላንት ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እየገቡ ይገኛሉ
2.9K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 11:24:28
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 16 ትምህርት ቤቶችን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሊገነባ ነው፡፡
---------------------------------
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከትምህርት ሚኒሰቴር ጋር በመተባበር በአራት ክልሎች 16 ትምህርት ቤቶችን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶሰባስቲያን ብራንዲስ ( ዶ/ር) ጋር ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት የሚደረገውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

አስራ ስድስቱ ት/ቤቶች በአፋር፣ ሶማሌ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገነቡ ሲሆን በዓመት በአማካይ ስምንት ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

የግንባታ ስራው በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች የአዳዲስ ት/ቤቶች መገንባትን ያካተተ ሲሆን በአፋር እና አማራ ክልሎች ደግሞ ኣዳዲሰ ከሚሰሩ ት/ቤቶች በተጨማሪ በጦርነት የተጎዱ የት/ቤት ህንፃዎችን በአዲስ የመተካት ስራንም እንደሚያካትት በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የወደሙ ትምህርት ቤቶችን የመገንባቱ ስራ የሁሉንም ማህበረሰብ ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስተዋፆውን እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0FhJZNdGGu3jZGPJdz2hcxfgRZDaasCxmeZxGJQREuZe1vnpkbhi357HKGUCUwEXql&id=100064682287722
3.6K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 14:33:37
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች(የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች) ከዛሬ ጀምሮ ፈተናውን ወደ ሚወስዱበት ዩኒቨርስቲ እየገቡ ይገኛሉ።

የሰመራ፣ጎንደር፣ ዋቸሞ፣ቦንጋ እና ደብረታቦር ዩኒቨርስቲዎች በከፊል
5.7K views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 12:53:16
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያደረገውን ዝግጅት ጎበኙ
-----------------------------------------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህር ቢሮ አመራሮች የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመስጠት ያደረገውን ዝግጅት ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኚታቸዉም በፕሮግራማቸዉ መሰረት ዛሬ ለፈተና መግባት የጀመሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን አግኝተዉ አናግረዋል፡፡

ፕ/ር ብርሃኑ በጉብኝታቸውም ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዩኒቨርሲቲዎች ያደረጉት ዝግጅት አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል።

የፈተናውን ደህንነት፣ያለምንም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መመልከት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን እየታየ ያለው ውጤትም አስደሳች መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎችና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት እያደረጉት ያለው ጥረቶች ምን ያህል አቅም እንዳለ የሚያሳይና የሚያስመሰግን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አሁን መፈተን ለማይችሉ ተማሪዎች ፈተናውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የ2014ዓም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እየገቡ ይገኛሉ።
3.9K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ