Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Education Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_moe — Ministry of Education Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_moe
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81.50K
የሰርጥ መግለጫ

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-02-29 17:14:35
የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካቲት 21/2016 ዓ.ም(ትሚ) «ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!»በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ128ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ሰንደቅ አላማ በጋራ በመስቀልና ሊሎች መርሃግብሮች አክብረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ችቦ እና አርማ በመሆኑ የድሉን እሴቶችና ቱሩፋቶች በሚገባ ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንደሃገር የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሆነው አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ተጠናቆ በተመረቀበት የሚከበር በመሆኑ ድሉን ድርብ ያደርገዋልም ብለዋል

ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የመስቀል መርሃ ግብሩን ተከትሎ በማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ሃላፊ አቶ ኡመር ኢማም የውይይት መነሻ ያቀረቡ ሲሆን የህዝቦች አብሮ የመኖርና የመልማት እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳዮች ላይ ይህ ትውልድ ከአባቶቹ ብዙ መማር እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡

ሙሉ ዜናው

https://www.facebook.com/share/p/xzABkDHNRqFwizd4/?mibextid=oFDknk
15.7K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 13:29:52
የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን የካቲት 22/2016 ዓ.ም ይከበራል!
.........................................................................................................................................................
የካቲት 21/2016 ዓ.ም (ትሚ) የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ነገ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ይከበራል።

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እኤአ አቆጣጠር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲከበር በወሰኑት መሠረት የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በየአመቱ ማርች አንድ በህብረቱ አባል ሀገራት አስተናጋጅነት እየተከበረ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህ አመትም 9ኛው የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን  "አካታችና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ላይ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይገባል” በሚል መሪ ቃል ነገ በድሬደዋ ከተማ  ይከበራል፡፡

በኢትዮጵያ ከ6.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሲሆኑ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ማጠናከር መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ የሁሉንም ዜጋ ትብብር ይሻል!

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
16.9K views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-26 14:52:02
#ማስታወቂያ

ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ

የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ ም ጀምሮ ስለተለቀቀ

https://result.ethernet.edu.et

ሊንክ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
19.2K viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-22 21:29:20
#ማስታወቂያ

የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ለምርምር ጆርናል ባለቤቶችና ለሀገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለምርምር ተቋማት እና ሙያ ማህበራት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ የሚታተሙ የምርምር ጆርናሎች ጥራትና እይታን ለማሳደግ ሲባል የምዘናና እውቅና አሰራር ስርአት መዘርጋቱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ከተመሰረተ 3 አመት የሞላቸው ጆርናሎችን የምታስተዳድሩና የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ Amended Guideline for Evaluation of Journals Published in Ethiopia No.: Research 01/2019) መስፈርቶችን የምታሟሉ ተቋማት በጆርናሉ ዋና አርታኢ በኩል ይህ ደብዳቤ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ

በhttp://survey.ethernet.edu.et/index.php/888858?lang=en

የተቀመጠውን ቅጽ በመጠቀም እንድታመለክቱ ጥሪ እያደረግን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ
ethiojournalaccreditation@ethernet.edu.et

በመላክ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
ይህ ማስታወቂያ በ2015 ዓ.ም አራተኛ ዙር ያመለከቱትንና ለዳግም እውቅና አመልክተው ፍተሻው በሂደት ላይ ያሉትን ጆርናሎች አይመለከትም፡። ይሁን እንጂ የግምገማ ውጤቱ እንደታወቀ መስፈርቱን ባለማሟላት እውቅና ለማያገኙ አመልካቾች ሚ/ር መስሪያ ቤቱ ወደፊት በልዩ ሁኔታ የሚያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፤

ማንኛውም አመልካች የሀገር ውስጥ ጆርናሎች ፍተሻ እና እውቅና አሰጣጥ Amended Guideline for Evaluation of Journals Published in Ethiopia No.: Research 01/2019) መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል፤

ትምህርት ሚኒስቴር
34.6K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-21 16:34:54
የማላዊ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የካቲት 13/2016 ዓ.ም(ትሚ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሸኔ የማላዊ ትምህርት ሚኒስቴር ሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር የሆኑትን ፕ/ር ቻሞራ ሜኬካን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ የትብብር መስኮች በተለይም በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ትብብር ለመፍጠር በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

በተያያዘም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በኩል በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎረም ተግባራትን አስመልክቶ በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በኩል ገለጻ ተደርጓላቸዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር ፍላጎት ለመለየት እና ወደፊት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማስጀመር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
26.1K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-20 20:22:54
የፊንላንድ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::
የካቲት 12/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የሁለቱ ወገኖች ውይይት ያተኮረው በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን በዋነኝነትም በአካቶ እና የልዩ ፍለጎት ትምህርት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በውይይቱ ወቅት ባደረጉት ገለጻ ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ውስጥ የፊንላንድ መንግሰትና ህዝብ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ እያይዘው በኢትዮጵያና ፊንላንድ መንግሰት መካከል ያለው ዘላቂ የትምህርት ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ትብብር ማሳያ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ክብርት አምባሳደሯ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ገለጻ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በትምህርቱ ዘርፍ በተለይም በአካቶና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሙሉ ዜናው
https://www.facebook.com/share/XjVxHDGGUvC37nLJ/?mibextid=oFDknk
26.4K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-15 17:58:08
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ ።

...................................................
የካቲት 7/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞች ምዝገባን በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች የመመዝገቢያ መስፈርቱን በማሟላት በተቀመጠው የጊዜ ገድብ መመዝገብ እንዳለባዉ አብራርተዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም እንደሚከተለው አሳስበዋል።

1. በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ እንዳለባቸው ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ

2. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል

3. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ መቻል

4. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት እንደሚሆን

5. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወረዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች እንደሚከናወን የየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
69.0K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-15 15:09:56
31.6K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-14 20:05:19
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀመረ

..............................................
የካቲት 6/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የተመደቡ ታዛቢዎችም በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ ጀምረዋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች  በ204 የፈተና ፕሮግራሞች የሚፈተኑ ሲሆን የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
36.8K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-13 21:16:43
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸውም ተገልጿል ።
..............................................
የካቲት 5/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጅና(ፒኤችዲ) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉንና በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።

የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውንም ዶ/ር ኤባ ገልጸዋል ።

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
38.0K viewsedited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ