Get Mystery Box with random crypto!

ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀመረ ............ | Ministry of Education Ethiopia

ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀመረ

..............................................
የካቲት 6/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የተመደቡ ታዛቢዎችም በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ ጀምረዋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች  በ204 የፈተና ፕሮግራሞች የሚፈተኑ ሲሆን የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።